የሚያዝያ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ሚያዝያ 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 89 (201)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የአገልግሎት ክልሎችን ለመሸፈን ባደረግነው ልዩ ዘመቻ ስለተደረገው እድገት ሪፖርት አድርግ እንዲሁም አሁንም መሸፈን ያለባቸው የትኞቹ ክልሎች እንደሆኑ ጥቀስ። በተጨማሪም በመታሰቢያው በዓል ላይ ለተገኙ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምሩ በመጋበዝ ጥሩ ክትትል እንዲያደርጉላቸው አበረታታ። “ፈጣሪ የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት እንችላለን?” የሚለውን አቅርብ። ሚያዝያ 18 የሚቀርበውን ልዩ የሕዝብ ንግግር እንዲያዳምጡ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ጋብዙ። የንግግሩ ርዕስ “ከአምላክ እና ከሰዎች ጋር እውነተኛ ወዳጅነት መመሥረት” የሚል ነው።
15 ደቂቃ፦ “ምሥራቹን በጉጉት ስበኩ።” ትምህርቱን አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ካስተዋወቅህ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርብ። በትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 191-2 አንቀጽ 12-13 ላይ ተመሥርተህ ማበረታቻ በማቅረብ ደምድም።
20 ደቂቃ፦ “የቤተሰብ አባላት የተሟላ ተሳትፎ ማድረግ የሚችሉበት መንገድ—በአገልግሎት።” በአንድ የቤተሰብ አባላት በውይይት የሚቀርብ። ቤተሰቡ የመስክ አገልግሎትን ሁሉም ሊሳተፉበት የሚገባ ቋሚ ሳምንታዊ ልማድ አድርጎ መመልከቱ ተገቢ የሆነበትን ምክንያት ተወያዩ። በመስከረም 1, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 17-18 አንቀጽ 9-12 ላይ የተሰጠውን ማበረታቻ ከልሱ። ከአድማጮች መካከል ለቤተሰባቸው ሳምንታዊ የአገልግሎት እንቅስቃሴ በማደራጀት ረገድ እንዴት ሊሳካላቸው እንደቻለ እንዲናገሩ አንዳንድ ወላጆችን ጋብዝ።
መዝሙር 31 (67) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47 (112)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ “መጨረሻው ሲቃረብ በምሥክርነቱ የምናደርገውን ተሳትፎ ማሳደግ።” ጥያቄና መልስ። በአንድ ወቅት በስብከቱ ሥራ እካፈላለሁ የሚል ሐሳብ እንኳ ያልነበራቸው ሆኖም የመንግሥቱን መልእክት ማዳረሱ አጣዳፊ እንደሆነ በመገንዘባቸው አሁን አዘውትረው ከሚያገለግሉ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አስፋፊዎች ሰዎች ወደሚገኙበት ቦታ እየሄዱ ለመመሥከር የሚያደርጉትን ጥረት ያጧጧፉበትን መንገድ በመግለጽ ከ1997 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 42-8 ላይ አጠር ያሉ ተሞክሮዎችን ጨምር።
መዝሙር 36 (81) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 35 (79)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ “የተወሰነ የመጽሔት ትእዛዝ አለህ?” ንግግር። የመጽሔት አገልጋይ ሆኖ በሚያገለግለው ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ቢቀርብ ይመረጣል። በየወሩ የሚደርሷችሁን የመጽሔቶች ብዛትና እንደተበረከቱ ሪፖርት የተደረጉትን አማካኝ ቁጥር ለጉባኤው አሳውቅ። መጽሔቶች እንዲባክኑ መፍቀድ የለብንም። የቆዩ ቅጂዎች ማበርከት የሚቻልበትን መንገድ ጠቁም።—የሐምሌ 1993 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1ን ተመልከት።
30 ደቂቃ፦ “አቅኚነት—ጊዜያችንን በጥበብ የምንጠቀምበት መንገድ!” ጥያቄና መልስ። በአንቀጽ 5-7 ላይ የቀረቡትን ተሞክሮዎች የሚናገሩ ሦስት ሰዎች መድብ። አቅማቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ ለረዳት ወይም ለዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ለማመልከት እንዲያስቡበት በማበረታታት ደምድም። ከጉባኤ የአገልግሎት ኮሚቴ አባላት ከአንዱ ማመልከቻውን ማግኘት ይቻላል። በግንቦት ረዳት አቅኚ ለመሆን አሁንም ማመልከት እንደሚቻል ጥቀስ።
መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 32 (70)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የሚያዝያ ወር ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስብ። የአገልግሎት ክልሎችን ለመሸፈን ባደረግነው ልዩ ዘመቻ ስለተደረገው እድገት ሪፖርት አቅርብ። በግንቦት መሸፈን ያለባቸው የአገልግሎት ክልሎች የትኞቹ እንደሆኑ ተናገር። በግንቦት ረዳት አቅኚ የሚሆኑትን ስም ዝርዝር አንብብ እንዲሁም ሌሎችም እንዲያመለክቱ አበረታታ። በቅርብ የወጡትን መጽሔቶች ለማበርከት የሚያስችሉ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦች ተናገር።—የጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8ን ተመልከት።
17 ደቂቃ፦ “ምን ባደርግ ይሻላል?” ትምህርቱን ከአድማጮች ጋር በአጭሩ ከከለስክ በኋላ በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኝ አንድ ወጣት (ወንድ/ሴት) የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ስላሉት እቅዶች ከወላጁ ጋር ሲነጋገር አሳይ። አንድ ላይ ሆነው የሐምሌ 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4ን ይከልሳሉ። ወላጁ በየካቲት 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14 እና በታኅሣሥ 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 17-19 ላይ ከቀረበው ማበረታቻ ጋር በሚጣጣም መንገድ ምክር ይሰጣል። አቅኚዎች ማሟላት ያለባቸው የሰዓት ግብ ስለተቀነሰ ልጁ ትምህርቱን ሲያጠናቅቅ አቅኚ መሆን ስለሚችልበት መንገድ ያስባል።
18 ደቂቃ፦ ከረዳት አቅኚዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በያዝነው ወር ረዳት አቅኚ ሆነው በማገልገል ላይ ከሚገኙ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ከነበሩ አንዳንድ አስፋፊዎች ጋር ቃለ ምልልስ ያደርጋል። ያገኙአቸውን አንዳንድ በረከቶች፣ ያከናወኗቸውን ነገሮች እንዲሁም በየዓመቱ ቢያንስ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ረዳት አቅኚ ለመሆን በጉጉት የሚጠባበቁበትን ምክንያት እንዲናገሩ ጋብዛቸው።
መዝሙር 43 (98) እና የመደምደሚያ ጸሎት።