የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/98 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 4/98 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎቸ ሚያዝያና ግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ነጠላ ቅጂዎች። ሰኔ፦ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ሰው። ሐምሌና ነሐሴ፦ ከሚከተሉት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሙታን መናፍስት ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? እና ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም።

◼ ለማንም ባልተመደቡ የአገልግሎት ክልሎች ውስጥ አስፋፊዎች ሲያገለግሉ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ሊያበረክቱ ይችላሉ። የቆዩ መጽሔቶችም ሊበረከቱ ይችላሉ። ቤታቸው ለማይገኙ ወይም ጽሑፎች ለማይወስዱ ሰዎች ለማበርከት የተለያዩ ዓይነት ትራክቶችን መያዝ ይገባናል። አሁንም የመንግሥት ዜና ቁጥር 35 ያላቸው አስፋፊዎች ወይም ጉባኤዎች ካሉ በዚህ ክልል ውስጥ ሊያሰራጩት ይገባል። በተለይ ለማንም ባልተመደበ የአገልግሎት ክልል ውስጥ የሚገኙ ልዩ አቅኚዎች ወይም በአቅራቢያው ያሉ ጉባኤዎች ጥረት ሊያደርጉ ይገባል።

◼ አምስት ቅዳሜና እሁዶች ያሉት የግንቦት ወር ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል ለብዙዎች አመቺ ሊሆንላቸው ይችላል።

◼ በአዲስ አበባ ሊደረጉ ለታቀዱት ለሁለቱ የአውራጃ ስብሰባዎች ከዚህ ቀጥሎ ሊቀየሩ የሚችሉ ድልድሎች ተደርገዋል:- አዲስ አበባ I (ጥቅምት 23-25):- ወረዳ 3፣ ወረዳ 2ለ (አዋሬ ጉባኤን አይጨምርም)፣ ወረዳ 1 (ነቀምቴ) በጅማና በሶዶ ልዩና የወረዳ ስብሰባ የሚካፈሉትን ጉባኤዎችና ቡድኖች አይጨምርም፣ ወረዳ 6 (ባሕር ዳር) በደሴና በመቀሌ ልዩና የወረዳ ስብሰባ የሚካፈሉትን ጉባኤዎችና ቡድኖች አይጨምርም። አዲስ አበባ II (ከጥቅምት 30-ኅዳር 1):- ወረዳ 5፣ ወረዳ 2ሀ እና አዋሬ ጉባኤ።

◼ የ1998 የአውራጃ ስብሰባ ደረት ላይ የሚለጠፉ ካርዶች ከሐምሌ ወር ጀምሮ ከሚላኩ ጽሑፎች ጋር አብረው ይመጣሉ። እነዚህን ካርዶች ማዘዝ አያስፈልግም። ጉባኤዎች ተጨማሪ ካርዶች ከፈለጉ በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14-AM) መጠየቅ አለባቸው። ደረት ላይ የሚለጠፉ ካርዶች መያዣ ጉባኤዎች ካስፈለጋቸው መጠየቅ ይገባቸዋል።

◼ የ1997 የመጠበቂያ ግንብ ቤተ መጻሕፍት (CD-ROM) በዘጠኝ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል። ምርምር ለማድረግ የሚረዳ ይህ ጠቃሚ መሳሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተዘጋጅቷል። ከ1980 እስከ 1997 የታተሙትን ጽሑፎች ይይዛል። በእንግሊዝኛ (ከ1950 ጀምሮ ያለውን መጠበቂያ ግንብ)፣ በጀርመንኛ፣ በጣልያንኛና በስፓንኛ ከ1970 ጀምሮ የታተሙትን ጽሑፎች ይይዛል። ጉባኤዎች የ1997 የመጠበቂያ ግንብ ቤተ መጻሕፍት በእነዚህ ቋንቋዎች እንዲመጣላቸው ማዘዝ ሊጀምሩ ይችላሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