የመጋቢት የአገልግሎት ስብሰባዎች
መጋቢት 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 13 (33)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ልዩ የአገልግሎት ክልሎችን የመሸፈን ዘመቻችን መጀመሩን አስታውሳቸው። በዚህ የአገልግሎት ዓመት እስካሁን ድረስ ምን ያህል የአገልግሎት ክልሎች ሳይሸፈኑ እንደቀሩ የክልል አገልጋዩን ጠይቅ። እነዚህን ክልሎች ለመሸፈን ምን ዝግጅቶች እንደሚደረጉ ተናገር። ወንድሞች በተደጋጋሚ ባልተሸፈኑ ክልሎች ውስጥ የቆዩ መጽሔቶችንና ትራክቶችን እንዲጠቀሙ አበረታታ።
17 ደቂቃ፦ “በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ።” ጥያቄና መልስ። ከየካቲት 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 11-12 አንቀጽ 10-14 ላይ ተጨማሪ ሐሳቦች አቅርብ። ይሖዋ ለእኛ ያለው ታላቅ ፍቅር ቤዛ እንዲያዘጋጅልን ያነሳሳው እንዴት እንደሆነ አጉልተህ ግለጽ።
16 ደቂቃ፦ በሚያዝያና በግንቦት ረዳት አቅኚ እንድንሆን ግድ የሚሉን ምክንያቶች። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት ያቀርበዋል። ሁሉም ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገልን በጥሞና እንዲያስቡበት ይመክራል። በጥር 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 2 ላይ በቀረበው ሐሳብ መሠረት የዘወትርና ረዳት አቅኚዎች እንዲያሟሉ በሚጠበቅባቸው ሰዓት ላይ የተደረገውን ማሻሻያ ከልስ። ይህ ማሻሻያ ተጨማሪ ቁጥር ያላቸው ወንድሞች በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የመካፈል መብት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። ለክርስቶስ መሥዋዕት ያለን አድናቆት ለሌሎች በመስበክ ረገድ ጥረታችንን እንድንጨምር ግድ የሚለን እንዴት እንደሆነ ግለጽ። (2 ቆሮ. 5:14, 15) በዚህ ዓመት የመታሰቢያው በዓል በሚያዝያ ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ ይውላል። ሁሉም የመንግሥቱ አስፋፊዎች ወሩን በሙሉ ተጨማሪ የአገልግሎት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ምንኛ ጥሩ ማበረታቻ ይሆናቸዋል! በየካቲት 1997 እና በመጋቢት 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪዎች ላይ የረዳት አቅኚነት አገልግሎትን በሚመለከት ከወጡት ነጥቦች ውስጥ ጎላ ያሉትን መርጠህ አቅርብ። የቀረቡትን የናሙና ፕሮግራሞች በመከተል ፕሮግራም ማዘጋጀት የሚቻልባቸውን መንገዶች ተናገር። ከሌሎች ጋር በአገልግሎት ለመሳተፍ በቂ አጋጣሚ የሚሰጡትን የጉባኤውን የአገልግሎት ዝግጅቶች ግለጽ። አስፋፊዎች ስብሰባው እንዳበቃ የረዳት አቅኚነት ማመልከቻ ቅጽ እንዲወስዱ አበረታታ።
መዝሙር 24 (50) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 28 (58)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
20 ደቂቃ፦ “እንዲመጡ ጋብዟቸው።” ጥያቄና መልስ። ፍላጎት ያሳዩትን አዲሶች ምንጊዜም ወደ ጉባኤ ስብሰባዎች የመጋበዝን አስፈላጊነት አጉላ። እውቀት መጽሐፍ ገጽ 159 አንቀጽ 20 እና ገጽ 162-3 አንቀጽ 5-8 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በመጠቀም ፍላጎት ካሳየ ሰው ጋር ውይይት ሲደረግ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችና ሌሎች ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ሚያዝያ 1 በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ለመርዳት ሁሉም ልዩ ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ። አንድ የመጋበዣ ወረቀት አሳይና ውጤታማ በሆነ መንገድ ልንጠቀምበት የምንችልበትን መንገድ ግለጽ። በዚህ ሳምንት ሁሉም የመታሰቢያውን በዓል የመጋበዣ ወረቀት ማደል መጀመር አለባቸው።
15 ደቂቃ፦ “የቤተሰብ አባላት የተሟላ ተሳትፎ ማድረግ የሚችሉበት መንገድ—በጉባኤ ስብሰባዎች።” አንድ ቤተሰብ በውይይት ያቀርበዋል። በርዕሱ በቀረቡት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ሐሳብ ሲሰጡ በቤተሰብ መልክ ለስብሰባዎች መዘጋጀት በሚችሉበት መንገድ ላይ ይወያያሉ። በጉባኤ ተሳትፎ ለማድረግ አንዳቸው ሌላውን መርዳት የሚችሉበትን መንገድና ቤተሰቡ ስብሰባዎች ላይ በሰዓቱ ለመድረስ ምን ማድረግ እንዳለበት ይወያያሉ።
መዝሙር 29 (62) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 26 (56)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “የጉባኤ አገልጋዮች ጠቃሚ አገልግሎት ያበረክታሉ።” ጥሩ ችሎታ ያለው አንድ የጉባኤ አገልጋይ በንግግር ያቀርበዋል። አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 57-9 ላይ የሚገኙትን ዋና ዋና ነጥቦች ከልስ። የጉባኤው አገልጋዮች ጉባኤውን ለመርዳት ጉባኤያችሁ ውስጥ ምን እንደሚያከናውኑ ግለጽ።
