የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/98 ገጽ 2
  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 8/98 ገጽ 2

የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ነሐሴ 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 66 (155)

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የአገሪቱንና የጉባኤውን የግንቦት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት በሚመለከት ሐሳብ ስጥ። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።

18 ደቂቃ፦ “በነሐሴ ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ማድረግ ይቻል ይሆን?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በነሐሴና በአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ባሉት በእያንዳንዱ ወር በአገልግሎት እንዲካፈሉ ሁሉንም አበረታታ። ሦስተኛውን አንቀጽ አንብብ።

15 ደቂቃ፦ “የሰዎችን አእምሮና ልብ ለመማረክ በብሮሹሮች ተጠቀሙ።” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። እጅግ አስፈላጊ የሆኑትን ቅዱስ ጽሑፋዊ ጉዳዮች ለሰዎች ለማሳወቅ ሲባል ማኅበሩ እስከ አሁን ድረስ ያሳተማቸውን ብሮሹሮች በአጭሩ ጥቀስ። (የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ 1986–1995 ከገጽ 652–3 ያለውን ተመልከት።) በቅርብ ጊዜ የታተሙትን ብሮሹሮች ጥቀስና እያንዳንዱ ብሮሹር በተለይ የማንን ፍላጎት ሊቀሰቅስ እንደሚችል ተወያዩ። በሐምሌ 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 12 ላይ ባሉት ሐሳቦች ተጠቅመህ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ።

መዝሙር 85 (191) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 51 (127)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በነሐሴ ሁሉም በመስክ አገልግሎት ለመካፈል ግብ እንዲያወጡ ሐሳብ አቅርብ። በሐምሌ የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ‘የሚያስፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው’ ከሚለው ላይ ቁልፍ የሆኑ ነጥቦችን ጥቀስ።

15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ፦ “ወጣቶች—የትምህርት ቤት ሕይወታችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ከሚያዝያ 8, 1992 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ከገጽ 17–19 እና ከሐምሌ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 23–26 ላይ ከሰፈሩት ሐሳቦች ተስማሚ የሆኑ ነጥቦችን መርጠህ አቅርብ።

መዝሙር 16 (37) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 71 (163)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በመንገድ ላይ፣ በመናፈሻ ውስጥ ወይም በሌላ ቦታ መሥክረንለት ፍላጎት ያሳየን ሰው ተከታትሎ ለመርዳት ይቻል ዘንድ የግለሰቡን ስምና አድራሻ እንዴት መቀበል እንደሚቻል አጠር ያለ ሐሳብ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። ቆላስይስ 3:23 ጠቅሰህ አንዳችን ሌላውን ለማበረታታት እርስ በርስ የመጠያየቅን አስፈላጊነት ግለጽ።

35 ደቂቃ፦ “አጣዳፊ ለሆነው ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የበለጠ ትኩረት መስጠት” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንቀጽ 5, 10 እና 11⁠ን አንብብ። ጉባኤው መጽሐፍ ቅዱስ በማስጠናት በኩል ምን ያህል እድገት እያደረገ እንዳለ ጨምረህ ተናገር። ጥናት የሚመሩ ሁሉ የማስተማር ችሎታቸውን ይበልጥ ማሻሻል ይችሉ ዘንድ በሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ የወጣውን ትምህርት ደግመው እንዲያነቡ አበረታታ። አባሪው ላይ በሚገኘው በአንቀጽ 5 እና 25 ላይ ተመርኩዘህ ሐሳብ ስጥ።

መዝሙር 80 (180) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 95 (213)

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሐምሌ 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኘውን “ወደ 6,000 ምን ያህል እንጠጋ ይሆን?” የሚለውን ሣጥን ከልስ። የነሐሴ ወር ሊጠናቀቅ የቀረው አንድ ሳምንት ብቻ በመሆኑ ወሩ ከማለቁ በፊት በአገልግሎት እንዲካፈሉ ሁሉንም አበረታታ።

18 ደቂቃ፦ በአቅኚነት አገልግሎት መጽናት የሚቻልበት መንገድ። በመስከረም 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 28–31 ላይ የተመሠረተ ንግግር። ከባድ ችግሮችን በመቋቋም በአቅኚነት አገልግሎት ለቀጠለ(ች) አንድ አቅኚ ቃለ መጠይቅ አድርግ።

