ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ሰኔ እና ሐምሌ፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለው መጽሐፍ በሦስት ብር ይበረከታል። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በማስጀመር ላይ ትኩረት አድርጉ። ነሐሴ እና መስከረም፦ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ የሙታን መናፍስት . . .፣ መለኮታዊው ስም . . .፣ እና የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች የተባሉት ብሮሹሮች እያንዳንዳቸው በአንድ ብር ይበረከታሉ።
◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው ሰኔ 1 ወይም በተቻለ መጠን ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር አለበት። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ለጉባኤው አስታውቁ።
◼ በእጃችን ያሉ አዳዲስ ጽሑፎች:-
እንግሊዝኛ፦ ቪዲዮ ካሴት:- የይሖዋ ምሥክሮች የናዚን ጥቃት በጽናት ተወጡ። ፈረንሳይኛ፦ የ1997 የቀን መቁጠሪያ። ሲዳምኛ፦ ትራክት ቁጥር 14 የይሖዋ ምሥክሮች ምን ብለው ያምናሉ?
◼ በ1997 በአዲስ አበባ በሚደረገው ሁለተኛ የአውራጃ ስብሰባ ጊዜያዊ ፕሮግራም ላይ የተደረገ ማስተካከያ:- ኅዳር 7-9, 1997
◼ በእጃችን ያሉ ጽሑፎች:-
አማርኛ፦ ትራክት ቁጥር 13-16, 19-22። እንግሊዝኛ፦ ኮንኮርዳንስ፣ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣ እውቀት፣ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያ፣ መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፣ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች፣ ትሩ ሰብሚሽን።
◼ በቅርቡ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች:-
እንግሊዝኛ፦ “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ”፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፣ ሃፒነስ፣ ፍለጋ፣ ማመራመር፣ ደም . . .፣ የሕይወት ዓላማ፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ ባለ ማጣቀሻው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ (Rbi8)። የቴፕ ክሮች:- ትክክል የሆነውን ማድረግ እንዲሁም የአምላክን ፈቃድ ማድረግ።