የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/98 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 12/98 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ታኅሣሥ፦ አማርኛ፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ፤ እንግሊዝኛ፦ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም። ጥርና የካቲት፦ በጉባኤው የሚገኝ ከ1985 በፊት የታተመ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ፣ በሦስት ብር። እነዚህ መጻሕፍት የሌሏቸው ጉባኤዎች መንግሥትህ ትምጣ፣ በሕይወት ተርፎ ወደ አዲስ ምድር መግባት ወይም እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት የተባሉትን መጻሕፍት በሦስት ብር ማበርከት ይችላሉ። መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል።

◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው በታኅሣሥ 1 ወይም ከዚያ ብዙ ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።

◼ እሁድ፣ ሚያዝያ 18 የሚቀርበው ልዩ የሕዝብ ንግግር ርዕስ “ከአምላክም ሆነ ከሰዎች ጋር እውነተኛ ወዳጅነት መመሥረት” የሚል ይሆናል። አስተዋጽኦው ይላክላችኋል።

◼ በ1999 የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1 ቀን ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። በ2000 የሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ደግሞ የሚውለው ረቡዕ፣ ሚያዝያ 19 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው። በዓሉ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው እንደመሆኑ መጠን የሽማግሌዎች አካል በመታሰቢያው በዓል ላይ ንግግር የሚሰጠውን ወንድም በሚመርጥበት ወቅት በየዓመቱ አንድ ወንድም ብቻ ከመጠቀም ወይም በየተራ ከማድረግ ይልቅ የተሻለ ብቃት ያለውን ሽማግሌ መምረጥ ይኖርበታል። ለየት ያለ አሠራር የሚኖረው ንግግሩን መስጠት የሚችል ቅቡዕ የሆነ ብቃት ያለው ሽማግሌ በሚኖርበት ጊዜ ነው።

◼ በአዲስ አበባ ወይም በአቅራቢያው የሚገኙ አስፋፊዎች መስማት የተሳናቸው ሰዎች ሲያገኙ የሰዎቹን ስምና አድራሻ ለጉባኤያቸው ጸሐፊ እንዲሰጡ እንጠይቃለን። ጸሐፊውም ስምና አድራሻውን ለአዲስ አበባ ሰሜን ጉባኤ፣ የመ. ሣ. ቁ. 7525፣ አዲስ አበባ በሚል አድራሻ ይልከዋል።

◼ አምስት ቅዳሜና እሁዶች ያሉት የጥር ወር ለብዙዎች በረዳት አቅኚነት ለመካፈል አመቺ ጊዜ ይሆናል።

◼ በዚህ ዓመት በሚደረገው ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ውስጥ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆነው ለማገልገል ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው የዘወትር አቅኚዎች ወይም ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መረጃዎች በመስጠት እስከ ጥር 20, 1999 ድረስ በትልቅ ወረቀት ጽፈው ሊልኩልን ይገባል:- 1) ስም፤ 2) ዕድሜ፤ 3) የጥምቀት ቀን፤ 4) ነጠላ ወይም ያገባ መሆኑንና የሚያስተዳድረው ቤተሰብ ብዛት፤ 5) ከመቼ እስከ መቼ ማገልገል እንደሚችል (መጋቢት—ግንቦት?)፤ 6) የሚያውቃቸው ቋንቋዎች፤ 7) አመልካቹ አዘውትሮ ከቤት ወደ ቤት የሚያገለግል መሆን አለመሆኑን። ከዚያም የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አመልካቹ ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ 1998 የነበረውን አማካይ ሪፖርት እንዲሁም የድጋፍ ሐሳቡንና ፊርማውን አስፍሮ ይልካል።

◼ አዲስ ጽሑፍ:- ጥር—መጋቢት 1999 እትም ጀምሮ ንቁ! መጽሔት በትግርኛ ቋንቋ በዓመት አራት ጊዜ ይታተማል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