የታኅሣሥ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ታኅሣሥ 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 174
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በሚቀጥለው ሳምንት ለሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ስለ ሠርግ የሚናገረውን የኅዳር የመንግሥት አገልግሎታችን መጽሔት አባሪ ገጽ ይዘው እንዲመጡ ሁሉንም አስታውሳቸው።
15 ደቂቃ፦ “ለመልእክታችን እነማን ጆሮ ይሰጣሉ?” ጥያቄና መልስ። መልእክታችን ማራኪ የሆነበትን ምክንያት የሚገልጸውን ከመጋቢት 22, 1987 የእንግሊዝኛ ንቁ! ገጽ 5 ላይ የተወሰደውን ሐሳብ አክለህ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “የአምላክ ቃል መመሪያ ይሰጣል።” አንቀጽ 1ና 2 እንደ መግቢያ አድርገህ ተጠቀም። (ማመራመር በተባለው መጽሐፍ በገጽ 57-58 “መጽሐፍ ቅዱስን እንድንመረምር የሚያደርጉን ምክንያቶች” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያሉትን አራት ነጥቦች በአጭሩ ከልስ።) ብቃት ያላቸው አስፋፊዎች የቀረቡትን ሁለት መግቢያዎች ተጠቅመው ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ:- (1) የቀረቡት ጥያቄዎች ፍላጎት ለማነሳሳት የሚረዱት እንዴት እንደሆነ (2) የተጠቀሱት ጥቅሶች ውይይት እየተደረገበት ካለው ርዕስ ጋር የሚስማሙት እንዴት እንደሆነ (3) ለመጀመሪያ ጊዜ ውይይት ከተደረገ በኋላ የተከናወነው ተመላልሶ መጠየቅ ትክክለኛ ቅደም ተከተሉን የጠበቀው እንዴት እንደሆነ እና (4) ጥናት ለማስጀመር የተደረገው ግብዣ እንዴት እንደቀረበ ይግለጹ።
መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 155
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ አረጋውያንን በአገልግሎት እንዲካፈሉ እርዷቸው። ብዙዎቹ በእድሜ የገፉ ታማኝ አስፋፊዎች ከጉባኤው ጋር ሆነው በስብከቱ ሥራ ለመካፈል ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ቢሆንም በእድሜያቸውና በጤና መታወክ ምክንያት እንዲህ ለማድረግ አቅም ያንሳቸዋል። ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መንገዶች ከሌሎች ጋር በአገልግሎት አብረው እንዲካፈሉ ለማድረግ አሳቢነት ልናሳይ እንችላለን። ትራንስፖርት እንደምታቀርብላቸው ንገራቸው። ብዙ ደረጃ ወደሌላቸው ቤቶች ሄደው እንዲሠሩ ዝግጅት አድርግ። ተመላልሶ መጠየቅ ወደሚያደርጉላቸው ሰዎች ልትወስዳቸው እንደምትችል ንገራቸው። ሲደክማቸው ወደ ቤት እንደምትመልሳቸው አስቀድመህ ንገራቸው። በእድሜ የገፉ ሰዎች ለሚደረግላቸው እርዳታ ሁሉ አመስጋኝ ናቸው። በጉባኤያችሁ ተመሳሳይ የሆነ አሳቢነት የምታሳዩባቸውን ሌሎች መንገዶች ጥቀስ። በየካቲት 1, 1986 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ በገጽ 28ና 29 ላይ የሚገኘውን “አረጋውያንን እናደንቃቸዋለን!” ከሚለው ርዕሰ ትምህርት ዋና ዋና ነጥቦችን ከልስ።
