የሚያዝያ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ሚያዝያ 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 10 (27)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሚያዝያ 11 ቀን የሚውለው የመታሰቢያ በዓል የት እንደሚከበርና በስንት ሰዓት እንደሚጀመር አስታውሳቸው። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
15 ደቂቃ፦ “አገልግሎታችን የእውነተኛ ፍቅር መግለጫ ነው።” ጥያቄና መልስ። መጠበቂያ ግንብ 3-108 ገጽ 4-5 ከአንቀጽ 3-7 ላይ ያለውን ሐሳብ አጠር አድርገህ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “መጽሔቶች መንግሥቱን ያስታውቃሉ።” አንድ ሽማግሌ መጽሔት በማበርከት ውጤታማ ከሆኑ ሦስት ወይም አራት አስፋፊዎች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። በቅርብ የወጡ መጽሔቶች በያዟቸው ማራኪ ርዕሶች ላይ ከተወያያችሁ በኋላ እነዚህን ርዕሶች እንዴት ለመግቢያነት ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ ሐሳብ ስጥ። በጉባኤያችሁ መጽሔት በማሰራጨት በኩል እንዴት መሻሻል ማድረግ እንደሚቻል አሳስብ። በቅርብ ከወጡት መጽሔቶች ለምሳሌ ያክል ማኅበረሰብን፣ ቤተሰብን ወይም ኅብረተሰብን ስለሚመለከቱ ችግሮች የሚያወሱ ፍላጎት የሚቀሰቅሱ ርዕሶች ጥቀስ። ሁለት ወይም ሦስት ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ።
መዝሙር 67 (156) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 57 (136)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች፣ በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። እስከ ግንቦት ወር ማብቂያ ድረስ አልፎ አልፎ የተሠሩና ራቅ ያሉ ክልሎችን ለመሸፈን ልዩ ጥረት ማድረግ እንደሚኖርብን ሁሉንም አስፋፊዎች አሳስብ። ከያዝነው የአገልግሎት ዓመት መጀመሪያ አንስቶ (ወይም ካለፈው ዓመት ልዩ የክልል ዘመቻ አንስቶ) ስንት ክልሎች በጭራሽ ተሸፍነው እንደማያውቁ የክልል አገልጋዩ ጠቅለል ያለ ሐሳብ እንዲያቀርብ ጋብዘው። በመቀጠልም እነዚህን ክልሎች ደረጃ በደረጃ ለመሸፈን የሚያስችል ተግባራዊ ዕቅድ ተናገር።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ “ለስብሰባዎች ‘ከበፊቱ የበለጠ’ ትኩረት ስጡ።” ጥያቄና መልስ። አገልግሎታችን መጽሐፍ ከገጽ 64-65 ላይ የሚገኘውን ምክር ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ከልስ። አዘውትረው በስብሰባ ለሚገኙ ልባዊ ምስጋና አቅርብ።
መዝሙር 87 (195) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 22 (47)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በግንቦት ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል የሚፈልጉ አሁንም ማመልከቻ ማስገባት እንደሚችሉ ግለጽ።
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር ሲሆን ጉባኤው በዚህ ረገድ ሊያሻሽል የሚችልባቸውን መንገዶች በደግነት በመጥቀስ ያቀርባል።
25 ደቂቃ፦ “ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እንዲኖሩን ይፈለጋል።” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ጉባኤው በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በኩል ያለውን እንቅስቃሴ ግለጽ። በዚህ በኩል ጉባኤው ያለውን መልካም ጎን በመጥቀስ አመስግን። የቤተሰብን ጥናት ጨምሮ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በማስጀመርና በማስጠናት በኩል በበለጠ ምን ማድረግ እንደሚቻል ጥቀስ። አንቀጽ 5ን ለቤተሰቡ ቋሚ የቤተሰብ ጥናት ለሚመራ ወላጅ ቃለ መጠየቅ በማድረግ አቅርበው። አንቀጽ 8ን ካነበብክ በኋላ የተዘረዘሩትን ስምንት ነጥቦች አጉላ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በመምራት በኩል ውጤታማ የሆነ አንድ አስፋፊ ሳያስፈልግ ጥናቱን ባለማራዘም ትምህርቱን በሙሉ እንዴት መሸፈን እንደሚቻል እንዲናገር በመጋበዝ አንቀጽ 13ን አብራራ። በጉባኤው ውስጥ ምን ያህል ጥሩ ውጤት እየተገኘ እንዳለ የሚያሳይ አንድ የተመረጠ ተሞክሮ አክል።
መዝሙር 98 (220) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 (48)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በግንቦት ወር ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉትን ስም ዝርዝር ለጉባኤው አንብብ። ጉባኤው ለመስክ አገልግሎት ስብሰባ ያደረገውን ተጨማሪ ዝግጅት ጥቀስ። በቅርብ ለወጡት መጽሔቶች መግቢያ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን አካፍል።—ጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 10ን ተመልከት።
15 ደቂቃ፦ “ክርስቲያን እረኞች የሚያገለግሏችሁ እንዴት ነው?” መጋቢት 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 24-7 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
18 ደቂቃ፦ አስቸጋሪ በሆኑ ክልሎች ውስጥ ስለማገልገል አዎንታዊ አመለካከት ያዙ። አስቸጋሪ በሆነ ክልል ውስጥ ሲያገለግሉ ጥሩ ምላሽ ባለማግኘታቸው ተስፋ ከቆረጡ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ጋር አንድ ሽማግሌ ይወያያል። መጠበቂያ ግንብ 14-109 ከገጽ 19-24 አንቀጽ 4-14 ያለውን አብሯቸው ይከልሳል። በዚህ መጠበቂያ ግንብ ላይ ያሉትን ሐሳቦች በጉባኤው ክልል ውስጥ እንዴት ሊሠሩባቸው እንደሚችሉ አዎንታዊ በሆነ መንገድ ይናገራሉ። ያልተሸፈኑ ክልሎችን ለመሸፈን ያደረጋችሁት ጥረት ያሳየውን እድገት በአጭሩ ጥቀስና አንድ ገንቢ ተሞክሮም ተናገር።
መዝሙር 85 (191) እና የመደምደሚያ ጸሎት።