የየካቲት የአገልግሎት ስብሰባዎች
የካቲት 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 73 (166)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
15 ደቂቃ፦ “የይሖዋ ምሥክሮች—እውነተኞቹ ወንጌላውያን።” ጥያቄና መልስ። በመስከረም 1, 1992 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 19 ላይ ያለውን ሳጥን ከልስ።
20 ደቂቃ፦ “አዎንታዊ አመለካከት በመያዝ ምሥራቹን ማቅረብ።” የቀረቡት መግቢያዎች ፍላጎት ለመቀስቀስ በሚያስችል ሁኔታ እንዴት እንደተዘጋጁ በመጥቀስና አድማጮችን ለሥራ በማነሳሳት ትምህርቱን አቅርብ። እንዲሁም በአንቀጽ 2 እና በአንቀጽ 6 ላይ የተመሠረቱ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
መዝሙር 62 (146) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 (48)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ “በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እየተሠቃዩ ነው—እርዳታ ማግኘት ይችሉ ይሆን?” በሚል ርዕስ በጥቅምት 1993 በወጣው ንቁ! ከገጽ 12-15 ያለውን ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በንግግር ያቀርበዋል። እባክህ የመጨረሻዎቹን አምስት ደቂቃዎች አድማጮች ተሳትፎ ለሚያደርጉበት ክለሳ ተጠቀምባቸው።
መዝሙር 98 (220) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 35 (79)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት የሚያስፈልግህ ለምንድን ነው? አንድ ሽማግሌ በነሐሴ 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 8-11 ላይ ያሉትን ዋና ዋና ነጥቦች በማብራራት በሁሉም ስብሰባዎች ላይ አዘውትሮ የመገኘትን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርጎ ይገልጻል።
15 ደቂቃ፦ “በየሳምንቱ በአገልግሎት መሳተፍ የበለጠ ደስታ ያስገኛል።” አንቀጾቹን እያነበብክ አብራራ። (የመንግሥት አገልግሎታችን (እንግሊዝኛ) 4/87 ገጽ 1) አዘውትሮ የማገልገልንና ሁሉም በትክክል ሪፖርት የማድረጋቸውን ግብ አጉላ። (የመንግሥት አገልግሎታችን (እንግሊዝኛ) 4/87 የሌላቸው ጉባኤዎች አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 106-110 ላይ ያለውን ትምህርት ሊጠቀሙ ይችላሉ።)
15 ደቂቃ፦ “ይሖዋ ረዳቴ ነው።” አንድ ሽማግሌ በግለትና በሚያበረታታ መንገድ በንግግር ያቀርበዋል።
መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 2 (4)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በመጋቢት የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። በታኅሣሥ 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን በገጽ 10 ላይ ባሉት ነጥቦች ተጠቅመህ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት የሚያስችል አንድ ወይም ሁለት ሐሳቦችን ጥቀስ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመርን ግብ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።
15 ደቂቃ፦ “ውጤታማ ሆኖ ካገኛችሁት ተጠቀሙበት!” ጥያቄና መልስ። ከአድማጮች መካከል ልምድ ያላቸው አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች በመግቢያው ቀላልነትና ባገኙት ውጤት የተነሳ ለረዥም ጊዜ ሲጠቀሙበት በቆዩት መግቢያ ላይ አጠር ያለ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። ከዚያም አንዳንዶች በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በቅርቡ ከወጡት መግቢያዎች መካከል ውጤታማ ሆኖ ያገኙትን እንዲናገሩ ጋብዝ።
20 ደቂቃ፦ መግቢያዎችህን ተለማመድ። ትምህርት ቤት መመሪያ ከተባለው መጽሐፍ በገጽ 98-9 በአንቀጽ 8-9 ላይ የተመሠረተ አጠር ያለ ንግግር። መግቢያዎቻችንን የመገምገምንና ይበልጥ ውጤታማ መሆን የምንችልባቸውን መንገዶች የመፈለግን አስፈላጊነት አበክረህ ግለጽ። ሁለት እህቶች ከቤት ወደ ቤት ሲሄዱ የተጠቀሙበትን መግቢያ ሲገመግሙና እንዴት ማሻሻል እንደሚችሉ ሲወያዩ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። በሚቀጥለው ጊዜ ሊጠቀሙበት ያሰቡትን መግቢያ የሚለማመዱበት አጭር ጊዜም ይኖራቸዋል። እርስ በርሳቸው ጠቃሚ ሐሳቦችን ይለዋወጣሉ። ክፍሉን የሚያቀርበው ወንድም ሁሉም መግቢያዎቻቸውን እንዲመረምሩና እንዲለማመዱ ማበረታቻ በመስጠት ይደመድማል።
መዝሙር 84 (190) እና የመደምደሚያ ጸሎት።