20 ደቂቃ፦ “ይሖዋን የሚያስከብር ሠርግ።” ከ1-6 ያሉትን አንቀጾች እያነበብክ ከአድማጮች ጋር ተወያዩባቸው። ጥያቄዎቹ:- 1. ሠርግን በተመለከተ ጥበብ የተሞላባቸው ምክሮች ማግኘት የምንችለው ከየትኞቹ ጽሑፎች ነው? 2. የሠርጋችን ዕለት በአካባቢው በተለመዱት የሠርግ ወራት የግድ መደረግ የማይኖርባቸው ለምንድን ነው? 3. (ሀ) ማዘጋጃ ቤት በሚደረገው ሥርዓትና የጋብቻ ንግግር በሚሰጥበት ዕለት መካከል የብዙ ቀን ልዩነት ማድረግ ጥበብ ያልሆነው ለምንድን ነው? (ለ) የጋብቻ ንግግር የሚደረግበትን ጊዜ ለመወሰን ቀደም ተብሎ መደረግ የሚኖርባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? (ሐ) የጋብቻው ንግግር የሚፈጀውን ጊዜና የሚሰጥበትን ሰዓት አስመልክቶ ማስታወስ የሚኖርብን ነገር ምንድን ነው? (መ) ተናጋሪው ሙሽራውንና ሙሽራይቱን አስቀድሞ አግኝቶ ማነጋገር የሚኖርበት በየትኞቹ ምክንያቶች የተነሳ ነው? 4. ጊዜ መጠበቅን፣ ፎቶ ማንሳትንና ሥርዓታማነትን በተመለከተ “የዓለም ክፍል” አለመሆናችንን የሚያሳዩት የትኞቹ ሐሳቦች ናቸው? 5. ተጋቢዎቹ ድግስ ማዘጋጀት የሚፈልጉ ከሆነ ድግሱ ዓለማዊ ሰዎች ከሚያዘጋጁት ድግስ የተለየ መሆን የሚኖርበት በምን መንገዶች ነው? 6. (ሀ) በድግስ ቦታዎች ላይ ሥርዓት እንዲጠበቅና ጨዋነት እንዲሰፍን ለማድረግ የሚረዳው ምንድን ነው? (ለ) እንግዶች በሚጋበዙበት ጊዜ አንድ ክርስቲያን ቅድሚያ የሚሰጠው ለእነማን ነው? በመደምደሚያህ ላይ የቀሩት አንቀጾች በሚቀጥለው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ እንደሚሸፈኑ እባክህ ጉባኤውን አሳስብ።
መዝሙር 117 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 215
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በበዓል ሰሞን ለሚቀርቡልን ሰላምታዎች በጥበብ ምላሽ መስጠት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ አንዳንድ ሐሳቦችን ተናገር።
15 ደቂቃ፦ “ራሳችንን በፈቃደኝነት ማቅረብ።” ጥያቄና መልስ። ግንቦት 1, 1984 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22 ላይ ካሉት ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “ይሖዋን የሚያስከብር ሠርግ።” አንቀጽ ከ7-13። የመጀመሪያውን ክፍል አስመልክቶ አጭር ክለሳ ካደረግህ በኋላ አንቀጾቹን እያነበብክ በሚከተሉት ጥያቄዎች ተጠቀም:- 7. (ሀ) “የግብዣ ኃላፊ” መመደብ ተገቢ የሚሆነው ለምንድን ነው? (ለ) ስጦታዎችን፣ ሙዚቃን፣ ውዝዋዜንና የአልኮል መጠጥን በተመለከተ ምን ምክር ተሰጥቷል? 8, 9. (ሀ) አስተዋይ የሆኑ ተጋቢዎች ለሠርግ ብለው ዕዳ ከመግባት የሚርቁት ለምንድን ነው? (ለ) ምክንያታዊነትና ልከኝነት የሠርግ ልብሶችን በመምረጥ በኩል እርዳታ ሊያበረክቱ የሚችሉት እንዴት ነው? 10. የሠርግ ግብዣን በተመለከተ በአእምሮ ሊያዙ የሚገባቸው ተግባራዊ ምክሮችና ሥርዓቶች ምንድን ናቸው? 11. ክርስቲያኖች የሚርቁት ከምን ዓይነት የይታይልኝ ድርጊቶች ነው? 12. (ሀ) በዓለማዊ ወዳጆችና በሩቅ ዘመዶች ሠርግ ላይ መገኘት አለመገኘታችንን ለመወሰን የሚረዱን የትኞቹ ቅዱስ ጽሑፋዊ ጥቅሶች ናቸው? (ለ) በሠርጋቸው ግብዣ ላይ መገኘት ሳያስፈልገን አዲስ ለተጋቡ ባልና ሚስት መልካም ምኞታችንን መግለጽ የምንችለው እንዴት ነው? 13. ከሠርግ ጋር የተያያዙ ነገሮችንም ጨምሮ ከዓለም ፍጹም የተለዩ ሆኖ መኖር ምን ጥቅሞች ያስገኛል?
