ማስታወቂያዎች
◼ በነሐሴ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማንኛውንም መጠቀም ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ ” (እንግሊዝኛ)፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም (እንግሊዝኛ)፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴት ልታውቀው ትችላለህ? (እንግሊዝኛ) እና የምትወዱት ሰው ሲሞት (እንግሊዝኛ)። መስከረም፦ ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ እናበረክታለን። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ጥረት መደረግ አለበት። ጥቅምት፦ ንቁ! ወይም መጠበቂያ ግንብ ኮንትራት ማስገባት። የመጽሔቶቹን ቅጂዎች ለማበርከት ልዩ ጥረት አድርጉ። ኅዳር፦ የቤተሰብ ኑሮ እና/ወይም ወጣትነትህ የተባሉት መጽሐፎች እያንዳንዳቸው በ3 ብር ይበረከታሉ። ከላይ የተዘረዘሩትን የዘመቻ ጽሑፎች እስካሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S–14–AM) መጠየቅ አለባቸው።
◼ ለ1996 የአገልግሎት ዓመት የሚያገለግሉ በቂ መጠን ያላቸው ቅጾች ለእያንዳንዱ ጉባኤ እየተላኩ ነው። እነዚህ ቅጾች በከንቱ መባከን የለባቸውም። ለታቀደላቸው ዓላማ ብቻ ሊውሉ ይገባል።
◼ እያንዳንዱ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S–18–AM) ይደርሱታል። የጉባኤው ጸሐፊና የጽሑፍ አገልጋዩ በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎች የሚቆጠሩበትን ቀን ለመወሰን በወሩ መጀመሪያ ላይ ተገናኝተው መነጋገር አለባቸው። በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎች ሁሉ አንድ በአንድ መቆጠር አለባቸው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ ላይ መሞላት አለበት። በጉባኤው እጅ ያሉትን የመጽሔቶች ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ ማግኘት ይቻላል። እባካችሁ ከመስከረም 6 በፊት ዋናውን ቅጂ ለማኅበሩ ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ በፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሥሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ጸሐፊው ቆጠራው ትክክል መሆኑን መቆጣጠር ሲኖርበት ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ተሠርቶ ያለቀውን ቅጽ መመርመር አለበት። ጸሐፊውና ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በቅጹ ላይ ይፈርማሉ።
◼ የመጽሐፍ ጥናት፦ ከመስከረም 1995 በመጀመር መንግሥትህ ትምጣ የተባለው መጽሐፍ ይጠናል። ጥልቀት ያለው ዝግጅትና ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ እናበረታታችኋለን።
◼ የአውራጃ ስብሰባ፦ “ደስተኛ አወዳሾች” የሚል ጭብጥ የያዘ የአውራጃ ስብሰባ በአዋሣ ከመስከረም 15–17፤ በአዲስ አበባ ከጥቅምት 6–8, 1995 ይካሄዳል።
◼ በእጃችን ያሉ አዳዲስ ጽሑፎች
ለሁሉም ሰዎች የሚሆን ምሥራች (በዓለም ላይ በሚገኙ ዋና ዋና ቋንቋዎች የተዘጋጁ ለናሙና የሚሆኑ ምሥክርነቶች ያሉበት የእንግሊዝኛ ቡክሌት)፤ ኢንዴክስ 91–93 (እንግሊዝኛ)፤ ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? የተባለው ትራክት ቁ. 22 (ትግርኛ)
ካሴት:- ታላቁ ሰው (እንግሊዝኛ)
የቪዲዩ ካሴቶች:- በመለኮታዊ ትምህርት አንድ መሆን (እንግሊዝኛ)፤ መጽሐፍ ቅዱስ— ትክክለኛ ታሪክና አስተማማኝ ትንቢት (እንግሊዝኛ)
◼ በቅርቡ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች፦
እንግሊዝኛ፦ ፍጥረት (ትንሹ)፤ ኮንኮርዳንስ፤ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፤ ኪንግደም ኢንተርሊኒየር፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ፤ ማመራመር፤ የወጣቶች ጥያቄ።
ካሴቶች:- ታላቁ ሰው፤ መጽሐፌ
እነዚህን ጽሑፎች ማዘዝ ትችላላችሁ። በልዩ ትእዛዝ የሚገኙ ጽሑፎችን በግል የሚጠይቋችሁ ካሉ ልታዙ ትችላላችሁ፤ እንደዚህ ከሆነ የመጡት ጽሑፎች ሁሉ ተወስደው በዚያው ወር ሒሳቡን መላክ ይቻላል።