የሚያዝያ ወር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ሚያዝያ 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 105
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የመታሰቢያውን በዓል በተመለከተ ጎላ ያሉ ሪፖርቶች ካሉ ጥቀስ።
20 ደቂቃ፦ “በሚያዝያ ወር ‘መልካም ሥራዎችን ለመሥራት ቀናተኞች’ ሁኑ!” የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከ1-10 ያሉትን አንቀጾች በጥያቄና መልስ ያቀርባቸዋል። (1) በሚያዝያ ወር የጉባኤውን የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴ ለማስፋት ምን የታቀደ ነገር አለ? (2) ሁሉም ተሳታፊዎች እንዲሆኑ እርዳታ ሊደረግላቸው የሚችለው እንዴት ነው? እንዲሁም (3) አዲሶችና ልጆችም ጭምር ሊሳተፉ የሚችሉት እንዴት ነው? የሚሉትን ነጥቦች አብራራ።
15 ደቂቃ፦ “ትክክለኛ ዝንባሌ ያላቸውን ሰዎች ፈልጉ።” የተሰጡትን አቀራረቦች ከልስና እንዴት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በመስከረም 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 5 ላይ መጽሔት ስለማበርከት የተሰጡትን ሐሳቦች ጥቀስ።
መዝሙር 47 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 33
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት፤ የተላከው መዋጮ እንደ ደረሰ የሚያሳይ ከማኅበሩ የተላከ ደብዳቤ ካለ ጥቀስ። በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ አዳዲስ ሰዎች በመንፈሳዊ እንዲያድጉ ለመርዳት የሚቻልባቸውን ተግባራዊ መንገዶች አብራራ። በሚያዝያ 1, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 9-12 ላይ ያለውን ሐሳብ ከልስ።
15 ደቂቃ፦ “ቀንና ሌሊት ቅዱስ አገልግሎት አቅርቡ።” ጥያቄና መልስ። አንቀጽ 5 እና 6ን አንብብ።
15 ደቂቃ፦ “በሚያዝያ ወር ‘መልካም ሥራዎችን ለመሥራት ቀናተኞች’ ሁኑ!” ከ11-15 ያሉት አንቀጾች በጥያቄና መልስ ይሸፈናሉ። ሁሉም የራሳቸውን ሁኔታ እንዲመረምሩና በመስክ አገልግሎት የሚያበረክቱትን እርዳታ ከፍ የሚያደርጉበትን መንገድ እንዲፈልጉ አበረታታ።
መዝሙር 113 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 136
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሚያዝያ 21 “በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ መኖር” በሚል ርዕስ ልዩ የሕዝብ ንግግር እንደሚሰጥ አድማጮችን አስታውሳቸው። ሁሉም በንግግሩ ላይ ለመገኘት ተጨማሪ ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “ጊዜው ተለውጧል።” ጥያቄና መልስ። የመንግሥቱን መልእክት በጣም አጣዳፊ ከሆኑት የሰዎች ፍላጎቶች ጋር በሚስማማ መንገድ ስለማቅረብ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። በጥር 1, 1994 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22-3 ላይ እንደሰፈሩት ያሉ በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ የሚጉላሉ ቤተሰብ ነክና ማኅበራዊ ጉዳዮችን ጥቀስ።
20 ደቂቃ፦ “እምነት ከመስማት ነው።” መጽሔት በማበርከት የሰዎችን ፍላጎት አነሳስቶ እውቀት ወይም ለዘላለም መኖር በተባሉት መጽሐፎች ወይም በደስታ ኑር! በተባለው ብሮሹር አማካኝነት ጥናቶች ማስጀመር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ አብራራ። ሁለት ወይም ሦስት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
