የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/97 ገጽ 2
  • የሐምሌ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሐምሌ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሐምሌ 7 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 14 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 21 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 28 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 7/97 ገጽ 2

የሐምሌ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ሐምሌ 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 3 (6)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሁሉም አመቺ በሆነበት ቦታ ሁሉ ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ እንዲጠቀሙ አበረታታ። የአገሪቱንና የጉባኤውን የሚያዝያ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት በሚመለከት ሐሳብ ስጥ።

15 ደቂቃ፦ “የታመኑ መሆን ይክሳል።” ጥያቄና መልስ። በጥር 22, 1993 የእንግሊዝኛ ንቁ! መጽሔት ገጽ 18-21 ላይ የሚገኘውን ምሳሌ ጨምረህ አቅርብ።

20 ደቂቃ፦ መደበኛ ያልሆነ ምስክርነት ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ። በየቀኑ ለምናገኛቸው ሰዎች ለመመሥከር የሚያስችሉ አጋጣሚዎች ይኖሩናል። አንዳንድ ጊዜ ለመመስከር የሚያስችል አጋጣሚ አግኝተን መጽሐፍ ቅዱስ ወይም ጽሑፎች ሳንይዝ እንቀር ይሆናል። አስቀድማችሁ እቅድ አውጡ። እንግዶችን ወደ ቤታችሁ በምታስገቡበት በር አጠገብ በቀላሉ በሚታዩበት ቦታ ጥቂት ጽሑፎችን አስቀምጡ። ልዩ ልዩ ዓይነት ጽሑፎችን በእጅ ወይም በኪስ በሚያዙ ቦርሳዎች በማድረግ ያዙ ወይም በመኪናችሁ ውስጥ፣ በሥራ ቦታችሁ ወይም በትምህርት ቤት መሳቢያችሁ ውስጥ አስቀምጡት። በሕዝብ መጓጓዣ በምትጠቀሙበት ጊዜ ጽሑፍ ከእጃችሁ አይለይ። ለሥራ ጉዳይ፣ በአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወይም ለእረፍት ወደ አንድ ቦታ በምትጓዙበት ጊዜ ጥቂት ጽሑፎችን ይዛችሁ ሂዱ። በትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 80-2 አንቀጽ 11-16 ላይ የሚገኙትን ተጨማሪ ሐሳቦች ተወያዩባቸው። አንድን ነጋዴ፣ የሥራ ባልደረባችንን፣ አብሮን የሚማርን ልጅ፣ በጉዞ ላይ ያገኘነውን ወይም በእረፍት ላይ ያለን አንድ ሰው ለማነጋገር የሚያስችሉ የተለያዩ መንገዶችን በሦስት ወይም አራት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።

መዝሙር 32 (70) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 23 (48)

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ በማበርከት የተገኙ ተሞክሮዎችን ተናገር።

18 ደቂቃ፦ “ሰዎች በሚገኙበት ቦታ ሁሉ መመሥከር።” በንግግር የሚቀርብ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ከ1997 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 43-6 ላይ የሚገኙትን ተሞክሮዎች ጨምረህ አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ ወላጆች ሆይ—ልጆቻችሁን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አስተምሯቸው። አንድ ሽማግሌ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ሊያስተምሯቸው የሚገባ መሆኑን የሚገልጹ ቅዱስ ጽሑፋዊ መመሪያዎችን በመዘርዘር በውይይት ያቀርበዋል። (ምሳሌ 22:6፤ 2 ጢሞ. 3:14, 15) አንዳንድ ወላጆች ልጆች አድገው የራሳቸውን ውሳኔ ማድረግ እስከሚችሉ ጊዜ ድረስ ጥልቀት ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ሊሰጣቸው አይገባም ብለው ያስባሉ። በዚህ ምክንያት ብዙ ልጆች በዓለም ተውጠዋል። መንፈሳዊ ስልጠና መሰጠት ያለበት ከሕፃንነታቸው አንስቶ ነው። (የእንግሊዝኛ ንቁ! 97 3/8 26-7፤ መጠበቂያ ግንብ 15-109 13-14) ለልጆቻቸው መንፈሳዊነት ትኩረት ከሚሰጡ ወላጆች ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። አባት የመሪነቱን ቦታ የሚይዝ ቢሆንም ሁለቱም ወላጆች ለልጆቻቸው ዘላቂ የሆነና የተሟላ ፕሮግራም በማውጣት የየግል ኃላፊነታቸውን እንዴት እንደሚወጡ አሳይ። ባልና ሚስቱ ማኅበሩ በቤት ውስጥ ማስተማርን በተመለከተ ውጤታማና ተግባራዊ ፕሮግራም ስለማውጣት የሰጠውን ሐሳብ ተግባራዊ በማድረግ እውነትን ለልጆቻቸው ለማስተማር ምን ጥረት እንዳደረጉ ይናገራሉ። ሽማግሌው ወላጆች የአምላክ ቃል እንዲያደርጉት የሚያዛቸውን ነገር ማድረጋቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርጎ ይገልጻል።—የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ 85 4/1 23፤ ኤፌ. 6:1-4

ነመዝሙር 72 (164) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 90 (204)

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ያወጣነውን ግብ ካስታወስክ በኋላ መጽሐፉን ለማበርከት የሚያስችል ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

13 ደቂቃ፦ ‘ማን ይሄድልናል?’ አዎንታዊ የሆነ ንግግር። በየካቲት 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ገጽ አንቀጽ 16-17 ላይ የዘወትር አቅኚ ስለመሆን የተሰጠውን ማበረታቻና ተሞክሮ ጨምረህ አቅርብ። የዘወትር አቅኚ ሆነው ለማገልገል የማይችሉ ደግሞ በሚመጣው የአገልግሎት ዓመት በየትኛው ወር ወይም ወራት ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል እንደሚችሉ አስቀድመው እቅድ ሊያወጡ ይፈልጉ ይሆናል።

20 ደቂቃ፦ አገልግሎትህን ሙሉ በሙሉ ፈጽም። አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 5-8 ላይ የተመሠረተ በአገልግሎት የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ሁሉም የአምላክ አገልጋዮች እንደመሆናቸው መጠን ያለባቸውን ኃላፊነት በቁም ነገር እንዲመለከቱት በማነቃቃት የስብከቱን ሥራ አስፈላጊነትና አጣዳፊነት ጎላ አድርገህ ግለጽ።

መዝሙር 33 (72) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 98 (220)

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በነሐሴ የሚበረከቱትን ብሮሹሮች ከልስ። (ሁለት ብሮሹሮች አንድ ላይ ሊበረከቱ ይችላሉ።) ብሮሹር የተበረከተላቸውን ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ሞክር። በመጋቢት 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ገጽ ላይ የቀረቡትን ውጤታማ የሆነ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ የሚያስችሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ጠቁም። ጥናት ማስጀመር ያለብን አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? በተባለው ብሮሹር ወይም እውቀት በተባለው መጽሐፍ መሆን አለበት።

15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

18 ደቂቃ፦ “‘በአምላክ ቃል ማመን’ የ1997 የአውራጃ ስብሰባ” አንቀጽ 1-9 ላይ የሚደረግ ውይይት።

መዝሙር 80 (180) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