የሰኔ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ሰኔ 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 81 (181)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የአገሪቱንና የጉባኤውን የመጋቢት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት በሚመለከት አንዳንድ ሐሳብ ስጥ።
15 ደቂቃ:- “የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ።” ጥያቄና መልስ።—በተጨማሪም በሚያዝያ 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-30 ላይ ያለውን ተመልከት።
22 ደቂቃ:- “ከአምላክ የሚገኘው እውቀት ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።” ሊቀ መንበሩ አንድ ወጣት ጨምሮ ከሁለት ወይም ከሦስት አስፋፊዎች ጋር ክፍሉን ይወያያል። ለዘላለም መኖር የተባለው መጽሐፍ ጥያቄዎችን በመመለስ በኩል አሁንም ሊረዳን የሚችለው እንዴት እንደሆነ አበክረህ በመግለጽ በአንቀጽ 1 ላይ ሐሳብ ስጥ። የልምምድ ሠርቶ ማሳያዎችን እንዲያቀርቡ አድርግና ከእያንዳንዱ አቀራረብ በኋላ የማሻሻያ ሐሳቦችን አክል።
መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 (48)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎችና። የሒሳብ ሪፖርት
15 ደቂቃ:- የእረፍት ጊዜ ማሳሰቢያዎች። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ብዙዎቻችን አንዳንድ ጊዜ ተጨማሪ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ እቅድ እናወጣ ይሆናል። እነዚህ ደግሞ ለእረፍት ወደ ሌላ ቦታ መሄድን፣ ዘመዶቻችንን መጠየቅን ወይም መዝናናትን ይጨምሩ ይሆናል። ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎቻችንን ችላ ሳንል ጉዳዮቻችንን እንዴት ልናደራጅ እንችላለን? የሚከተሉትን ነጥቦች ተወያዩባቸው:- (1) ሦስቱንም የአውራጃ ስብሰባ ቀናት በሙሉ መካፈል። (2) ቤታችን እያለንም ሆነ ርቀን ስንሄድ በስብሰባዎች ላይ አዘውትሮ መገኘት። (3) ዘወትር በአገልግሎት ለመካፈል ዝግጅት ማድረግና ከቤታችን ርቀን ከሄድን ደግሞ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታችንን ለጉባኤያችን መላክ። (4) በጉዟችን ወቅት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመስከር እንድንችል ጽሑፎችን ይዘን መሄድ። (5) የቀኑ ክፍለ ጊዜ በሚረዝምባቸው ቀናት በምሽት ምስክርነት ይበልጥ መሥራት። (6) ለአንድ ወይም ከአንድ ለሚበልጡ ወራት ረዳት አቅኚ መሆን። (7) በሽማግሌዎች በኩል ደግሞ የጉባኤውን እንቅስቃሴዎች በጥሩ ሁኔታ ማደራጀትና ለአንድ ሥራ የተመደበ ሰው በማይኖርበት ጊዜ ሥራዎቹ መከናወናቸውን ማረጋገጥ።
20 ደቂቃ:- ሌሎችን ማስተማር—አጣዳፊ ሥራ ነው። በሽማግሌ የሚሰጥ ንግግር። በ1997 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 33 ላይ ወይም በጥር 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ ላይ የሚገኘውን የ1996 ዓለም አቀፍ የአገልግሎት ሪፖርት ከልስ። ሰዎች በሚገኙበት በየትኛውም ቦታ ለመመስከር የሚደረገው የተጠናከረ ጥረት ፍሬ እያፈራ ነው። አሁን አጣዳፊ የሆነው ነገር ጽሑፍ ያበረከትንላቸውን ሰዎች ተመልሰን መጠየቁና እውነትን ለሰዎች ማስተማሩ ነው። ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ሰዎችን ስናነጋግር ተመልሰን ልንጠይቃቸው እንድንችል ስማቸውንና አድራሻቸውን በዘዴ እንጠይቅ፤ ወይም ቤታቸው ሩቅ ካልሆነ እንዲያሳዩን እናድርግ። የመንግሥቱን ዘር መትከል ብቻ ሳይሆን ማጠጣትም ያስፈልገናል። (1 ቆሮ. 3:6-8) በመልካም መሬት ላይ የተዘራ ዘር ጥሩ የማስተማር ዘዴ ሲታከልበት ግለሰቡ ትርጉሙን እንዲያስተውል ሊረዳው ይችላል። (ማቴ. 13:23) በማስተማሩ ሥራ የቻልነውን ያህል ሙሉ በሙሉና በብቃት ልንካፈል ይገባናል። (ዕብ. 5:12) በሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ገጽ አንቀጽ 25-6 ላይ ያሉትን ነጥቦች አክለህ አቅርብ። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? በተሰኘው ብሮሹር ወይም እውቀት በተባለው መጽሐፍ ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ አሳስብ።
