የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/95 ገጽ 2
  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ነሐሴ 7 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 14 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 21 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 28 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 8/95 ገጽ 2

የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ነሐሴ 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 177

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሰዎችን ለማነጋገር ሊጠቅሙን የሚችሉ በቅርብ በወጡ መጽሔቶች ውስጥ የሚገኙ ርዕሶችን ጥቀስ።

15 ደቂቃ፦ “እንዴት ዓይነት ሰዎች ልትሆኑ ይገባችኋል?” በጥያቄና መልስ።

20 ደቂቃ፦ “በብሮሹሮች በመጠቀም የአምላክ ቃል አስተማሪዎች ሁኑ።” ይህንን ክፍል እንዲያቀርብ የተመደበው ወንድም ስለ ብሮሹሮቹ የተለያዩ ገጽታዎች ከሌሎች ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ጋር ይወያያል። ከዚያም አንዳቸው ከሌላው ጋር በመሆን አቀራረባቸውን ይለማመዳሉ። በተጨማሪም “ለእያንዳንዱ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ እወቁ” በሚለው ርዕስ ውስጥ የተገለጹትን ዋና ዋና ነጥቦች ጥቀስ።

መዝሙር 204 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 191

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

13 ደቂቃ፦ “መልካም ፍሬ የሚያስገኙ ተመላልሶ መጠየቆች ውጤታማ የማስተማር ችሎታ ይጠይቃሉ።” ዋና ዋና ነጥቦችን ከልስና አንድ ወይም ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ “ደስተኛ ወላጆች!” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በ16–108 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 6–8 አንቀጽ 14–23 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ።

12 ደቂቃ፦ “በትምህርት ቤት ልታሳየው የሚገባ ክርስቲያናዊ ጠባይ።” በጥያቄና መልስ። ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በመሆን በሐምሌ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 23–6 ላይ በተለይ ልጆች ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ ጉዳዮች የሚናገረውን ክፍል እንዲከልሱ አበረታታ።

መዝሙር 174 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 33

7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ለሚቀጥለው ሳምንት ስብሰባ በሐምሌ መአ ላይ የወጣውን አባሪ ገጽ ይዘው እንዲመጡ አሳስባቸው።

18 ደቂቃ፦ “ለማንኛውም መልካም ሥራ ራሳችንን በፈቃደኝነት ማቅረብ።” ከ1–9 ባሉት አንቀጾች ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ግለት ያለው ንግግር።

20 ደቂቃ፦ “ለማንኛውም መልካም ሥራ ራሳችንን በፈቃደኝነት ማቅረብ።” ከ10–15 ያሉትን አንቀጾች በጥያቄና መልስ ሸፍን። ለጉባኤው የሚያስፈልጉትን ነገሮችና ሁሉም እርዳታ ማበርከት የሚችሉባቸውን መንገዶች ጥቀስ።

መዝሙር 172 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 155

5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ በመስከረም ወር ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። ይህ መጽሐፍ የይሖዋን የፍርድ መልእክት በማስተላለፍ ረገድ ምን ያህል ጠቃሚ ሚና እንደሚጫወት አብራራ። (7–109 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18 ከአንቀጽ 17–18 ተመልከት።) በሚያዝያ 1, 1992 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 15 አንቀጽ 3–4 ላይ ያሉትን ተሞክሮዎች ተናገር። በመጽሐፉ ውስጥ በገጽ 3, 11–13 እና 156–8 ባሉት ትኩረት የሚስቡ ሥዕሎች ላይ እንዲያተኩሩ አድርግ። እነዚህ ሥዕሎች ውይይት ለማስጀመር ሊያገለግሉ የሚችሉባቸውን መንገዶች አብራራ። አንድ ችሎታ ያለው አስፋፊ ከገጽ 156–8 ላይ ከቀረቡት ጥቅሶች መካከል በአንዱ ሲጠቀም የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ጥረት ለማድረግ ግብ እንዲያወጡ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ሁሉም በዚህ ሳምንት መጨረሻ የሚጠቀሙባቸውን ቅጂዎች እንዲወስዱ አስታውሳቸው።

25 ደቂቃ፦ “‘ደስተኛ አወዳሾች’ የ1995 የአውራጃ ስብሰባ።” በሐምሌ መአ አባሪ ገጽ ላይ የተመሠረተ በጥያቄና መልስ የሚሸፈን ክፍል።

መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