የሐምሌ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ሐምሌ 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 155
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የአገሪቱንና የጉባኤውን የሚያዝያ ወር የአገልግሎት ሪፖርት በሚመለከት አንዳንድ ሐሳቦችን አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ “ዕለት ዕለት ስእለታችንን መፈጸም።” ጥያቄና መልስ። ስእለት ከበድ ተደርጎ የሚታይ ጉዳይ እንደሆነ ለማሳየት ማስተዋል ጥራዝ 2 ገጽ 1162 አንቀጽ 6-7 ላይ ያለውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።
22 ደቂቃ፦ “ለሌሎች ልባዊ አሳቢነት በማሳየት ይሖዋን ምሰል።” (አንቀጽ 1-3) የክፍሉን ጭብጥ ለማዳበር በመጀመሪያው አንቀጽ ተጠቀም። በአሁኑ ጊዜ በጉባኤያችሁ ከሚገኙት ብሮሹሮች መካከል በክልላችሁ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ፍላጎት ሊቀሰቅሱ የሚችሉትን ምረጥ። ከዚያም አንቀጽ 2-3 ላይ ያለውን ሐሳብ ብቻ ከልስና አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? በተባለው ብሮሹር ውይይት ለመጀመርም ሆነ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ እንዴት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ። አስፋፊዎች ለክልላቸው ተስማሚ የሆነ ሌላ ብሮሹር ለመጠቀም የራሳቸውን መግቢያ እንዴት ሊያዘጋጁ እንደሚችሉ አሳይ። በተጨማሪም “አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ንቁ ሁን” የሚለውን ክፍል ተወያዩበት።
መዝሙር 85 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 114
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ “ለሌሎች ልባዊ አሳቢነት በማሳየት ይሖዋን ምሰል።” (አንቀጽ 4-5) አንቀጽ 4-5ንና የምትወዱት ሰው ሲሞት የተሰኘው ብሮሹር ያካተታቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ተወያዩ። ከዚያም ውይይት ለመጀመርና ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ የተሰጡትን አቀራረቦች በሠርቶ ማሳያዎች መልክ አቅርብ። አስፋፊዎች የብዙ ሰዎችን ዓይን ለመንፈሳዊ እውነቶች ለመክፈት ሊያገለግሉ የሚችሉትን መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሙታን መናፍስት እና ሥላሴ የተሰኙትን ብሮሹሮች እንዲያበረክቱ ለማበረታታት በቀረው ጊዜ ተጠቀም።
20 ደቂቃ፦ “በአቅኚነት አገልግሎት ተጨማሪ ወንድሞች ያስፈልጋሉ።” ጥያቄና መልስ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በመስከረም 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-31 ላይ አቅኚዎች የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ ማግኘት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ የሚገልጹትን ሐሳቦች ከልስ። በተጨማሪም ባለፈው ወር በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣው “የመቄዶንያ ጥሪ” የተባለው ርዕስ ያካተታቸውን ዋና ዋና ነጥቦች አክለህ አቅርብ።
መዝሙር 143 እና የመደምደሚያ ጸሎት
ሐምሌ 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ “በምሽት ምሥክርነት ለመካፈል ሞክረሃል?” አድማጮች ተሳትፎ የሚያደርጉበት ንግግርና ጥቂት ቃለ ምልልሶች። በክልሉ ውስጥ ከሥራ ሰዓት በኋላ አገልግሎት በሚከናወንበት ወቅት ምን ነገሮች እንደተስተዋሉ ግለጽ። በምሽት ምሥክርነት መልካም ውጤቶች እንደተገኙ የሚያሳዩ ተሞክሮዎች ጨምረህ አቅርብ። በሳምንቱ ውስጥ በጉባኤያችሁ ያሉትን የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች ፕሮግራም ዘርዝር።
15 ደቂቃ፦ “ለሌሎች ልባዊ አሳቢነት በማሳየት ይሖዋን ምሰል።” (አንቀጽ 6-8) ሁሉም አስፋፊዎች ብሮሹር ላበረከቱላቸው ሰዎች ሳይዘገዩ ተመላልሶ መጠየቅ እንዲያደርጉ ለማበረታታት የክፍሉን የመጨረሻ አንቀጽ ተጠቀም። አንቀጽ 6-7ን በመጠቀም ሰዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በምታነጋግሩበት ወቅት በደስታ ኑር! ወይም የሕይወት ዓላማ (የእንግሊዝኛ) የተባሉትን ብሮሹሮች እንዴት ማበርከት እንደሚቻልና በተመላልሶ መጠየቅ ጊዜ እውቀት ወይም ለዘላለም መኖር በተሰኙት መጽሐፎች የመጀመሪያ ምዕራፍ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ። አስፋፊዎች በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ያሉትን አቀራረቦች በመከተል ሌሎች ብሮሹሮችን ለማበርከት የራሳቸውን መግቢያ ማዘጋጀት እንደሚችሉ አስታውሳቸው።
መዝሙር 6 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 204
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከቤት ወደ ቤት ለሚደረገው አገልግሎት ሊጠቅሙ የሚችሉ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ፍሬ ሐሳቦችን በማጉላት በቅርብ ጊዜ የወጡ መጽሔቶችን በአጭሩ ከልስ።
