ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
◼ በደሴ፣ በድሬ ዳዋና በጅማ የሚገኙ ተጨማሪ ሰዎች ከፕሮግራሙ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ በማሰብ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት በላይ የአውራጃ ስብሰባዎች አድርገናል። በአምስቱ ቦታዎች በተደረጉት በእነዚህ ስብሰባዎች ጠቅላላ ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር 9,861 ሲሆን የተጠማቂዎች ቁጥር ደግሞ 342 ነበር።
◼ በኬንያ ናይሮቢ ከጥር 15, 1998 ጀምሮ በአዲሱ የቅርንጫፍ ቢሮ ሕንፃ ለሚካሄደው 7ኛው የአገልጋዮች ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ከአገራችን ሰባት ነጠላ አቅኚ ወንድሞች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።
◼ ጥቅምት 25, 1997 በናይሮቢ ሰፊና ውብ የሆኑ የቅርንጫፍ ቢሮ ሕንፃዎች ለአምላክ አገልግሎት ተወስነዋል። ከተለያዩ አገሮች የመጡ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ ከ1,700 በላይ ለሆኑ አድማጮች የሕንፃዎቹን ለአምላክ መወሰን አስመልክቶ ንግግር ያቀረበው የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ወንድም ኤም ጂ ሄንሼል ነበር። በኬንያ የሚገኘው የቤቴል ቤተሰብ አባላት ቁጥር ወደ 80 አካባቢ ከፍ ብሏል።
◼ በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ዳር በሚገኙት በአቃቂና በቡራዩ ሁለት የመንግሥት አዳራሾች ለአምላክ ተወስነዋል። በአዋሳ፣ በጊምቢ፣ በነቀምት፣ በሻሸመኔና በሶዶ በግንባታ ላይ ያሉት ሌሎች የመንግሥት አዳራሽ ፕሮጄክቶችም በመፋጠን ላይ ናቸው። የሚጠናቀቁበትንና ለአምላክ የሚወሰኑበትን ጊዜ በጉጉት እንጠባበቃለን።
◼ የተጠናቀቀው የ1997 የአገልግሎት ዓመት 5% ጭማሪ በማግኘት 5,649 የደረሰ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥርና 15,716 የደረሰ ከፍተኛ የመታሰቢያው በዓል ተሰብሳቢዎች ቁጥር ነበሩት! ይህ በጣም ያስደስተናል። አንድ አስፋፊ የሚደርሰው የሰው ብዛት በሬሾ ሲሰላ 10,000 የነበረው ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ለ9,736 ደርሷል። ቢሆንም ገና መሠራት ያለበት ከፍተኛ የመሰብሰብ ሥራ አለ፤ በተለይ ደግሞ በትንንሽ ከተሞችና በገጠር አካባቢዎቸ ብዙ ሥራ ይቀራል። በየወሩ ሳናቋርጥ በማገልገል ሪፖርታችንን የምንመልስና ክልላችንን በሚገባ የምንሸፍን፣ ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎቸ ሁሉ ተመልሰን የምንጠይቅና አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በተባለው ብሮሹርም ሆነ በእውቀት መጽሐፍ አማካኝነት ጥናት ለማስጀመር ንቁ ከሆንን የበለጠ ጭማሪ ለማግኘት ልንጠብቅ እንችላለን።