15 ደቂቃ፦ በመንግሥት አገልግሎታችን ጥሩ አድርጋችሁ ተጠቀሙ። ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በቅርብ ጊዜ በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጡ ወቅታዊ ሐሳቦችን ለአብነት ያክል በመጥቀስ ያስገኙልንን ጥቅም ግለጽ:- (1) በአገልግሎት አዘውትረን እንድንካፈል የሚያነሳሱ ርዕሶች፤ (2) በቅዱስ አገልግሎት መካፈላችንን እንድንቀጥል የሚያበረታቱ ተሞክሮዎች፤ (3) ምሥራቹን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድናቀርብ የሚረዱ ሐሳቦች፤ (4) ለአገልግሎት ክልላችን ተስማሚ የሆኑ አዳዲስ ጽሑፎች መውጣታቸውን የሚያበስሩ ማስታወቂያዎች፤ (5) የመንግሥቱ እንቅስቃሴ የት እንደደረሰ የሚያሳዩ የአገልግሎት ሪፖርቶች፤ (6) የዓለም አቀፉን ሥራ እድገት የሚያሳዩ ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች፤ (7) ከፊታችን ስለሚጠብቁን መንፈሳዊ ዝግጅቶች የሚገልጹ ማስታወቂያዎችና ፕሮግራሞች፤ (8) ትኩረት ሊደረግባቸው ለሚገቡ ጉዳዮች መልስ የሚሰጡን የጥያቄ ሣጥኖች፤ እንዲሁም (9) ትላልቅ ስብሰባዎችን፣ ልዩ ዘመቻዎችንና ለመንፈሳዊ ፍላጎቶቻችን ዘወትር ንቁ እንድንሆን የሚነግሩን አባሪዎች። የጉባኤው አስፋፊዎች የሚደርሳቸውን እያንዳንዱን እትም እንዲያነቡ፣ በእያንዳንዱ እትም ላይ የሚወጡትን ሐሳቦች ተግባራዊ እንዲያደርጉ፣ በአገልግሎት ስብሰባና በመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ላይ ይዘው እንዲመጡና በሌላ ጊዜ ማንበብ ሲያስፈልጋቸው ደግሞ በቀላሉ እንዲያገኙት በግል ቤተ መጻሕፍታቸው ውስጥ እንዲያስቀምጡት ሁሉንም አበረታታ።

መዝሙር 45 (106) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 31 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 51 (127)

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የነሐሴ የመስክ አገልግሎት ሪፖርት እንዲመልሱ ሁሉንም አስታውሳቸው። ሁሉም ሪፖርቶች ተጠናቅረው ከመስከረም 6 በፊት እንዲላኩ ለማድረግ እያንዳንዱ የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት መሪ በየቡድኑ ያሉትን የእያንዳንዱን ግለሰብ ሪፖርት መቀበል ይኖርባቸዋል። በመስከረም የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። “በአምላክ ስም መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው?” በሚል ጥያቄ ውይይት ሲያደርጉ የሚያሳይ አንድ አጠር ያለ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ለዘላለም መኖር ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 41 አንቀጽ 18 ላይ መልሱን ማግኘት ይቻላል።

15 ደቂቃ፦ “ግንባር ቀደም ሆነው የሚያገለግሉ የበላይ ተመልካቾች—ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች።” ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በንግግር ያቀርበዋል። የሥራ ተግባሮቹን ከገለጸ በኋላ ጉባኤው መንጋውን ለመጠበቅ ከሚሠሩት ሽማግሌዎች ጋር እያደረገ ያለውን ትብብር በአድናቆት ይገልጻል።

18 ደቂቃ፦ ልጃችሁ ትምህርት ቤት የሚገጥሙትን ችግሮች መቋቋም እንዲችል እርዱት። አንድ ሽማግሌ ተማሪ ልጆች ካሏቸው ከሁለት ወይም ከሦስት ወላጆች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። በነሐሴ 8, 1994 እንግሊዝኛ ንቁ! ከገጽ 5–7 ላይ በሰፈረው ሐሳብ መሠረት ልጆችን የሚያጋጥሟቸውን አንዳንድ በጣም የተለመዱ ችግሮች አጠር አድርገው ይጠቅሳሉ። ከዚያም ከገጽ 8–10 ላይ የሰፈሩትን ሐሳቦች በመጠቀም ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ እንዲሁም በወላጆችና በአስተማሪዎች መካከል ጥሩ ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ የሚችሉበትን መንገድ ይወያያሉ።

መዝሙር 54 (132) እና የመደምደምያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