መዝሙር 136 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 23 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በዚህ ሳምንት ለሚደረገው አገልግሎት ሊጠቅሙ የሚችሉ አንዳንድ መነጋገሪያ ነጥቦችን ወቅታዊ ከሆኑት መጽሔቶች ላይ ጥቀስ።
15 ደቂቃ፦ “አምላክ በሚሰጠው ጭማሪ መደሰት።” በሽማግሌ የሚቀርብ ሞቅ ያለ ንግግር። በቅርቡ ከወጡት የዓመት መጽሐፎች ውስጥ ታሪካቸው በሰፊው ከተገለጹት አገሮች ተሞክሮዎችንና ጭማሪ እንዳለ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን አቅርብ። በሞዛምቢክ የሚገኙ ወንድሞች ስደት ሲደርስባቸው እንዴት እንደዳኑ ከገለጽክ በኋላ የ1996 ዓመት መጽሐፍ ከገጽ 172-185 ላይ የሚገኙትን ጎላ ያሉ አስደሳች ነጥቦች እንድትጠቅስ ሐሳብ እናቀርባለን። ይህን ክፍል የሚያቀርበው ወንድም እንግሊዝኛ ማንበብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል።
20 ደቂቃ፦ “በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመዝገብ።” በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። በጉባኤው ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ክፍል ለማቅረብ የተመዘገቡት ምን ያህል እንደሆኑ ግለጽና ሁሉም እንዲመዘገቡ አበረታታ። ‘በ1997 ቲኦክራሲያዊው የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም’ ላይ ክፍል ለሚወስዱ ተማሪዎች የተሰጠውን መመሪያ ከልስ።
መዝሙር 53 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 136
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ጉባኤያችሁ በአዲሱ ዓመት የስብሰባ ሰዓት የሚለውጥ ከሆነ አስፈላጊውን ማስተካከያ እንዲያደርጉና በአዲሱ የስብሰባ ሰዓት ከጉባኤው ጋር አዘውትረው እንዲሰበሰቡ ሁሉንም በደግነት አበረታታ። ሁሉም በመጋቢት ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል እንዲችሉ አስቀድመው ዝግጅት አንዲያደርጉ አበረታታ። ወሩ አምስት ቅዳሜና እሁድ ያለው የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው በዚሁ ወር መሆኑ ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል የሚያበረታታ ነው። ቀደም ሲል ምንም ዓይነት ትኩረት ያልተሰጠውን የአገልግሎት ክልል ለመሸፈን ይህ ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል።
20 ደቂቃ፦ “አስፈላጊ በሆነ ወቅት የተገኘ እርዳታ።” ጥያቄና መልስ። ከእያንዳንዱ አዲስ ጽሑፍ ጠቃሚ የሆኑ ዋና ዋና ሐሳቦችን ግለጽ።
15 ደቂቃ፦ በጥር የሚበረከተው ጽሑፍ ምን እንደሆነ ግለጽ። ከ1984 በፊት የታተሙ ባለ 192 ገጽ ጽሑፎች ማበርከት ይቻላል። በጉባኤ ውስጥ ኢተርናል ፐርፐዝ፣ ታላቁ አስተማሪ፣ ሆሊ ስፒሪት እና እውነት የተሰኙት መጻሕፍት ካሉ እነዚህን ጽሑፎች ለማበርክት ቁርጥ ያለ እርምጃ መውሰድ ይገባል። እነዚህ ጽሑፎች በጉባኤያችሁ ከሌሉ በሕይወት ተርፎ ወደ አዲስ ምድር መግባት የተሰኘውን መጽሐፍ አበርክቱ። የትኛው ጽሑፍ በጉባኤያችሁ እንዳለ ግለጽ። በአገልግሎት ክልላችሁ ውጤት ሊያስገኙ የሚችሉትን ሁለት ወይም ሦስት መጻሕፍት ምረጥ። ማመራመር ከተሰኘው መጽሐፍ ከገጽ 9-14 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጠቀም ለእያንዳንዱ መጽሐፍ ተስማሚ የሆኑ መግቢያዎችን በአጭሩ አቅርብ። አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ።
መዝሙር 211