የመጋቢት ወር የአገልግሎት ስብሰባዎች
መጋቢት 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 53
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። መጋቢት 23 ለሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች መጋበዝ እንዲጀምሩ አበረታታ። የመታሰቢያውን በዓል የመጋበዣ ወረቀት አንድ ቅጂ አሳያቸውና የተወሰኑ ቅጂዎች ወስደው በዚህ ሳምንት ማሠራጨት እንዲጀምሩ አበረታታቸው።
10 ደቂቃ:- በመጋቢት እና በሚያዝያ የሚበረከተው ጽሑፍ ምን እንደሆነ ግለጽ። የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎችን አበርክቱ። በጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 አንቀጽ 3, 4 እና 8 ላይ መጽሔት ለማስተዋወቅ የሚረዱ መግቢያዎችን እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል የተሰጡትን ነጥቦች በአጭሩ ጥቀስ። ሁለት አስፋፊዎች አንድ ወይም ሁለት አጫጭር አቀራረቦችን እንዲያሳዩ አድርግ። አስፋፊዎች መጽሔት የወሰዱትን ሰዎች መመዝገብና በመጽሔት ደንበኞቻቸው ዝርዝር ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል።
25 ደቂቃ:- “ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ደፋሮች ሁኑ።” (አንቀጽ 1-17) ጥያቄና መልስ። አንቀጽ 16ን በአጭሩ በሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
መዝሙር 204 እና የመደምደሚያ ጸሎት
መጋቢት 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 79
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ሁሉም ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር በተባለው ቡክሌት ላይ የሚገኘውንና ከመጋቢት 18-23 ድረስ የሚደረገውን የመታሰቢያውን በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ተከታትለው ማንበባቸውን እንዳይዘነጉ አስታውሳቸው።
20 ደቂቃ:- “‘የምታመሰግኑ ሁኑ።’” ጥያቄና መልስ። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን፣ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች፣ የቤተሰብ አባሎቻቸውን እንዲሁም ከጉባኤው ጋር ያላቸውን ቅርርብ የቀነሱ ወንድሞችና እህቶች ሁሉ በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ ሁሉም ልባዊ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል። በ13-109 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 9 አንቀጽ 16-17 ላይ የተመሠረተ ተጨማሪ ሐሳብ ስጥ። በሚያዝያና በግንቦት ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ ረዳት አቅኚ ሆነው እንዲያገለግሉ አበረታታ።
15 ደቂቃ:- “የሰይጣንን ሽንገላዎች ጸንታችሁ ተቃወሙ።” ብቃት ባለው ሽማግሌ በግለት የሚቀርብ ንግግር፤ በየመሃሉ አንዳንድ ጥያቄዎችን ለአድማጮች ያቀርባል። የክፉው ዓለም ሥርዓት ቀኖች እየተሟጠጡ ባሉበት በአሁኑ ጊዜ ሰይጣንና አጋንንቱ የአምላክ አገልጋዮች ተስፋ እንዲቆርጡ፣ እንዲዘናጉ ወይም እንዲደናቀፉ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ አስረዳ። በእኛ ላይ ጫና ለመፍጠር በታላቂቱ ባቢሎን፣ በሌሎች ክፉ ሰዎችና በሁኔታዎች ይጠቀማሉ። ከዚያም ሮሜ 12:21ን ጠቅሰህ 17-109 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-23 ላይ የወጣውን ትምህርት አያይዘህ አቅርብ። ክፉውን መቋቋም ይችሉ ዘንድ ሁሉም ጥሩ የማጥናት፣ የጸሎት፣ በስብሰባዎች ላይ የመገኘትና የአገልግሎት ልማድ እንዲያዳብሩ አሳስባቸው።
መዝሙር 191 እና የመደምደሚያ ጸሎት
መጋቢት 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 8
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ክፍል ከከለስክ በኋላ ጉባኤው ለመታሰቢያው በዓል ያደረጋቸውን ዝግጅቶች ግለጽ። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችና ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ለማድረግ ሁሉም የመጨረሻ ዕቅድ ሊያወጡ ይገባል።
15 ደቂቃ:- “አቀራረብህን ሕያው ለማድረግ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ተጠቀም።” ማመራመር የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 10-11ን በመጥቀስ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በመጠቀም ውይይት መክፈት የሚቻልበትን መንገድ አስረዳ። ምሳሌዎች:- በትምህርት ቤት በልጆች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ወይም ዘረፋ፤ ቦምብ ሊፈነዳ ይችላል የሚል ስጋት፤ የአውሮፕላን ጠለፋ፤ የስደተኞች ቁጥር መጨመር፤ ጦርነትና ጎሰኛነት (ሩዋንዳ)፤ ለማኞችና የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ ልጆች ቁጥር መጨመር፤ የመጠጥ ውኃ ወይም የምግብ እጥረት፤ በአካባቢው የተከሰተ ሞትና በሽታ ወዘተ . . .። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ከሐምሌ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን “አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ንቁ ሁን” ከሚለው ርዕስ በተለይ አንቀጽ 3 እና 4ን ጥቀስ።
