የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/96 ገጽ 2
  • የሰኔ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሰኔ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሰኔ 3 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 10 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 17 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 24 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 6/96 ገጽ 2

የሰኔ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ሰኔ 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 191

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በአገሪቱና በጉባኤው ወርኃዊ የአገልግሎት ሪፖርት ላይ አንዳንድ ሐሳብ ስጥ።

15 ደቂቃ፦ “በእምነታቸው ምሰሏቸው።” ጥያቄና መልስ። በመስከረም 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 13 ላይ በሚገኘው ሣጥን ውስጥ የሠፈሩትን የእምነት መግለጫዎች ጥቀስ። ከአንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ጋር ቃለ ምልልስ በማድረግ ለብዙ ዓመታት አዘውትረው በመንግሥቱ ሥራ እንዲቀጥሉ የረዳቸው ምን እንደሆነ እንዲናገሩ አድርግ።

20 ደቂቃ፦ “ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራውን እውቀት ማሠራጨት።” (አንቀጽ 1-5) በመጀመሪያ አንቀጽ 1 ላይ ያለውን ሐሳብ አቅርብ። (በጥር 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 12-13 አንቀጽ 11-12 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።) የመንግሥት አገልግሎታችን የመጨረሻ ገጽ አዲስ መልክ መያዙ መጀመሪያ ያነጋገርናቸውን ሰዎች ተመልሰን ለመጠየቅ የተዘጋጀን እንድንሆን ታስቦ የቀረበ መሆኑን ግለጽ። ብዙውን ጊዜ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ረጅም ቀናት ከመጠበቅ ይልቅ ከአንድ ወይም ከሁለት ቀናት በኋላ ተመልሶ መሄዱ ጥሩ ስለሚሆን ከቤት ወደ ቤት ሄደን ለማነጋገርና ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ የሚያስችሉን ሁለቱም አቀራረቦች በአንድ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ይቀርባሉ። አንቀጽ 2 እና 3⁠ን በአጭሩ ከልስ፤ በሁለቱም አንቀጾች ላይ ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ። በዚህ ርዕስ ውስጥ ያሉት ቀሪዎቹ አቀራረቦች በሌላ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ይሸፈናሉ።

መዝሙር 143 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 215

7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

8 ደቂቃ፦ ልጆችን በመስክ አገልግሎት ማሠልጠን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ልጆቻችን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ከእኛ ጋር በአገልግሎት መካፈል ይኖርባቸዋል። አሁን የሚያገኙት ሥልጠናና ተሞክሮ በኋላኞቹ ዓመታት ለሚኖራቸው እምነትና ቅንዓት ጠንካራ መሠረት ይሆንላቸዋል። አገልግሎቱን በቁም ነገር መመልከትንና ራሳቸውን በሥርዓት የመምራታቸውን አስፈላጊነት መገንዘባቸው ጠቃሚ ነው። ልጆች በአገልግሎት ላይ ከመረበሽ መቆጠብ ይኖርባቸዋል፤ አገልግሎት የጨዋታ ጊዜ አይደለም። ከአዋቂዎች ጋር መሥራታቸው የተሻለ ነው። እንደ አቅማቸው አቀራረቦችን ተጠቅመው ሰዎችን በማነጋገር እንዲካፈሉ እርዳታ ሊደረግላቸው ይገባል። (መጠበቂያ ግንብ 15-109 ገጽ 17 አንቀጽ 20⁠ን ተመልከት።) ወላጆች የመቆጣጠር ኃላፊነት አለባቸው፤ የሚቆጣጠራቸው አዋቂ ሰው ሳይኖር ልጆቻቸውን ወደ መስክ ስምሪት ስብሰባዎች ሊልኳቸው አይገባም። መልካም ነገር ሲሠሩ አመስግኗቸው።

10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። (ወይም በጥር 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 29-31 ላይ የተመሠረተ “የእውነትን ቃል በትክክል የሚጠቀም” የሚል ንግግር ይቀርባል።)

20 ደቂቃ፦ “እውቀት በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት ደቀ መዛሙርት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?” በአንቀጽ 1 አና 2 ላይ የተመሠረተ አጭር የመግቢያ ሐሳብ አቅርብ። ከ3 እስከ 11 ያሉትን አንቀጾች በጥያቄና መልስ ሸፍን። የቀረው የአባሪ ገጹ ክፍል በሐምሌና በነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች ላይ እንደሚሸፈን ግለጽ። አባሪ ገጹን በጥሩ ሁኔታ እንዲያስቀምጡት አበረታታቸው።

መዝሙር 114 እና የመደምደሚያ ጸሎት

ሰኔ 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 172

5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

10 ደቂቃ፦ “‘የመቄዶንያ’ ጥሪ።” የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የምሥራቹ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉባቸው ቦታዎች በመዛወር አገልግሎታቸውን የማስፋት አጋጣሚ ያላቸውን ወንድሞች ልብ ለማነሳሳት ይጥራል።

15 ደቂቃ፦ “በወዳጅነት ስሜት የሚደረጉ ውይይቶች የሰዎችን ልብ ሊነኩ ይችላሉ።” ጥያቄና መልስ። አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች በወዳጅነት ስሜት ውይይት ማድረግ እንዴት ጥሩ ምላሽ እንደሚያስገኝ የሚያሳዩ አበረታች ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ።

15 ደቂቃ፦ “ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራውን እውቀት ማሠራጨት።” (አንቀጽ 6-7) የሰዎችን ፍላጎት በመኮትኮት፣ ጥናት በማስጀመር፣ ተመልሶ ለመሄድ ቁርጥ ያለ ቀጠሮ በመያዝ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ግብ ማውጣትን ጎላ አድርገህ ግለጽ። በአንቀጽ 6 እና 7 ላይ የተጠቀሱትን አቀራረቦች ባጭሩ ከከለስክ በኋላ በእነዚህ መግቢያዎች ተጠቅሞ ጥናት እንዴት መጀመር እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በጥር 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 13 ላይ የሚገኘውን አንቀጽ 17 አንብብ።

መዝሙር 204 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 6

7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።

20 ደቂቃ፦ “ከፊታችን ያለውን ሕይወት እየተመለከትን መጽናት።” አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 14 ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በመደምደሚያው ላይ የክለሳ ጥያቄዎችን አቅርብ። ሁሉም የዚህ መጽሐፍ የግል ቅጂ እንዲኖራቸው አበረታታ።

18 ደቂቃ፦ “እንደገና አገልግሎት እንዲጀምሩ እርዷቸው።” በውይይት መልክ በአንድ ሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። አገልግሎት ያቆሙትን ለማበረታታት በነሐሴ 1, 1992 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን “ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” የሚለውን ርዕስ እንዲጠቀሙ አበረታታ። በዚያ ውስጥ ካሉት ዋና ዋና ነጥቦችም ጥቂቶቹን ጥቀስ።

መዝሙር 174 እና የመደምደሚያ ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