15 ደቂቃ፦ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ግብ ላይ ለመድረስ መጣጣር። በታኅሣሥ 15, 1988 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ገጽ 25-27 ላይ የተመሠረተ በአንድ ሽማግሌና አንድ ወይም ሁለት በአሥራዎቹ ዕድሜ በሚገኙ ወጣቶች መካከል የሚደረግ ውይይት። ወጣቶቹ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ ምን ዓይነት ግብ ላይ ለመድረስ እንደሚጣጣሩ ለመወሰን ይሞክራሉ። ሥጋዊ ሥራ የሚያስገኛቸውን ቁሳዊ ጥቅሞች የማግኘት ፍላጎት አሳይተዋል። ሽማግሌው ወደ አቅኚነት አገልግሎት ለመግባት መጣጣር የተሻለ የሆነው ለምን እንደሆነ ያብራራል። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙት ወጣቶች በዚህ ቢስማሙም አቅኚ ሆነው ቁሳዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት ስለመቻላቸው ይጠራጠራሉ። ሽማግሌው የአቅኚነት አገልግሎት ለብዙዎች ደስታ ያመጣ ምክንያታዊና ሊደረስበት የሚችል ግብ እንደሆነ የሚያሳዩ ተሞክሮዎች ከመጠበቂያ ግንቡ ያካፍላቸዋል። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙት ወጣቶች ሽማግሌው ላካፈላቸው ሐሳቦች ያላቸውን አድናቆትና በመንግሥቱ አገልግሎት የተሟላ ተሳትፎ የማድረግ ግብ ላይ ለመድረስ በጥሞና እንደሚያስቡበት መወሰናቸውን ከገለጹ በኋላ ውይይቱ ያበቃል።
20 ደቂቃ፦ “እውቀት በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት ደቀ መዛሙርት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?” በሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ አባሪ ሆኖ በወጣው ክፍል በአንቀጽ 12-16 ላይ የተመሠረተ ንግግር። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሲደረግ የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎችን አክል። የመጀመሪያው ሠርቶ ማሳያ በመጽሐፉ ውስጥ ለሚገኙት ጥያቄዎች በቀጥታ መልስ በሚሆኑ ቃላት እና ሐረጎች ሥር በማስመር ትምህርቱን የሚዘጋጅበትን መንገድ ተማሪውን እንዴት ማሠልጠን እንደሚቻል ያሳያል። ሁለተኛው ሠርቶ ማሳያ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪው በሕዝባዊ ስብሰባና በመጠበቂያ ግንብ ጥናት ላይ እንዲገኝ ለማበረታታት ምን መናገር እንደምትችል ያሳያል።
መዝሙር 191 እና የመደምደሚያ ጸሎት
ሐምሌ 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 212
7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማግኘት የሚረዱት ነገሮች ምንድን ናቸው? አንድ ሽማግሌ ከሁለት ወይም ከሦስት የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች ጋር የሚደረገውን ውይይት ይመራል። ጥናት ለመጀመር የሚያስችሉ በይበልጥ ውጤታማ የሆኑ መንገዶችን ይከልሳሉ። (1) የይሖዋን እርዳታ ለማግኘት ጸልዩ። (2) ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ለማግኘት ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ሥራ ዘወትር ተካፈሉ። (3) ፍላጎት ያሳዩትን በማስታወሻ ያዙና ሳትዘገዩ ተመላልሶ መጠየቅ አድርጉ። (4) ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ሲገኙ ጥናት እንዲጀምሩ ጋብዟቸው። (በየካቲት 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20 ላይ ያለውን “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመር” የሚለውን ንዑስ ርዕስ ተመልከት።) (5) በነሐሴ 1, 1984 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ገጽ 13-17 ላይ የተዘረዘሩትን አራት ነጥቦች በመጠቀም በማስተማር ችሎታህ ላይ እምነት አዳብር። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በመስከረም 1994 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 ላይ “ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን መምራት እንችላለንን?” በሚለው ርዕስ ሥር አንቀጽ 5 እና 6ን ካነበባችሁ በኋላ ተወያዩበት። በትራክቶች፣ በደስታ ኑር! እና አምላክ ያስባልን? በመሳሰሉት ብሮሹሮች በመጠቀም ጥናት ማስጀመር የሚቻልባቸውን አጋጣሚዎች ጎላ አድርገህ ግለጽ።
18 ደቂቃ፦ “በአደባባይና ከቤት ወደ ቤት አስተምሩ።” ከቤት ወደ ቤት ለሚደረገው አገልግሎት ጥሩ መንፈስ ያለው ወንድም ከጥር 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ላይ ገጽ 10-15 ያለውን ሐሳብ ይከልሳል። መጽሐፍ ቅዱስን በብዛት መጠቀም ደስታችንና እርካታችን ከፍ እንዲል አስተዋጽኦ የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ። በጸሎትና በይሖዋ በመታመን ፍርሃትን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል አብራራ። (2 ጢሞ. 1:7) ከቤት ወደ ቤት በሚካሄደው ሥራ በመካፈል ደስታ ካገኙ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ጋር ቃለ ምልልስ በማድረግ ደምድም።
መዝሙር 180 እና የመደምደሚያ ጸሎት