ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያና ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ነጠላ ቅጂዎችና ኮንትራቶች። ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ለማበርከት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር አዘጋጅታችሁ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሰኔ፦ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች።
◼ በሚያዝያና በግንቦት ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል የሚፈልጉ አስፋፊዎች ከወዲሁ ሊያስቡበትና ማመልከቻዎቻቸውን ቀደም ብለው ሊሰጡ ይገባል። እንዲህ መደረጉ ሽማግሌዎች አስፈላጊ የሆኑ የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶች እንዲያደርጉና በቂ መጽሔቶችና ሌሎች ጽሑፎች እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል። በረዳት አቅኚነት እንዲያገለግሉ የተፈቀደላቸው በሙሉ ስም ዝርዝራቸው ለጉባኤው መነበብ አለበት።
◼ በመጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙ ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ ለጉባኤው አስታውቁ።
◼ የመታሰቢያው በዓል ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1, 1999 ይከበራል። ጉባኤያችሁ ሐሙስ ዕለት ስብሰባ የሚያደርግ ከሆነና የመንግሥት አዳራሹ ደግሞ በሳምንቱ ቀኖች ውስጥ ነጻ ከሆነ ስብሰባው ወደ ሌላ ቀን መዛወር አለበት። እንዲህ ማድረግ የማይቻል ከሆነና የአገልግሎት ስብሰባችሁ የሚነካ ከሆነ ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑት ክፍሎች በሌላ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ሊካተቱ ይችላሉ።
◼ ጉባኤ የሚሰበሰቡ ሁሉ የግል ኮንትራታቸውን ጨምሮ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች ኮንትራት ሲያስገቡም ሆነ ሲያሳድሱ መላክ ያለባቸው በጉባኤ በኩል ነው።
◼ ማኅበሩ አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ማኅበሩ ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ነገሮች ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማስታወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። በልዩ ትእዛዝ የሚገኙት የትኞቹ ጽሑፎች እንደሆኑ እባካችሁ አስታውሱ።
◼ በወላይትኛ የሚዘጋጅ የመንግሥት አዳራሽ ምልክት በሚከተለው መንገድ መጻፍ አለበት:- YIHOWAA MARKKATU KAWOTETTA ADDARAASHSHAA. በሲዳምኛ የሚዘጋጅ የመንግሥት አዳራሽ ምልክት በሚከተለው መንገድ መጻፍ አለበት:- YIHOOWU FARCI’RAASINE MANGISTETE HARA.
◼ አሁንም እርዳታ የሚያስፈልጋቸውና ከእርዳታ መዋጮ ሒሳባችን ተጠቃሚ የሆኑ አንዳንድ ወንድሞች አሉ። በርካታ ጉባኤዎች ለዚህ ዓላማ የሚውል የተለየ የመዋጮ ሣጥን ስለሌላቸው ለእርዳታ ሒሳቡ የሚደረጉ መዋጮዎችን ለሒሳብ አገልጋዩ በደረሰኝ መስጠት ወይም “እርዳታ” የሚል ጽሑፍ ባለበት ፖስታ መዋጮ ሣጥኑ ውስጥ መጨመር ይቻላል። ለእርዳታ ሒሳቡ የሚውለው መዋጮ በS-20 ገንዘብ መላኪያ ቅጽ ላይ ለብቻው መጻፍ አለበት።
◼ የአንዳንድ ጉባኤዎች የመዋጮ ሣጥኖች ገንዘብ መክተቻ በጣም ጠባብ ስለሆነ ወንድሞች አስተዋጽኦ ለመክተት እንደሚቸገሩ ተስተውሏል። የሚቻል ከሆነ ቀዳዳውን ሰፋ ማድረጉ ጥሩ ይሆናል።