የጥቅምት የአገልግሎት ስብሰባዎች
ማሳሰቢያ፦ ከዚህ በታች በየሳምንቱ የሚደረጉትን የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራሞች ታገኛላችሁ። ጉባኤዎች “የአምላካዊ ሰላም መልእክተኞች” በተባለው የአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሲሉ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያዎችን ማድረግ ይችላሉ። ስለዚህ አንዳንድ ክፍሎችን ሊተዉ ወይም ሊያሳጥሩ ይችላሉ። በአውራጃ ስብሰባው ላይ በእያንዳንዱ ዕለት የቀረቡትን ክፍሎች መከለስ እንዲቻል በዋና ዋናዎቹ ነጥቦች ላይ ማተኮር የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሁለት ወይም ሦስት ወንድሞች አስቀድመው መመደብ አለባቸው። ይህ ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት ክለሳ የጉባኤው አባላት በግልም ይሁን በአገልግሎት ሊሠሩባቸው የሚገቡትን ቁልፍ ነጥቦች እንዲያስታውሱ ይረዳቸዋል። አድማጮች የሚያደርጉት ተሳትፎና የሚቀርቡት ተሞክሮዎች አጭርና የሚፈለገውን ነጥብ ብቻ የሚገልጹ መሆን ይኖርባቸዋል።
ጥቅምት 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎቸ። በአገሪቱና በጉባኤው የሐምሌ ወር ሪፖርት ላይ ሐሳብ ስጥ። አንዳንድ አስፈላጊ የሆኑ የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎችን ተናገር።
15 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ወይም ሌላ ብቃት ያለው ሽማግሌ ከአድማጮች ጋር በመወያየት ያቀርበዋል።
20 ደቂቃ፦ “መጽሔት ለማበርከት የሚያስችልህን የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።” (አንቀጽ 1-7) ከ1-4 ባሉት አንቀጾች ላይ ጥያቄ ካቀረብክ በኋላ በአንቀጽ 5-7 ላይ የተሰጡትን ሐሳቦች በመጠቀም በቅርቡ የወጡ መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ወይም ሦስት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ። በመጠበቂያ ግንብ 5-108 ገጽ 6, 7 አንቀጽ 8-9 ላይ ያለውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 222 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 143
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ “የተሻለ ነገር እንደሚመጣ የሚያበስረውን ምሥራች ማወጅ።” ጥያቄና መልስ። በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ላይ የወጡትን ታሪካዊ ርዕሶች ጠቃቅስ።— መጠበቂያ ግንብ 5-108 ገጽ 3 እና 4ን ተመልከት።
20 ደቂቃ፦ “መጽሔት ለማበርከት የሚያስችልህን የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።” (አንቀጽ 8-11) ጥያቄና መልስ። በጥር 1, 1994 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 24-25 አንቀጽ 18-21 ላይ ስለቀረቡት አራት ነጥቦች ተጨማሪ ሐሳብ ስጥ። በጥቅምት ወር የወጡትን መጽሔቶች በመጠቀም አቀራረባችንን እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል አሳይ:- (1) በአገልግሎት ክልልህ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ስሜት ሊማርክ የሚችል አንድ ርዕስ ምረጥ፣ (2) አንድ አስደሳች ነጥብ ምረጥ፣ (3) በነጥቡ ላይ እንዲያተኩሩ ሊያደርግ የሚችል ጥያቄ አዘጋጅ፣ (4) አጋጣሚውን የምታገኝ ከሆነ የምታነበውን ጥቅስ ምረጥ እንዲሁም (5) በመግቢያህ ላይ የምትናገራቸውን ቃላትና የቤቱ ባለቤት ጽሑፉን እንዲወስድ ለማበረታታት እንድትችል ስለ መጽሔቱ የምትናገረውን ነገር ተዘጋጅ። ብቃት ያላቸው ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። በተጨማሪም አንድ ልጅ መጽሔት ለማበርከት የሚያስችል ቀላል አቀራረብ እንዲያሳይ አድርግ።
መዝሙር 204 እና የመደምደሚያ ጸሎት
ጥቅምት 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 114
