ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች የካቲት፦ ወጣትነትህ እና/ወይም የቤተሰብ ኑሮ። መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ትኩረት አድርጉ። ሚያዝያና ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ነጠላ ቅጂዎች።
◼ የአውራጃ ስብሰባ የሚደረግባቸው ጊዜያዊ ፕሮግራሞች:- ድሬዳዋ:- መስከረም 25-27, 1998፤ ደሴ:- ጥቅምት 2-4, 1998፤ ሻሸመኔ:- ጥቅምት 9-11, 1998፤ ጅማ:- ጥቅምት 16-18, 1998፤ አዲስ አበባ:- ጥቅምት 23-25 እና ጥቅምት 30—ኅዳር 1, 1998
◼ ኮንትራት የማደስ ሥራችንን ለማቅለል “Expiring Subscription Slips” (M-91 እና M-191) የተባሉትን ቅጾች ጉባኤዎች እዲጠቀሙ እንጠይቃለን። በሆነ ምክንያት ይህን ቅጽ ካላገኛችሁ የኮንትራት መጽሔቱ ተጠቅልሎ ከሚመጣበት ወረቀት ላይ የተለጠፈውን አድራሻ ቆርጣችሁ ከተለመደው የኮንትራት መግቢያ ቅጽ ጋር አያይዛችሁ ልትልኩልን ትችላላችሁ።
◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች እንቅስቃሴ መመርመር ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸው ላይ ለመድረስ ያልቻሉ አቅኚዎች ካሉ እርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ ሽማግሌዎቹ መቀየስ ይኖርባቸዋል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በጥቅምት 1, 1993 (S-201) እና በጥቅምት 1, 1992 (S-201) የተላኩትን የማኅበሩን ደብዳቤዎች ከልሱ።