የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/96 ገጽ 7
  • ለስኬታማነት ቁልፉ ዝግጅት ነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለስኬታማነት ቁልፉ ዝግጅት ነው
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዝግጅት በማድረግ ለሰዎች ልባዊ አሳቢነት አሳዩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • አስቀድሞ መዘጋጀት ደስታ ያስገኛል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • “መልካም የሆነውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ” ሁኑ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ውጤታማ ሆኖ ካገኛችሁት ተጠቀሙበት!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 3/96 ገጽ 7

ለስኬታማነት ቁልፉ ዝግጅት ነው

1 ለመስክ አገልግሎት ቀደም ብሎ መዘጋጀት አንድ ሰው በመስክ አገልግሎት ለመካፈልና ላለመካፈል በውስጡ ሊፈጠር የሚችለውን የማመንታት ስሜት እንዲያሸንፍ ይረዳል። ወደ በሩ ስትደርስ ለቤቱ ባለቤት መናገር የምትፈልገውን ነገር ታውቃለህ። ሊገጥምህ የሚችለውን ፈታኝ ሁኔታ እያሰብክ ጭንቅ ጥብብ አይልህም። አገልግሎትህን ጨርሰህ ወደ ቤት ስትመለስ በአገልግሎት ተገቢውን ጥረት እንዳደረግህ ስለምታውቅ ትበረታታለህ። አዎን፣ የመስበክና የማስተማር ሥራችን በይበልጥ ለማሻሻል ቁልፉ የተሟላ ዝግጅት ማድረግ ነው።

2 ጳውሎስ ‘በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችን ተጫምተው እንዲቆሙ’ በማሳሰብ ዝግጁ የመሆንን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርጎ ገልጿል። (ኤፌ. 6:15) ይህም አእምሮና ልባችንን ማዘጋጀትን እንዲሁም አዎንታዊ አመለካከትና የፈቃደኝነት ዝንባሌ መያዝን ይጨምራል። እውነትን ለሌሎች ለማካፈል ዝግጅት ካደረግን የመንግሥቱ ፍሬ ስለሚክሰን ደስታ እናገኛለን።— ሥራ 20:35

3 ለስብከቱ ሥራ ዝግጅት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?፦ ማመራመር ከተባለው መጽሐፍ ውስጥ ወይም በመንግሥት አገልግሎታችን የመጨረሻ ገጽ ላይ ከሚገኙት አቀራረቦች መካከል የሚቀለንን አቀራረብ መምረጥ ይኖርብናል። ልትጠቀምበት ያሰብከውን ጥቅስ በደንብ አስብበት፤ ዋናውን መልእክትህን ለማጉላት እንድትችል ጠበቅ አድርገህ ልትገልጸው የፈለግኸውን ቃል ወይም ሐረግ ምረጥ። አቀራረብህን በቃልህ መሸምደድ አያስፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ ሐሳቡን ብቻ በአእምሮህ ይዘህ በራስህ አባባል ማስቀመጥና አድማጭህን ይስባል ብለህ በምታስበው መንገድ መናገር የተሻለ ነው።

4 ልታበረክተው ያሰብኸውን ጽሑፍ በመመርመር የሰዎችን ፍላጎት የሚቀሰቅሱ ጥቂት መነጋገሪያ ነጥቦች ምረጥ። በአገልግሎት ክልልህ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ትኩረት ይስባል ብለህ የምታስበውን ነጥብ ምረጥ። የተለያዩ ሰዎች ማለትም ወንድ፣ ሴት፣ በዕድሜ የገፉ፣ ወይም ወጣቶች ስታገኝ አቀራረብህን እንደ ሁኔታው እንዴት ማስተካከል እንደምትችል አስቀድመህ አስብ።

5 የልምምድ ፕሮግራም እንዲኖርህ ለማድረግ ሞክረህ ታውቃለህን? ከቤተሰብ አባሎችህ ወይም ከሌሎች አስፋፊዎች ጋር አንድ ላይ በመሆን ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት የትኞቹ አቀራረቦች እንደሆኑ ከተወያያችሁ በኋላ ሁላችሁም በአእምሯችሁ ልትቀርጿቸው እንድትችሉ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ተለማመዷቸው። በአገልግሎት ክልል ውስጥ ሊያጋጥሟችሁ የሚችሉትን ሁኔታዎችና ተቃውሞዎች ለማስመሰል ሞክሩ። እንዲህ ዓይነቱ ልምምድ የንግግር ጥራታችሁንና በስብከቱ ሥራ ያላችሁን ውጤታማነት የሚያሻሽልላችሁ ከመሆኑም በተጨማሪ ይበልጥ ትምክህት እንዲኖራችሁ ይረዳችኋል።

6 አቀራረብህን ከመዘጋጀትህና ከመለማመድህ በተጨማሪ ራስህን እንደሚከተለው እያልክ ጠይቅ:- ‘ልለብሰው ያሰብኩት ልብስ ለአገልግሎት ተስማሚ ነውን?’ በመጽሐፍ መያዣ ቦርሳዬ ውስጥ ልጠቀምባቸው ያሰብኳቸውን ጽሑፎች ጨምሮ የምፈልገውን ነገር ሁሉ ይዤአለሁን? ቦርሳው በጥሩ ሁኔታ የተያዘ ነውን? ማመራመር የተባለውን መጽሐፍ፣ ትራክቶች፣ ከቤት ወደ ቤት መመዝገቢያ ቅጽና እርሳስ ይዤአለሁን? አስቀድሞ ዝግጅት ማድረግ በአገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ የሆነ ቀን ለማሳለፍ ይረዳል።

7 ዝግጅት ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ ከጣርን በኋላ የይሖዋ መንፈስ ስኬታማ እንድንሆን እንዲረዳን መጸለይ ይኖርብናል። (1 ዮሐ. 5:14, 15) ለዝግጅት ትልቅ ትኩረት መስጠት ‘አገልግሎታችንን ሙሉ በሙሉ ስንፈጽም’ በሥራችን በጣም እንድንደሰት ያስችለናል።— 2 ጢሞ. 4:5

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