መዝሙር 90 (204) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 42 (92)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በቅርቡ ከወጡ መጽሔቶች ላይ ውይይት ለመጀመር የሚያስችሉ ነጥቦችን ጥቀስ።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- ሃይማኖትህ እውነተኛ ይሁን ሐሰተኛ ለይተህ እወቅ። አንድ ሽማግሌ ብቃት ካላቸው ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ጋር ታኅሣሥ 22, 1989 የእንግሊዝኛ ንቁ! ገጽ 18ን መሠረት በማድረግ ውይይቱን ይመራል። በተደጋጋሚ ጊዜያት የምናነጋግራቸው ቅን ልብ ያላቸው የሚመስሉ ብዙ ሰዎች አሉ። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ፈቃደኞች አልሆኑም። ካገኙት ትክክለኛ እውቀት ጋር የሚስማማ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን እንዲገነዘቡ ለማድረግ በዚህ ንቁ! መጽሔት ርዕስ ላይ ያሉትን ነጥቦች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ተወያዩ። እውቀት በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 5 ላይ “አምላክ የሚቀበለው የእነማንን አምልኮ ነው?” በሚለው ርዕስ ሥር የሚገኙትን ቁልፍ ነጥቦች ከልስ። አንቀጽ 20ን አንብብ። እንደዚህ ያሉ ሰዎችን ተመልሰን በመጠየቅ ጥናት እንዲጀምሩ እንዲሁም በስብሰባዎች እንዲገኙ በደግነትና በዘዴ ልናበረታታቸው እንችላለን።
መዝሙር 89 (201) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 86 (193)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- ሌሎች ስለ እኛ ምን ይላሉ? በመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎች ማውጫዎች 1986-1990 ገጽ 268-9 እንዲሁም 1991-1994 ገጽ 84-5 በሚገኘው ሐሳብ ላይ የተመሠረተ ንግግር። የይሖዋ ምሥክሮችን ማለትም ጠባያችንና ሥራችንን በተመለከተ ‘ሌሎች ከሰነዘሯቸው አስተያየቶች’ መካከል ጎላ ያሉትን ምረጥ። ሌሎች በእኛ ላይ ያዩት ነገር እንዴት በመልካም ጎኑ እንደነካቸው አሳይ። ይህ ሁልጊዜ ተገቢ ጠባይ እንድናሳይና በሥራችን ወደኋላ እንዳንል ሊያነሳሳን የሚገባው ለምን እንደሆነ አብራራ። እነዚህን የመሰሉ መልካም አስተያየቶችን ስለ እኛ የበለጠ ለማወቅ ከሚፈልጉ ጓደኞቻችንና ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ጋር ስንነጋገር እንዴት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል ጠቁም።
20 ደቂቃ:- “ወላጆች—ልጆቻችሁን እንዲሰብኩ አሰልጥኗቸው።” ጥያቄና መልስ። አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 99-100 “ወጣቶችን መርዳት” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን መመሪያ ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 93 (211) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 82 (183)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የሰኔ ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው።
20 ደቂቃ:- “ወጣቶች—መንፈሳዊ ግቦቻችሁ ምንድን ናቸው?” ሁለት አባቶች ክፍሉን አብረው ይወያዩበታል። ልጆቻቸው ቁሳዊ ጥቅሞችን ከማሳደድ ይልቅ መንፈሳዊ በረከቶች የሚያስገኙ ቲኦክራሲያዊ ግቦች ማውጣታቸው የግድ አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት እንዲገነዘቡ ሊረዷቸው የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ይመረምራሉ።—አገልግሎታችን የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 116-18 ተመልከት።
15 ደቂቃ:- የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ “የዘመቻው እንቅስቃሴያችን ምን ይመስላል?” በሚል ርዕስ ንግግር ያቀርባል። እስካሁን ምን ያህል ለዘላለም መኖር መጽሐፍ እንደተበረከተ ግለጽና ዘመቻውን አስመልክቶ ከማኅበር ከተላከው ደብዳቤ ውስጥ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን ከአንድ ሠርቶ ማሳያ ጋር አቅርብ።
ነመዝሙር 46 (107) እና የመደምደሚያ ጸሎት።