“ማንበብና መጻፍ ለመማር ትጉ”
ይህ የንባብና የጽሑፍ ችሎታን ለማሻሻል እንዲረዳ ታስቦ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀው አዲስ ብሮሹር ርዕስ ነው። በብዙ ጉባኤዎች ውስጥ በዚህ ረገድ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው አስፋፊዎችና የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ስላሉ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የበላይ ተመልካቾች ጉባኤው እነዚህን ሰዎች ለመርዳት ምን ማድረግ እንደሚችል እንዲያስቡበት ልናበረታታቸው እንወዳለን። (1 ጢሞ. 4:13 የ1980 ትርጉም) ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ለማስተማር ጊዜ ያላቸውና ፈቃደኛ የሆኑ ወንድሞችና እህቶች ይኖሩ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ አስፋፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻቸውን ያስተምራሉ። እንዲህ ማድረጋቸው የሚያስመሰግን ነው። በዚህ ረገድ የሚደረገውን ጥረት በጉጉት የምንከታተል ሲሆን ጉባኤው ወይም አስፋፊዎች በግላቸው ምን ያህል ሰዎች ማንበብ እንዲችሉ እንደረዱ የሚገልጹ ሪፖርቶችን ብናገኝ ደስ ይለናል። ይህን መረጃ የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ሲጎበኛችሁ ለእርሱ ልትሰጡት ትችላላችሁ።