ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች። በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት ፍላጎት ካሳዩ ኮንትራት እንዲገቡ መጋበዝ ይቻላል። ኅዳር፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ በመያዝ መጽሐፉ ለተበረከተላቸው ሰዎች ሁሉ ክትትል ለማድረግ ልዩ ጥረት ይደረጋል። ታኅሣሥ፦ በዚህ ወር የሚበረከተው ጽሑፍ በኅዳር የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ይገለጻል። ጥር፦ በጉባኤው ውስጥ ያለ ከ1984 በፊት የታተመ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ። እነዚህ መጻሕፍት የሌሏቸው ጉባኤዎች ወጣትነትህን ከሁሉ በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት እና የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው! የተባሉትን መጻሕፍት ማበርከት ይችላሉ።
◼ የዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ገጽ “የ1997 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ሲሆን በ1997 ዓመቱን ሙሉ ልንጠቀምበት እንድንችል በጥሩ ሁኔታ ልንይዘው ይገባል።