ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ነጠላ ቅጂዎችና ኮንትራት። ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ማበርከት እንድትችሉ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለው ብሮሹር ይኑራችሁ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመርም ጥረት አድርጉ። ሰኔ፦ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች። ሐምሌና ነሐሴ፦ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ እና የምትወዱት ሰው ሲሞት።
◼ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! የተባለውን መጽሐፍ አጥንተን ስንጨርስ ቀጥሎ የምናጠናው ስንሞት ምን እንሆናለን? የተባለውን ብሮሹር ይሆናል።
◼ ባለፈው ዓመት ጉባኤዎች የጉባኤ ፋይላቸውን በሥርዓት መያዝ የሚችሉበት የተሻለ መመሪያ ተልኮላቸው ነበር። እስካሁን እነዚህን ለውጦች ያላደረጉ ጉባኤዎች ተጨማሪ የእረፍት ቀኖች ያሉት የግንቦት ወር የጉባኤ ጸሐፊዎች ፋይላቸውን እንደገና በሥርዓት ለማስቀመጥና አስፈላጊ ያልሆኑትን ወረቀቶች ለማስወገድ ጥሩ አጋጣሚ ሊሰጣቸው ይችላል።
◼ በቅርቡ የሚደርሱን አዳዲስ ጽሑፎች:-
አረብኛ፦ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር 1999፣ ትራክት ቁ. 74፣ እሳታማ ሲኦል—ከመለኮታዊ ፍትሕ ጋር ይጣጣማልን?፤ እንግሊዝኛ፦ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር 1999፣ የቴፕ ክር “በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የሕይወታችሁ መንገድ ይሁን”፤ ፈረንሳይኛ፦ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር 1999፣ የ1999 ቀን መቁጠሪያ፤ ኑዌር፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
◼ በድጋሚ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው:-
አረብኛ፦ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፤ እንግሊዝኛ፦ አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት፣ ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፣ ዴሉክስ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም (Dbi12)፣ በኪስ የሚያዝ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም (Dbi25)፣ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣ ማውጫ 1986-1995፣ እውቀት፣ መዝሙር መጽሐፍ (ትልቁና ትንሹ)፣ የይሖዋ ምሥክሮችና ትምህርት፣ እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፣ ስለ አንተ የሚያስብ ፈጣሪ ይኖር ይሆን?፣ ሕይወት እንዴት ተገኘ . . .? (ትንሹ)፣ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፣ ትራክቶች (ሁሉም ዓይነት)፣ የመጠበቂያ ግንብ ጥራዝ (1989, 1990, 1994)፣ 24 የቴፕ ክሮች የሚይዝ ባዶ አልበም፤ የቪዲዮ ክሮች:- ቱ ዚ ኤንድስ ኦቭ ዚ ኧርዝ፣ ኒው ዎርልድ ሶሳይቲ ኢን አክሽን፣ ዘ ባይብል—አኪውሬት ሂስትሪ . . .፣ ዘ ባይብል—ኢትስ ፖወር . . .፤ የቴፕ ክሮች:- ምሳሌ፣ ማቴዎስ፣ የመንግሥቱ ዜማዎች (ቁ. 1, 2, 3, 4)፣ የውዳሴ መዝሙሮች (8 የቴፕ ክሮች)፣ የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመር፣ እውቀት (5 ክሮች)፣ ድራማዎች:- “ጅሆቫስ ጀጅመንት”፣ “ቲኦክራሲያዊ ዝግጅቶችን ማክበር ያለብን ለምንድን ነው?”፤ ፈረንሳይኛ፦ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
◼ በድጋሚ በእጃችን የሚገኙ ቅጾች:- የአገልግሎት ክልል ካርድ መያዣ ፕላስቲክ፣ S-12 (የአገልግሎት ክልል ካርድ)፣ S-13 (የአገልግሎት ክልል መዝገብ)፣ S-14 (የጽሑፍ ማዘዣ)፣ S-88 (የተሰብሳቢዎች ቁጥር መመዝገቢያ)፣ M-1 (የመጠበቂያ ግንብ ኮንትራት ቅጽ)። እባካችሁ ከእነዚህ ውስጥ የሚያስፈልጋችሁ ቅጽ ካለ እዘዙ።