ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ነጠላ ቅጂዎች፤ በተጨማሪም ቶሎ ቶሎ በሚሸፈን ክልል ማንኛውንም ተስማሚ ብሮሹር መጠቀም ይቻላል። ኮንትራት እንዲገቡ መጋበዝም ይቻላል። ሰኔ፦ ታላቁ ሰው (እንግሊዝኛ) ወይም ለዘላለም መኖር። ሐምሌና ነሐሴ፦ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ውስጥ ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ? (እንግሊዝኛ)፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች እና የሙታን መናፍስት ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
◼ ሰባኪው ‘ተስማሚ የሆኑትን የእውነት ቃላት’ ለማግኘት እንደመረመረ ሁሉ እኛም ለምደናቸው በነበሩ ቲኦክራሲያዊ ቃላት ላይ አንዳንድ ጊዜ ለውጥ እናደርጋለን። (ምሳሌ 4:18) በዚህ መሠረት “ዲያቆን” በሚለው የአማርኛ ቃል ላይ ለውጥ የተደረገ ሲሆን ከአሁን በኋላ የምንጠቀመው “የጉባኤ አገልጋይ” ብለን ነው። ይህ ለውጥ በዚህ የአገልግሎት መብት የሚያገለግሉ ወንድሞች የሚያቀርቡትን ትሕትና የተሞላበት አገልግሎት ከማሳየቱም በተጨማሪ ከዓለምና ከታላቂቱ ባቢሎን እንድንለይ ያደርገናል።