የታኅሣሥ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ታኅሣሥ 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 41 (89)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሦስት ለዘላለም መኖር መጻሕፍት ለማበርከት የነበራቸው ግብ ተሳክቶላቸው እንደሆነ ሁሉንም ጠይቅ። በዘመቻ ዋጋ ማለትም በሦስት ብር ማበርከት የሚቻልባቸውን አማራጮች ጥቀስ። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
18 ደቂቃ፦ “ደጋግመን መሄድ አለብን።” ጥያቄና መልስ። ሕዝቅኤል 3:17–19ን ጠቅሰህ የማስጠንቀቂያውን መልእክት በማሰማት የመቀጠል ኃላፊነታችንን በማጉላት አጠር ያለ ሐሳብ ስጥ። ጉባኤያችሁ የአገልግሎት ክልሎችን በመሸፈን ረገድ ስላከናወነው ሥራና ከቤት ወደ ቤት በማገልገል ስለሚያደርገው ተሳትፎ ጥቀስ።
17 ደቂቃ፦ “አዲሲቱ ዓለም ትርጉምን ማበርከት።” ክፍሉን የሚያቀርበው ወንድም ከሁለት ወይም ሦስት ብቃት ያላቸው አስፋፊዎች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ” ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 327–31 ያሉትን ተስማሚ ነጥቦች ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 56 (135) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 7 (19)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በዓለማዊ በዓላት ወቅት ለሚሰነዘሩልን ሰላምታዎች እንዴት በዘዴ መልስ መስጠት እንደምንችል ሐሳብ ስጥ። ጉባኤው ታላቅ ሰው ወይም ታላቁ አስተማሪ የተባሉት መጻሕፍት ካሉት በበዓል ወቅቶች እንዴት ውጤታማ በሆነ መንገድ በአገልግሎት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል ግለጽ። ለበዓላቱ ቀናት የተደረጉትን ልዩ የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶች ግለጽ።
15 ደቂቃ፦ “ግንባር ቀደም ሆነው የሚያገለግሉ የበላይ ተመልካቾች—የመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪ።” በመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪው የሚቀርብ ንግግር። የጥናቱ መሪ ምን ኃላፊነቶች እንዳሉበት እንዲሁም ጥናቱ ሕያው፣ እውቀት ሰጪና በመንፈሳዊ የሚገነባ እንዲሆን ሁሉም ተሰብሳቢዎች ምን ማድረግ እንደሚችሉ ይገልጻል።—አገልግሎታችን ገጽ 67ን ተመልከት።
20 ደቂቃ፦ “የተለየን መሆናችንን ማየት ይችላሉ።” ጥያቄና መልስ። ልዩ የሚያደርገንን እያንዳንዱን ባሕርይ በአጭሩ ከልስ። እነዚህ ነጥቦች ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ወደ ድርጅቱ ለመምራትና ሕይወታቸውን በእውነት የሚመሩ ከሆነ እንዴት ክርስቲያናዊ ባሕርያትን ሊያፈሩ እንደሚችሉ ለማስረዳት ሊያገለግል እንደሚችል ጥቀስ።
መዝሙር 62 (146) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 71 (163)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ለዘላለም መኖር የተባለው መጽሐፍ ለአንድ ጎረቤት ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። በአዲሱ ዓመት ጉባኤያችሁ የስብሰባ ሰዓቱን የሚቀይር ከሆነ ሁሉም በአዲሱ የመሰብሰቢያ ሰዓት ዘወትር በስብሰባ ላይ እንዲገኙ በደግነት አበረታታ። የጉባኤ አስፋፊዎች የተደረገውን ለውጥ ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻቸውና ለሌሎች ፍላጎት ላላቸው ሰዎች እንዲያሳውቁ አስታውሳቸው። ሁሉም አስፋፊዎች የመንግሥት አገልግሎታችን የግል ቅጂዎቻቸውን በተለይ ደግሞ አባሪዎቹን እንዲያስቀምጡ አበረታታቸው። ወደፊት እነዚህን ጽሑፎች መልሰን እንመለከታቸው ይሆናል።
12 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
25 ደቂቃ፦ “ሕይወታችሁን በይሖዋ አገልግሎት ዙሪያ ገንቡ።” ጥያቄና መልስ። በየሳምንቱ የማያቋርጥና ቋሚ የሆነ የመስክ አገልግሎት ፕሮግራም በመከተል ለተሳካላቸው አንድ ነጠላ እና አንድ የቤተሰብ ራስ ቃለ ምልልስ አድርግ። ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ቅድሚያ መስጠት ምን ዓይነት የግል ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠይቅ እንዲናገሩ አድርግ።
መዝሙር 83 (187) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 67 (156)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የታኅሣሥ ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስባቸው። በጉባኤው የሚገኙትን በጥር የሚበረከቱ ጽሑፎች አሳይ። አስፋፊዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀኖች የሚያበረክቷቸውን ጽሑፎች እንዲወስዱ አበረታታ። እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
12 ደቂቃ፦ “ከ1999 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ተጠቀሙ።” በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። “ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም” ላይ ያሉትን ምዕራፎች በየሳምንቱ ተከታትለው በማንበብ ስላገኙት ጥቅም አንዳንድ አስፋፊዎች እንዲናገሩ አድርግ። ሁሉም የአምላክን ቃል በየቀኑ እንዲያነቡ አበረታታ።
18 ደቂቃ፦ ስንሞት ምን እንሆናለን? ከተባለው አዲስ ብሮሹር ጥቅም ማግኘት። ከብሮሹሩ ይዘት ጎላ ያሉ ነጥቦች ከልስ። ብሮሹሩ ነፍስ አትሞትም የሚለውን ትምህርት ምንጭ በመግለጽ ይህ እምነት በዓለም ላይ ላሉ አብዛኞቹ ሃይማኖቶች መሠረታዊ ትምህርት ሊሆን የቻለበትን መንገድ ያብራራል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ነፍስ፣ ለምን እንደምንሞት፣ ሙታን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ ከሞት በኋላ ስላለው የሕይወት ተስፋ እንዲሁም ስለ እነዚህ ጉዳዮች እውነቱን ማወቅ ያለብን ለምን እንደሆነ ማራኪ በሆነ መንገድ ይገልጻል። ሁሉም ይህን ብሮሹር ማንበብ ይኖርባቸዋል። በእያንዳንዱ ክፍል መጀመሪያ ላይ ከሚገኙት የሰዎችን ፍላጎት ለመቀስቀስ ልንጠቀምባቸው ከምንችላቸው 40 የሚያክሉ ሥዕላዊ መግለጫዎችና አስተያየቶች ውስጥ አንዳንዶቹን ጥቀስ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምሩ ሐሳብ ስናቀርብ የመጨረሻውን ክፍል እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል አስረዳ። አስፋፊዎች አዲሱን ብሮሹር በአገልግሎት እንዴት ሊጠቀሙበት እንዳሰቡ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
መዝሙር 87 (195) እና የመደምደሚያ ጸሎት።