መዝሙር 204 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ባለፈው እሑድ በቀረበው ልዩ ንግግር ላይ የተጠቀሱትን ጎላ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከልስ። በንግግሩ ላይ የተሰጠው ምክር ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን በእውነተኛው አምልኮ ጎን እንዲቆሙ የሚያንቀሳቅሳቸው እንዴት እንደሆነ አብራራ። በተጨማሪም “በትክክለኛ እውቀት እያደጋችሁ መሄዳችሁን ቀጥሉ” የሚለው ክፍል ላይ በማተኮር በጉባኤ መጽሐፍ ጥናት ዘወትር የመገኘትን አስፈላጊነት ጎላ አድርገህ ግለጽ።
12 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
18 ደቂቃ፦ አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ላይ ከገጽ 138-142 የሚገኘውን “ችግሮች በሚነሱበት ጊዜ” የሚለውን ጭብጥ በጥያቄና መልስ ሸፍን። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን የተመደቡትን አንቀጾችና የተጠቀሱትን ጥቅሶች አንብብ። ሁሉም ክርስቲያናዊ ሰላማችንንና አንድነታችንን በመጠበቅ ረገድ ንቁዎች እንዲሆኑ አበረታታ።
መዝሙር 191 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 29 የሚጀምር ሳምንት
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አንዳንድ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች “መናፍቃን” ወይም “መጤ” እንደሆኑ በመናገር ሌሎች ስለ እንቅስቃሴያችንና ስለ ዓላማችን የተሳሳተ ሐሳብ እንዲያድርባቸው ያደርጋሉ። ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ገጽ 202 በመጠቀም ለዚህ ክስ እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚቻል በአጭሩ ግለጽ።
15 ደቂቃ፦ ክልላችንን በተሟላ ሁኔታ አጣርቶ መሸፈን። በአገልግሎት የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ዘርዘር ብለው ወይም ርቀው የሚገኙ ቦታዎች ብዙም አልተሠራባቸው ይሆናል። አንዳንዶች ሆን ብለው ሀብታሞች ወይም አጥባቂ ሃይማኖተኛ ሰዎች በሚኖሩባቸው ቦታዎች ከማገልገል ታቅበው ይሆናል። የንግድ ክልሎች ችላ ተብለው ሊሆን ይችላል። አንዳንድ አስፋፊዎች በወቅቱ መሸፈን የሚኖርባቸውን ክልሎች ሳይሆን ራሳቸው የመረጡትን ክልል አዘውትረው ይጠይቁ ይሆናል። ያልተሠራባቸውን ክልሎች ለመሸፈን በሚደረገው ጥረት ሁሉም እንዲተባበሩ አበረታታቸው። ክልሉን ከመመለሳችሁ በፊት እቤት አልተገኙም የተባሉትን ጨምሮ ክልሉ አንድ በአንድ ተጣርቶ እንደተሸፈነ አረጋግጡ። ክልላችሁን በተሻለ ሁኔታ ለመሸፈን ሁሉም ድጋፍ መስጠት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ የሚያሳዩ ሌሎች ተግባራዊ ሐሳቦችን አቅርብ።
18 ደቂቃ፦ በግንቦት ወር መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን አበርክቱ። ነጠላ ቅጂዎችን አበርክቱ። ቶሎ ቶሎ በሚሸፈኑ ክልሎች ማንኛውንም ተስማሚ የሆነ ብሮሹር አበርክቱ። የመጽሔት ደንበኛ የማግኘት ግብ ይዛችሁ ያበረከታችሁላቸውን ሰዎች በጠቅላላ መዝግቧቸው። ፍላጎት ካላቸው ኮንትራት እንዲገቡ መጋበዝ ይቻላል። መጽሔት ማሰራጨት የመንግሥቱ መልእክት ወደ ሰዎች እንዲደርስ ከሚያስችሉ ይበልጥ ውጤታማ የሆኑ መንገዶች አንዱ እንደመሆኑ መጠን ይህ ሥራ ያሉትን ከፍተኛ ጥቅሞች ጎላ አድርገህ ግለጽ። ወደ አገልግሎት ስንወጣ በቂ መጽሔቶች እንደያዝን እናረጋግጥ። በማንኛውም አጋጣሚ እናበርክት። በግላችን ሳምንታዊ የመጽሔት ቀን መመደባችን ብዙ መጽሔቶችን ለማበርከት ከሚያስችሉን መንገዶች አንዱ ነው። ከሱቅ ወደ ሱቅ እና በመንገድ ላይ በሚደረግ ምሥክርነት መጽሔቶችን ማበርከትም ውጤታማ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ አድርጉላቸው። በቅርቡ የወጡ መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳይ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ለሠርቶ ማሳያዎቹ በመስከረም 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 አንቀጽ 3-5 ላይ የሚገኙትን አቀራረቦች መጠቀም ይቻላል። አንቀጽ 16ን አንብብ።
መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።