የየካቲት የአገልግሎት ስብሰባዎች
የካቲት 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 56 (135)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የጥር ወር ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስብ።
17 ደቂቃ፦ “በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች የቤተሰብ ደስታ የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ።” አንድ ሽማግሌ ጥሩ ችሎታ ካላቸው ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር መከተል መሆኑን ሌሎች እንዲያስተውሉ መርዳትን ግብ በማድረግ ላይ አተኩር። (የቤተሰብ ደስታ ገጽ 10-12ን ተመልከት።) ከተዘረዘሩት አቀራረቦች አንዱን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ለተመላልሶ መጠየቅ ቀጠሮ መያዝ የሚቻልበትን መንገድ አሳይ።
18 ደቂቃ፦ “አዲሱን ሰው ልበሱ።” ኤፌሶን 4:20-24ን በማብራራት የሚቀርብ ንግግር። (የመጋቢት 1, 1993 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 14-18, አንቀጽ 4-17ን ተመልከት።) አሮጌውን ሰው አውልቀን አዲሱን የምንለብሰው እንዴት እንደሆነ አብራራ።
መዝሙር 2 (4) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 4 (8)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
13 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ “ታላቁ ፈጣሪያችን ስለ እኛ ያስባል!” ጥያቄና መልስ። የአምላክን ሕልውና የሚጠራጠሩ ወይም የሚክዱ ሰዎችን ለመርዳት ፈጣሪ (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ወይም አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለውን ብሮሹር (ክፍል 3) እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል ግለጽ። መጽሐፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመምራት የተዘጋጀ ባይሆንም እንኳ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን እንዲመረምሩ ለማነሳሳት ውጤታማ መሣሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። (ፈጣሪ የተባለውን መጽሐፍ ከገጽ 189-91 ወይም አምላክ ስለ እኛ ያስባልን? የተባለውን ብሮሹር ክፍል 4 ተመልከት።) አስፋፊዎች ስለ መጽሐፉ ያላቸውን የግል አስተያየት እንዲናገሩና ለሌሎች በማበርከት ረገድ ያገኙት ተሞክሮም ካለ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 88 (200) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 9 (26)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “ማንበብና መጻፍ ለመማር ትጉ” የሚለውን አቅርብ።
18 ደቂቃ፦ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በመመዝገባችን የተጠቀምነው እንዴት ነው? የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት ያቀርበዋል። የትምህርት ቤቱ ዓላማ በሕዝብ ተናጋሪነት ረገድ ሥልጠና መስጠት ብቻ አይደለም። በቀጥታ ጥቅም የምናገኝባቸው ሌሎች መንገዶችም አሉ። (ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ከገጽ 12-13 ተመልከት።) ከሌሎች ሰዎች ጋር በተሻለ መንገድ የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ የምንችልበትን መንገድ እንማራለን። በግልጽ፣ ተረጋግተንና ተማምነን መናገርን ተምረናል። እምነታችንን በሚመለከት ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠትና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ውሳኔዎቻችንን በማስረዳት ረገድ ችሎታችን ይዳብራል። የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችን ይጨምራል፤ ይህም ለሌሎች በመመሥከሩ ሥራ ይበልጥ ውጤታማ እንድንሆን ይረዳናል። ስህተቶቻችንን ማመንንና ምክር መቀበልን እንማራለን፤ ይህ ደግሞ ከሌሎች ጋር ይበልጥ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንድንኖር ያስችለናል። ትምህርት ቤቱ የሚሰጠን አጠቃላይ ሥልጠና የአምላክ አገልጋዮች እንደመሆናችን መጠን ‘ብቃታችንን’ ይዘን እንድንቀጥል ይረዳናል።—2 ቆሮ. 3:5, 6
17 ደቂቃ፦ “የቤተሰብ አባላት የተሟላ ተሳትፎ ማድረግ የሚችሉበት መንገድ—በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት።” በአንድ የቤተሰብ አባላት በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብና ጥናትን በሚመለከት በግንቦት 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 14-15 እና በጥቅምት 15, 1992 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 16-17 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች በምን መልኩ እየሠሩባቸው እንዳሉ ያጤናሉ።
መዝሙር 27 (57) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 21 (46)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ ትምህርትን በዓላማ መከታተል። በሽማግሌ የሚቀርብ። የሚከተሉትን የመጠበቂያ ግንብ አንቀጾች እያነበብክ መጽሔቱ ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ተጠቅመህ አብራራ:- የካቲት 1, 1996 ገጽ 14 አንቀጽ 21-24 እና ታኅሣሥ 1, 1996 ገጽ 17-19 አንቀጽ 9-15።
20 ደቂቃ፦ “ደቀ መዝሙር በማድረጉ ሥራ ደስታ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?” በየካቲት 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 19-22 ላይ የተመሠረተ ንግግር።
መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።