ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴ፦ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መካከል ማንኛውንም ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በአንድ ብር ማበርከት ይቻላል:- በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም እና የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች። መስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። በሦስት ብር።
◼ ጸሐፊዎችና የሒሳብ አገልጋዮች በቅናሽ ዋጋ የተበረከቱትን ብሮሹሮችና ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ልዩነት እንዲቀነስላቸው መጠየቅ እንዳለባቸው ማስታወስ ይኖርባቸዋል።
◼ በ1999 የአገልግሎት ዓመት የምትጠቀሙባቸው በቂ መጠን ያላቸው ቅጾች ለእያንዳንዱ ጉባኤ በመላክ ላይ ናቸው። እባካችሁ እነዚህን ቅጾች በአግባብ ተጠቀሙባቸው። ለታቀደላቸው ዓላማ ብቻ መዋል ይኖርባቸዋል።
◼ እያንዳንዱ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18-AM) ይደርሱታል። በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎች የሚቆጠሩበትን ቀን ለመወሰን የጉባኤው ጸሐፊ በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ የጽሑፍ አገልጋዩን ማነጋገር ይኖርበታል። በጉባኤው ያሉት ጽሑፎች ሁሉ አንድ በአንድ መቆጠር አለባቸው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጹ ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ የመጽሔቶች ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ ማግኘት ይቻላል። እባካችሁ ከመስከረም 6 በፊት ዋናውን ቅጂ ለማኅበሩ ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ በፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛው ቅጂ ጊዜያዊ መሥሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ጸሐፊው አብሮ መቁጠር ያለበት ሲሆን ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ደግሞ ተሠርቶ ያለቀውን ቅጽ መመርመር ይኖርበታል። ጸሐፊውና ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በቅጹ ላይ ይፈርማሉ።
◼ ጉባኤዎች መስከረም በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ1999 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ ማዘዝ ይኖርባቸዋል።
◼ የረዳት አቅኚነት ማመልከቻ ሞልተው በመስክ አገልግሎት ግን 60 ሰዓት ማሳለፍ ያልቻሉ እንደ ረዳት አቅኚ ሊቆጠሩ ይችሉ እንደሆነና እንዳልሆነ በርካታ ጸሐፊዎች ጥያቄ አቅርበዋል። መልሱ ረዳት አቅኚ ሆነው ሊቀጠሩ ይችላሉ የሚል ሲሆን ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ማመልከቻ ያስገቡ ሁሉ ያገኙትን ሹመት በቁም ነገር በመመልከት 60 ወይም ከዚያ የሚበልጥ ሰዓት ለመመለስ የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል።—ማቴ. 5:37፤ ሥራ 18:5
◼ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ ለዘወትር አቅኚነት አገልግሎት የሚደርሷቸውን ማመልከቻዎች ሳይዘገዩ መመልከት ይኖርባቸዋል። አመልካቹ የሚፈለግበትን የአገልግሎት ሰዓት ማሟላት ይችል እንደሆነና እንዳልሆነ ለማረጋገጥ ሲባል የአገልግሎት ኮሚቴው ማመልከቻውን ይዞ መቆየት አይገባውም። ማኅበሩ ማመልከቻው የደረሰው አስፋፊው የአቅኚነት አገልግሎቱን ለመጀመር ካሰበው ቀን በኋላ ከሆነ ማኅበሩ ወዲያው ቀኑን ሊለውጠው ይችላል። አጥጋቢ ምክንያቶች እስከሌሉ ድረስ ላለፈ ወር የሹመት ጥያቄ ማቅረብ በማኅበሩ ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም። እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ካሉ ከማመልከቻው ጋር ደብዳቤ መላክ ይኖርበታል።—የነሐሴ 1986 የመንግሥት አገልግሎታችን (የእንግሊዝኛ) አባሪ አንቀጽ 24–6ን ተመልከቱ።