ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴና መስከረም፦ ከሚከተሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ የሙታን መናፍስት . . .፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም እና የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች። ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ነጠላ ቅጂዎች፤ ኮንትራት ማስገባት ይቻላል። ኅዳር፦ የመንግሥት ዜና ቁጥር 35 ስርጭት። የመንግሥት ዜና ቁጥር 35 ቅጂን በእያንዳንዱ መኖሪያ ቤት ውስጥ ለሚገኙ የቤቱ ባለቤቶች በማዳረስ የአገልግሎት ክልላቸውን ሸፍነው የጨረሱ ጉባኤዎች ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ሊያበረክቱ ይችላሉ።
◼ በዓመት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ትምህርት ቤት የሚዘጋባቸውና ሥራ የማይኖርባቸው ዓለማዊ በዓላት ይኖራሉ። እነዚህ ጊዜያት የጉባኤውን የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴ ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ በጣም ጥሩ አጋጣሚዎች ናቸው። ሽማግሌዎች እነዚህ ወቅቶች መቼ እንደሚውሉ አስቀድመው በመመልከት በእነዚህ የበዓል ቀናት የቡድን ምሥክርነት ለማከናወን እየተደረጉ ያሉትን ዝግጅቶች ለጉባኤው በቅድሚያ ሊያሳውቁ ይገባል።
◼ በአዲስ አበባ ሊደረግ የታቀደው የ1997 የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም ሁለት ጊዜ መሆኑ ቀርቶ ከጥቅምት 17-19, 1997 ለአንድ ጊዜ ብቻ እንዲካሄድ ዝግጅት ተደርጓል።
◼ ለ1998 የአገልግሎት ዓመት የሚውሉ በቂ መጠን ያላቸው ቅጾች ለእያንዳንዱ ጉባኤ እየተላኩ ነው። እባካችሁ እነዚህን ቅጾች ሳታባክኑ ተጠቀሙባቸው። ቅጾቹ ለታቀደላቸው ዓላማ ብቻ ሊውሉ ይገባል።
◼ እያንዳንዱ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S(d)-18-AM) ይደርሱታል። የጉባኤው ጸሐፊና የጽሑፍ አገልጋዩ በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎች የሚቆጠሩበትን ቀን ለመወሰን በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ተገናኝተው መነጋገር አለባቸው። በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎች ሁሉ አንድ በአንድ መቆጠር አለባቸው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ ላይ መሞላት አለበት። በጉባኤው እጅ ያሉትን የመጽሔቶች ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ ማግኘት ይቻላል። እባካችሁ ዋናውን ቅጂ ከመስከረም 6 በፊት ለማኅበሩ ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ በፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሥሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ጸሐፊው ቆጠራው ትክክል መሆኑን መቆጣጠር ያለበት ሲሆን ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ደግሞ ተሠርቶ ያለቀውን ቅጽ መመርመር ይኖርበታል። ጸሐፊውና ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በቅጹ ላይ ይፈርማሉ።
◼ የመንግሥት አዳራሽ ያላቸው ጉባኤዎች በሙሉ የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ የሚል ምልክት እንዲኖራቸው እናበረታታለን። ይህ ምልክት በሕንፃው ላይ ወይም ከሕንፃው አጠገብ መሆን አለበት። በተለያየ መልክ የተሠሩ የዚህ ዓይነት ምልክቶች እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች በተባለው ብሮሹር ገጽ 15 ላይ በጥሩ ሁኔታ በሥዕል ቀርበዋል። የኦሮምኛው ትክክለኛ አጻጻፍ የሚከተለው ነው:- GALMA MOOTUMMAA Dhugaa Baaftota Yihowaa. የወላይትኛው ትክክለኛ አጻጻፍ ደግሞ የሚከተለው ነው:- Yihowaa Markkatu KAWOTETTAA ADDARAASHSHAA (ይሖዋ ማርካቱ ካዎተታ አዳራሻ)
◼ በእጃችን ያሉ አዳዲስ ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ፦ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ጥራዞች 1996፣ የ1997 የዓመት መጽሐፍ። የቴፕ ክሮች፦ የመንግሥቱን መዝሙሮች ዘምሩ፣ ታላቁ ሰው (በካሴት)፣ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት (በካሴት)። ስፓንኛ፦ ፍለጋ፣ ማመራመር፣ እውቀት፣ የቤተሰብ ደስታ፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ (ትንሹ)፣ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም።
◼ በቅርቡ በድጋሚ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ጽሑፎች፦ አረብኛ፦ ትራክት:- ዘ ሮድ ቱ ፓራዳይዝ። እንግሊዝኛ፦ ፍጥረት፣ ዴሉክስ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም (Dbi-12) (ቡናማና ደማቅ ቀይ)፣ ኪንግደም ኢንተርሊኒየር። የቴፕ ክሮች:- የመንግሥቱ ዜማዎች ቁጥር 2-8። ፈረንሳይኛ፦ መጽሐፌ፣ . . . በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች፣ መለኮታዊው ስም፣ ሥላሴ፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት።