ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥር እና የካቲት፦ ወጣትነትህ እና/ወይም የቤተሰብ ኑሮ። መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሚያዝያ፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ነጠላ ቅጂዎች።
◼ ጥር 5 በሚጀምር ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚገኙት የተጠመቁ አስፋፊዎች በሙሉ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገው ሰነድ ይሰጣቸዋል። ለልጆቻቸው ደግሞ መታወቂያ ካርዱ ይሰጣቸዋል።
◼ ከየካቲት (ቢዘገይ ከመጋቢት 1) ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር “አምላክ ለሕይወት ያለው ዓይነት አመለካከት አላችሁን?” የሚል ይሆናል።
◼ እሁድ መጋቢት 29, 1998 የሚቀርበው ልዩ ንግግር “በመጽሐፍ ቅዱስ ልትተማመኑ የምትችሉበት ምክንያት” በሚል ይሆናል። ለሁሉም ጉባኤዎች አስተዋጽዖው ይላካል።
◼ ከጥር 5 ጀምሮ በጉባኤ መጽሐፍ ጥናት የሚጠናው ጽሑፍ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? የተባለው ብሮሹር ይሆናል።
◼ የዋጋ ማስተካከያ:- ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር 1998:- ለአስፋፊዎችም ሆነ ለአቅኚዎች ብር 2.50፤ የቴፕ ክሮች (4 በአንድ ላይ) ቤተሰብ:- ለአቅኚ ብር 41.50፣ ለአስፋፊ ብር 51.50፤ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ዴሉክስ (Dbi12):- ለአቅኚ ብር 40፣ ለአስፋፊ ብር 50፤ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም በኪስ የሚያዝ (Dbi25) ለአቅኚ ብር 30፣ ለአስፋፊ ብር 40።
◼ በዚህ ዓመት በሚደረገው ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ውስጥ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆነው ለማገልገል ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው የዘወትር አቅኚዎች ወይም ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መረጃዎች በመስጠት እስከ ጥር 20, 1998 ድረስ በትልቅ ሉክ ወረቀት ጽፈው ሊልኩልን ይገባል:- 1) ስም፤ 2) ዕድሜ፤ 3) የጥምቀት ቀን፤ 4) ነጠላ ወይም ያገባ መሆኑንና የሚያስተዳድረው ቤተሰብ ብዛት፤ 5) ከመቼ እስከ መቼ ማገልገል እንደምትችሉ (መጋቢት-ግንቦት?) 6) የምታውቋቸው ቋንቋዎች፤ 7) አመልካቹ አዘውትሮ ከቤት ወደ ቤት የሚያገለግል መሆን አለመሆኑን። ከዚያም የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አመልካቹ ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ 1997 ያገለገለውን አማካይ ሰዓት ማስፈር አለበት። እንዲሁም ድጋፋቸውንና ፊርማቸውንም ያሰፍራሉ።
◼ የሚከተሉት ብሮሹሮች በቅርቡ ደርሰውናል:-
አማርኛ፦ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፤ ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?፤ እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?
እንግሊዝኛ፦ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ
ኦሮምኛ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
ትግርኛ፦ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፤ እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች፤ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፤ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፤ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፤ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?፤ የምትወዱት ሰው ሲሞት፤ መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች (ለጥምቀት እጩዎች የተዘጋጁ ጥያቄዎች)፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይት መጀመርና መቀጠል የሚቻልበት መንገድ (በማመራመር መጽሐፍ ላይ የተመሰረተ)
◼ በድጋሚ የደረሱን:-
አማርኛ፦ የመዝሙር መጽሐፍ
አረብኛ፦ ፍለጋ፣ የቤተሰብ ደስታ፣ ትሩ ሰብሚሽን፣ መለኮታዊ ስም
ፈረንሳይኛ፦ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም
ጣሊያንኛ፦ የ1997 የዓመት መጽሐፍ
ትግርኛ፦ በደስታ ኑር፣ ትራክት ቁ. 14 እና 16