20 ደቂቃ፦ ከ1999 የዓመት መጽሐፍ መጠቀም። በአንድ ባልና ሚስት መካከል የሚደረግ ውይይት። ባልየው ለመጀመሪያ ጊዜ የዓመት መጽሐፍ በመጽሐፍ መልክ የተዘጋጀው በ1927 መሆኑንና ከ70 ለሚበልጡ ዓመታት ዓለም አቀፉን የይሖዋ ምሥክሮች ሪፖርት ይዞ ሲወጣ እንደቆየ ይገልጻል። ገጽ 31 ላይ የሚገኘው “የ1998 አጠቃላይ ድምር” የሚለውን ክፍል ጎላ ያሉ ነጥቦች ይከልሳሉ። ከገጽ 3-5 ላይ በሚገኘው “የአስተዳደር አካል ደብዳቤ” ላይ ከተወያዩ በኋላ የተሰጠውን ማበረታቻ በሥራ ሊያውሉ በሚችሉበት መንገድ ላይ ሐሳብ ይለዋወጣሉ።
መዝሙር 65 (152) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 70 (162)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉትን ወንድሞች ስም ዝርዝር አንብብ። አሁንም ማመልከቻ ለማስገባት ጊዜው አለማለፉን ተናገር። ለሚያዝያ የታቀዱትን የመስክ ስምሪት ስብሰባ ፕሮግራሞች በሙሉ ዘርዝር። ሁሉም ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—1999 በተባለው ቡክሌት እንዲሁም የ1999 ቀን መቁጠሪያ ላይ በሰፈረው መሠረት ከመጋቢት 27-ሚያዝያ 1 ድረስ የመታሰቢያ በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም እንዲከታተሉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ ለመታሰቢያው በዓል ተዘጋጁ። ንግግር። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻቸውና ሌሎች ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ለመርዳት ሁሉም ዕቅድ ማውጣት አለባቸው። በስብሰባው ላይ የሚገኙ አዳዲስ ሰዎች ከቂጣውና ከወይኑ ማን መካፈል እንዳለበት ወይም ይህ የበዓሉ መከበር ያለውን ጠቀሜታ አይረዱ ይሆናል። በሚያዝያ 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 6-8 ላይ የቀረበውን ሐሳብ በመከለስ አንድን ፍላጎት ያሳየ አዲስ ሰው የዚህን በዓል ትርጉምና ዓላማ እንዲገነዘብ እንዴት ልንረዳው እንደምንችል ግለጽ። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ከከለስክ በኋላ ጉባኤው ያደረገውን የመታሰቢያ በዓል ዝግጅቶች በመግለጽ ደምድም።
20 ደቂቃ፦ ስንሞት ምን እንሆናለን? አንድ ሽማግሌ ብሮሹሩ የያዘውን ቁም ነገርና እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል ከሁለት ወይም ሦስት ብቃት ያላቸው አስፋፊዎች ጋር ይወያያል። ወደፊት ብሮሹሩን በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ ስናጠናው የተሻለ ትውውቅ ይኖረናል። እስከዚያው ግን በመስክ አገልግሎት ላይ ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተጠቀምንበት ነው? ቀጥሎ ባሉት ነጥቦች ላይ ይወያያሉ:- ይህ ርዕስ የብዙ ሰዎችን ትኩረት የሚስበው ለምንድን ነው? ከሐሰት ሃይማኖታዊ ትምህርቶች በተለየ መንገድ ይህ ብሮሹር ጎላ አድርጎ የሚያቀርበው ተስፋ ምንድን ነው? በኋላው ሽፋን ላይ ባሉት ጥያቄዎች ተጠቅመን የሰዎችን ፍላጎት ማነሳሳት የምንችለው እንዴት ነው? ይህን ብሮሹር ለማበርከት የሚያስችሉን ምን ምን አጋጣሚዎች አሉ? በገጽ 27 አንቀጽ 14 ላይ ያሉትን ጥቅሶች በመጠቀም አንድ አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ሁሉም በዚህ ብሮሹር ጥሩ አድርገው ለመጠቀም ንቁዎች እንዲሆኑ አበረታታ።
መዝሙር 42 (92) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 80 (180)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የመጋቢት የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስባቸው። በሚያዝያ የምናበረክተው መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ይሆናል። በቅርብ የወጡትን መጽሔቶች አሳይ፣ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚችሉትን ርዕሶች ጥቀስ እንዲሁም አንዳንድ የመወያያ ነጥቦች ተናገር። ሁሉም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ሊይዙና ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ሊጠቀሙበት ይገባል። የጥያቄ ሣጥን።
12 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
18 ደቂቃ፦ ምክር ሲሰጠን ምን ዓይነት ዝንባሌ ልንይዝ ይገባል? በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ሁላችንም ዝንባሌን፣ ባሕርይን፣ ጓደኝነትን ወይም በጉባኤ እንቅስቃሴዎች የምናደርገውን ተሳትፎ በተመለከተ ምክር ይሰጠናል። አንዳንድ ጊዜ ምክሩን ላለመቀበል እናንገራግር ወይም በተሰጠን ምክር ቅር እንሰኝ ይሆናል። ምክርን ተቀብሎ በሥራ ለማዋል ፈቃደኛ መሆን ለመንፈሳዊ ደህንነታችን ወሳኝ ሊሆን ይችላል። የሚሰጠንን ምክር የመቀበልንና የማድነቅን አስፈላጊነት ጎላ አድርገው የሚገልጹ ምክንያቶችን ጥቀስ።—የሚያዝያ 1, 1987 መጠበቂያ ግንብ (እንግሊዝኛ) ገጽ 27-30ን ተመልከት።
መዝሙር 4 (8) እና የመደምደሚያ ጸሎት።