ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
ኢትዮጵያ፦
▪ አሁንም መጽሔቶቻችንን ለማንበብ የሚፈልጉ በርካታ ሰዎች አሉ። በደብረ ዘይት የሚገኙ ሁለት የዘወትር አቅኚዎች በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ በድምሩ 196 መጽሔቶችን አበርክተዋል።
▪ በጊምቢና በአዲስ አበባ ፍልውኃ አዳዲስ የመንግሥት አዳራሾች ለይሖዋ አምልኮ ተወስነዋል።
▪ በተከታታይ ሲደረግ የቆየው የወረዳ ስብሰባ 8,643 በሚያክል የተሰብሳቢ ቁጥር ሲጠናቀቅ አሥራ ስድስቱ የልዩ ስብሰባ ቀናት በጠቅላላው 8,464 የሚያክል ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር አስመዝግበዋል።
▪ በሚያዝያ በተደረገው መጽሔት የማበርከት ዘመቻ ብዙ ጉባኤዎች አመርቂ ውጤት አግኝተዋል። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች የግል ቤተ መጻሕፍት እንዲያደራጁ በመርዳትና መጽሔት የሚበረከትባቸው ልዩ ቀናት በማዘጋጀት የአዲስ አበባ አዋሬ ጉባኤ የተሳካ ውጤት አግኝቷል። አንዲት አቅኚ በአንድ ቀን ውስጥ 42 መጽሔቶችን አበርክታለች። በሚያዝያ ወር ግማሽ የሚሆነው የጉባኤው አስፋፊ አቅኚ ሆኖ አገልግሏል። በሚያዝያ ወር በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ አምስት ጉባኤዎች እያንዳንዳቸው ከ1,000 የሚበልጡ መጽሔቶች አበርክተዋል።
▪ ሃያ አራት አስፋፊዎች ያሉት የጊምቢ ጉባኤ በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የቀረበውን ሐሳብ ተከትለው በመሥራታቸው በጥር ወር ከ200 የሚበልጡ መጽሐፎችን እንዳበረከቱ ጉባኤው ሪፖርት አድርጓል። በእጃቸው ያለው ሲያልቅ ከጎረቤት ጉባኤ ተጨማሪ መጽሐፎች ወሰዱ። በውጤቱም ጉባኤው በሚያዝያ ወደ 500 የሚጠጉ ተመላልሶ መጠየቆች እንዳደረገ ሪፖርት አድርጓል።