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የመጽሔት ደንበኞች ማግኘት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ግለጽ:- (1) መጽሔት ያበረከትክላቸውን ሰዎችና ያስተዋወቅኸውን ርዕስ መዝግብ፣ (2) የሚቀጥለውን እትም ይዘህ ለመሄድ ዝግጅት አድርግ፤ ከዚያም (3) በሳምንታዊ የአገልግሎት ፕሮግራምህ መሀል እነዚህን ሰዎች የምታነጋግርበት የተወሰነ ጊዜ መድብ። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ስታገኝ ኮንትራት እንዲገቡ ጋብዛቸው፤ በተጨማሪም እያንዳንዱ የመጽሔት ደንበኛ ጋር ተመልሰህ ስትሄድ ተመላልሶ መጠየቅ መመዝገብህን አትርሳ።
8 ደቂቃ፦ “የአገልግሎት ክልልህን አጣርተህ ሸፍን።” ከክፍሉ በተጨማሪ ጉባኤው የንግድ ክልሎችን ለመሥራት ስላደረገው ዝግጅት ግለጽ። በቅርቡ በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ ከቤት ወደ ቤት በመሄድ የተገኙ አንዳንድ ውጤቶችን ጥቀስ። ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች በጥሩ ሁኔታ በማስታዎሻ መመዝገብና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ በመያዝ ወዲያውኑ ተመልሶ መጠየቅ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉንም አሳስባቸው። አድማጮች በአገልግሎት ክልላቸው ውስጥ የሚገኙትን ሱቆች ሲሸፍኑ ያገኙትን የሚያበረታታ ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዛቸው።
25 ደቂቃ፦ ከአውራጃ ስብሰባ የተገኙ ቁልፍ ነጥቦችን ከልሱ፤ በግለሰብ ደረጃ ሐሳቦችን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ጠበቅ አድርጋችሁ ግለጹ።
መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት
ጥቅምት 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 42
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ረዳት አቅኚ ሆነው ስለ ማገልገል እንዲያስቡበት ሁሉንም አበረታታቸው። የጥቅምትን የመስክ አገልግሎት ሪፖርት በዚህ ሳምንት መጨረሻ መመለስ እንዳለባቸው ሁሉንም አሳስብ።
20 ደቂቃ፦ “ዘመኑን መዋጀት የሚቻለው እንዴት ነው?” ጥያቄና መልስ። መጠበቂያ ግንብ 23-110 ገጽ 16-17 አንቀጽ 7-11 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ አክለህ አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ በኅዳር ወር የሚበረከተው ጽሑፍ ምን እንደሆነ ግለጽ። በኅዳር ወር ለዘላለም መኖር የተባለው መጽሐፍ ይበረከታል፤ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ በመያዝ የተበረከተላቸውን ሰዎች ሁሉ ተከታትሎ ለመርዳት ልዩ ጥረት ይደረጋል። ብቃት ያላቸው ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች መጽሐፉ ያለውን ጠቀሜታና እንዴት በመጽሐፉ መጠቀም እንደሚቻል ይወያያሉ። በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኘው ትምህርት በየትኛውም የኑሮ ዘርፍ ያሉትን ሰዎች ሁሉ የሚነካ ነው። አዲሶች ከመጠመቃቸው በፊት ሊያውቋቸው የሚገቡአቸውን ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳዮችና መሠረታዊ ሥርዓቶች ይዳስሳል። ጥናቱን ካላጓተትነው ተማሪው ፈጣን እድገት ማድረግ ይችላል። ቀጥተኛ አቀራረብ በመጠቀም እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል ከተናገርክ በኋላ ሠርቶ ማሣያ አቅርብ። በገጽ 12 እና 13 ላይ የሚገኘውን ሥዕል ካሳየኸውና አንቀጽ 12ን ካነበብክለት በኋላ ሰዎችን እንዴት እንደምናስጠና ግለጽ፤ በምዕራፍ አንድ ውስጥ ያሉትን የመጀመሪያ አምስት አንቀጾች ባጭሩ ተወያዩባቸው፤ ሌላ ጊዜ ተመልሰህ ሄደህ ውይይቱን ለመቀጠልና የዘላለም ሕይወት ሕልም ነውን? ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ያዝ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት የሚያስገኘውን ደስታ ጎላ አድርገህ ግለጽ።
መዝሙር 187 እና የመደምደሚያ ጸሎት።