ፈጣሪ የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት እንችላለን?
ባለፈው ዓመት ስለ አንተ የሚያስብ ፈጣሪ ይኖር ይሆን? (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ በማግኘታችን ሁላችንም ተደስተናል። መጽሐፉ በተለይ በዓለማዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ትምህርት ቢኖራቸውም በአምላክ የማያምኑ ሰዎችን ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህ መጽሐፍ ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄደውን የእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ፍላጎት ያሟላል።
በየወሩ እንዲበረከቱ የሚመረጡት ጽሑፎች ተግባራዊነት እንዲኖራቸው ሲባል ባብዛኛው ሁሉንም ሰው ሊያቅፍ የሚችል መልእክት ያላቸው ጽሑፎች ናቸው። ታዲያ እንዲህ ሲባል ፈጣሪ የተባለውን መጽሐፍ ከማበርከት መቆጠብ አለብን ማለት ነው? በጭራሽ! በዓመቱ ውስጥ በየትኛውም ጊዜ መጽሐፉን በአምላክ ለማያምኑ ሆኖም ጥቅም ያገኙበታል ለምንልላቸው እንግሊዝኛ የሚያነቡ ሰዎች ማበርከት እንችላለን። በተጨማሪም በአምላክ ቢያምኑም ስለ እርሱ ማንነት ወይም ምን ባሕርያትና ዓላማዎች እንዳሉት ትክክለኛ ግንዛቤ ለሌላቸው ሰዎች ማበርከት እንችላለን። ስለዚህ በአገልግሎት ቦርሳችሁ ውስጥ አንድ ቅጂ እንድትይዙና መጽሐፉን ቢያነብ ይጠቀማል ብላችሁ ለምታስቡት ለማንኛውም ሰው ለማበርከት ዝግጁ እንድትሆኑ እናበረታታችኋለን።