የግንቦት ወር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ግንቦት 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። “ወደ ሌላ ቦታ ለመጓዝ ስትነሱ . . .” የሚለውን ርዕስ ከልስ። በሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት ለሚደረጉ የአገልግሎት ስብሰባዎች ሁሉም አገልግሎታችን የተባለውን መጽሐፍ የራሳቸውን ቅጂ ይዘው እንዲመጡ አስታውሳቸው።
15 ደቂቃ፦ “በሙሉ ነፍስ አገልግሉ!” ጥያቄና መልስ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በ10-102 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 12 ላይ ያለውን “በቤተሰብ መልክ ሆናችሁ የምትወያዩባቸው ነጥቦች” የሚለውን ተነጋገሩበት።
20 ደቂቃ፦ “ለሰዎች እውነትን ተናገሩ።” ጥያቄና መልስ። የተሰጡትን አቀራረቦች ከልስ። አዳዲሶች በአጫጭር አቀራረቦች ተጠቅመው ውይይት በማስጀመር መጽሔት በማሰራጨቱ ሥራ እንዲካፈሉ አበረታታ።
መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47
7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
18 ደቂቃ፦ “እንዳሁኑ የተትረፈረፈ መንፈሳዊ በረከት ያገኘንበት ጊዜ የለም!” ጥያቄና መልስ። አንድ በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኝ አስፋፊ ጨምሮ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ካገኟቸው በረከቶች መካከል ጥቂቶቹን እንዲናገሩ አድርግ። አድናቆታችን ሲጨምር በቅዱስ አገልግሎት በቅንዓት ለመካፈል ምን ያህል እንደሚያንቀሳቅሰን በመግለጽ ደምድም።
20 ደቂቃ፦ “ከበድ ያሉ ኃጢአቶችን ችላ ብሎ አለማለፍ”— ክፍል 1። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ንግግሩ አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 142 እስከ 147 (ንዑስ ርዕስ) ላይ የተመሠረተ ሲሆን መደምደሚያው ላይ ጥቂት የክለሳ ጥያቄዎች ይኖሩታል። ይሖዋ ድርጅቱን የሚባርከው በሥነ ምግባር ንጹሕ ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ ግለጽ።
መዝሙር 13 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 105
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም በመጽሔት ማሰራጨቱ ሥራ እንዲካፈሉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “እውነትን መናገራችሁን ቀጥሉ።” በልዩ ዘመቻው ወቅት መጽሔት ለተበረከተላቸው ሰዎች ሁሉ ጥናት የማስጀመር ግብ ይዞ ተመላልሶ የማድረግን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ኮንትራት እንዲገቡ ግብዣ አቅርቡላቸው። ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “ከበድ ያሉ ኃጢአቶችን ችላ ብሎ አለማለፍ”— ክፍል 2። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ንግግሩ አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 147-153 ላይ የተመሠረተ ሲሆን በየንዑስ ርዕሱ አጫጭር የክለሳ ጥያቄዎች ይኖሩታል።
መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 121
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር።” አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 13 ላይ የተመሠረተ ንግግር።
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። እያነበብክ ከአድማጮች ጋር ተወያይበት።
15 ደቂቃ፦ “ሥራ በጣም ይበዛብሃልን?” ጥያቄና መልስ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በሰኔ 8, 1990 የእንግሊዝኛ ንቁ! መጽሔት ከ14-16 ባሉት ገጾች ላይ የሰፈሩትን ነጥቦች ጨምረህ አቅርብ። አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች በቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች ተወጥረው በተሳካ ሁኔታ ሥራቸውን የተወጡት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድርግ።
መዝሙር 155 እና የመደምደሚያ ጸሎት።