15 ደቂቃ:- “የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።” በግንቦት 15, 1992 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21 እስከ 23 ላይ የተመሠረተ ለተግባር የሚያንቀሳቅስ ንግግር። ትምህርቱን ወጣቶች ከሚገጥማቸው ፈታኝ ሁኔታ፣ ከፍቅረ ነዋይ ወጥመድና ከኩራት አደገኛነት ጋር አያይዘህ አቅርብ። ሁሉም በግ መሰል ሰዎችን ለማግኘት በሚያደርጉት ፍለጋ ጊዜያቸውን በአግባቡ ተጠቅመው የተቻላቸውን ያክል ብዙ ሰዎች በማነጋገር ትርጉም ያለው አገልግሎት ለማከናወን ይችሉ ዘንድ የጸና ግብና ፕሮግራም እንዲያወጡ አበረታታቸው።
መዝሙር 123 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 67
18 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎቸ። በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ለመሆን የሚፈልጉ አሁንም ማመልከቻውን መሙላት እንደሚችሉ ግለጽ። በዚህ ወር ለመስክ ስምሪት ስብሰባ በጉባኤው ስለተደረጉ ተጨማሪ ዝግጅቶች ግለጽ። ውጤታማ የሆኑ የመስክ ስምሪት ስብሰባዎች ያላቸውን ጥቅም አሳስባቸው:- የመጽሐፍ ጥናት መሪው እንደ አገልግሎት ክልሉ ሁኔታና ለአስፋፊዎች አመቺ የሚሆንበትን መንገድ አመዛዝኖ የመስክ ስምሪቱን ሰዓት መወሰን ይገባዋል፤ ቦታው ለአገልግሎት ክልሉ ቅርብ ቢሆን ይመረጣል፤ ከአገልግሎታችን ጋር የሚያያዝ ከሆነ በዕለት ጥቅሱም ላይ ውይይት መደረግ ይኖርበታል፤ የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት መሪዎች የራሳቸው የአገልግሎት ክልል ለሌላቸው አስፋፊዎች መስጠት ይችሉ ዘንድ የአገልግሎት ክልል ሊኖራቸው ይገባል፤ የመስክ ስምሪቱ ሰዓት ከ15 ደቂቃ መብለጥ የለበትም፤ በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በወጡ ሐሳቦች ላይ ወይም በአገልግሎት ላይ ስለሚያጋጥሙ ችግሮች አዎንታዊ ውይይት ማድረግ ይቻል ይሆናል፤ የአገልግሎት ጓደኞች የሚመደቡት እንደ አስፈላጊነቱ መሆን ይገባዋል። በዓለማዊ በዓላት ወቅት ለሚቀርቡት ሰላምታዎች እንዴት በጥበብ መልስ መስጠት እንደሚቻል ሐሳብ ስጥ።— የመጋቢት 8, 1986 የእንግሊዝኛ ንቁ! ገጽ 16-17ን ተመልከት።
15 ደቂቃ:- “‘ቤተሰባችሁን ገንቡ።’” ጥያቄና መልስ። ከ1995 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 228 ላይ ተሞክሮዎችን ጨምረህ አቅርብ።
12 ደቂቃ:- አስፋፊ እንዲሆኑ መርዳት። በሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ገጽ የሚገኘውን 19ኛ አንቀጽ ከልስ። ብቃት ያለው አንድ አስፋፊ ሽማግሌዎች ያልተጠመቀ አስፋፊ ሆኖ እንዲያገለግል የፈቀዱለትን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ለአገልግሎት ሲያዘጋጀው የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 111 አንቀጽ 2 ላይ ይወያያሉ። ተሞክሮ ያለው አስፋፊ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ምሥክርነት ሲካፈል ሊያጋጥሙት የሚችሉትን ነገሮችና አብዛኞቹ ሰዎች ጥሩ ምላሽ ባይሰጡ እንኳ ተስፋ መቁረጥ እንደማይኖርበት ይጠቁመዋል። ቅን ልብ ያለው የሚያዳምጥ ሰው ማግኘት ምን ዓይነት የደስታ ስሜት እንደሚያሳድር የሚያሳይ የሚያበረታታ ተሞክሮ ይነግረዋል። አንድ ላይ ሆነው መጽሔት ለማበርከት የሚያስችል አጭርና ቀላል አቀራረብ ይዘጋጁና አብረው ይለማመዱታል። የሚያበረታታ የምስጋና ቃል ከተናገረው በኋላ በዚያው ሳምንት ውስጥ አብረው ወደ አገልግሎት የሚሠማሩበት ቁርጥ ያለ ዝግጅት ያደርጋሉ።
መዝሙር 32 እና የመደምደሚያ ጸሎት
መጋቢት 31 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 211
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የመጋቢት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስብ። በሚያዝያ ወር ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉትን ወንድሞች ስም በሙሉ አስታውቅ። የጥያቄ ሣጥኑን ከልስ።
20 ደቂቃ:- “ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ደፋሮች ሁኑ።” (አንቀጽ 18-30) ጥያቄና መልስ። በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን ሣጥን ከልስ። ሁሉም የመስክ አገልግሎታቸውን ሪፖርት ሲመልሱ በየወሩ የሚያደርጓቸውን ተመላልሶ መጠየቆች እንዲሞሉ አበረታታቸው።
10 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። ወይም አንድ ሽማግሌ በመስከረም 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22-4 ላይ የሚገኘውን “ይቅርታ መጠየቅ ይኖርብሃልን?” የሚለውን ርዕስ ያቀርባል።
መዝሙር 207 እና የመደምደሚያ ጸሎት