የጥያቄ ሣጥን
◼ የጉባኤ አስፋፊዎች ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የመኖሪያ ቦታ ለመቀየር ሲዘጋጁ መታወስ ያለበት ነገር ምንድን ነው?
ወደ ሌላ ቦታ፣ ከተማ ወይም አገር የሚደረግ ማንኛውም የቦታ ለውጥ ተጨማሪ ሥራ እንዲሁም በአብዛኞቹ ሁኔታዎች የተወሰነ አለመረጋጋት ያስከትላል። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ስር ጥሩ ቲኦክራሲያዊ ልማዳችንን በቀላሉ ልናቋርጥ እንችላለን። ስለዚህ ዛሬ ነገ ሳንል በተዛወርንበት አካባቢ ከሚገኙ ወንድሞች ጋር ለመገናኘት የሚያስችል ተገቢ ዝግጅት ለማድረግ ልዩ ትኩረት መስጠት አለብን።
አንድ የጉባኤ አስፋፊም ሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ የቦታ ለውጥ ከማድረጉ በፊት የጉባኤውን ጸሐፊ ማነጋገሩ ጥሩ ነው። ግለሰቡ በሚሄድበት አካባቢ ያለው ጉባኤ አድራሻ ይታወቃል? ሁኔታው እንዲህ ከሆነ የጉባኤው ጸሐፊ ለዚያኛው ጉባኤ ጸሐፊ ደብዳቤ መላኩ ቀላልና የተሻለ አማራጭ ነው። አንድ አስፋፊ የቦታ ለውጥ ካደረገ ከደብዳቤው ጋር የአስፋፊ ካርዱ ተያይዞ መላክ አለበት። አስፋፊው ሁለቱንም የምክር መስጫ ቅጽ ቅጂዎች በእጁ ይዞ የማይሄድ ከሆነ ቅጾቹ አንድ ላይ ሊላኩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ የአዲሱ ጉባኤ አድራሻ ባይታወቅስ? የጉባኤው ጸሐፊ የቦታ ለውጥ የሚያደርገውን ሰው ስምና አዲሱን አድራሻውን ለቅርንጫፍ ቢሮው ከላከ ግለሰቡ ረጅም ጊዜ የሚፈጅ ፍለጋ ከማድረግ ሊተርፍ ይችላል። ተዛውሮ በሄደበት ቦታ ያለውን የጉባኤ አድራሻና የስብሰባዎቹን ሰዓት ለመስጠት ፈቃደኞች ነን። እንዲሁም ለአዲሱ ጉባኤ ወደ ክልላቸው ተዛውሮ የሄደውን ፍላጎት ያለው ሰው አድራሻ ማሳወቅ እንችላለን። የቦታ ለውጥ ያደረገው ሰው የጉባኤ አስፋፊ ከሆነ የጉባኤው ጸሐፊ መጻፍ እንዲችል የአዲሱን ጉባኤ የፖስታ አድራሻ ልንሰጠው እንችላለን።
ግለሰቡ በሄደበት አካባቢ አንድም ጉባኤ ከሌለ የወረዳ የበላይ ተመልካቹ አስፋፊውን ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪውን እንዲጎበኘው ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን። በተጨማሪም ለጉባኤ አስፋፊዎችና ቋሚ የጉባኤ ተሰብሳቢዎች ለሆኑ ሰዎች የመንግሥት አገልግሎታችን የመሳሰሉትን አስፈላጊ የሆኑ ጽሑፎች ልንልክላቸው እንችላለን። ግለሰቡ በእንዲህ ዓይነት ገለልተኛ ቦታ የሚኖር ከሆነ በተቻለ ፍጥነት የመጽሔቶቻችን ኮንትራት እንዲገባ ዝግጅት ማድረጉ ጠቃሚ ነው። እንዲሁም አስፋፊዎች በመስክ አገልግሎት የሚያበረክቷቸው አንዳንድ ጽሑፎች እንዲላኩላቸው ማዘዝ ይችላሉ። አንድ ሰው ጊዜ ሳያባክን በሄደበት አዲስ አካባቢ ‘ብርሃኑ እንዲበራ’ ማድረጉ መብት ብቻ ሳይሆን ጥበቃም ነው። (ማቴ. 5:16) በገለልተኛ አካባቢዎች የሚኖሩ አስፋፊዎች እንዲህ በማድረጋቸው ብዙ አስደሳች ተሞክሮዎች ተገኝተዋል። በአንዳንድ አጋጣሚዎች አንጻራዊ በሆነ ሁኔታ ሲታይ በአጭር ጊዜ ውስጥ አዳዲስ ቡድኖች አልፎ ተርፎም አዳዲስ ጉባኤዎች ተቋቁመዋል። በተጨማሪም ጥሩ የግል ጥናትና የስብሰባ ልማድ ማዳበር ጠቃሚ ነው። ምንም እንኳ በስብሰባ የሚጠናውን ጽሑፍ አንድ ላይ ሆነን በቤተሰብ መልክ ወይም አስፈላጊ ከሆነ በግል አንብበነው ሊሆን ቢችልም አንድ የተወሰነ ሰዓት መድቦ ስብሰባ ማድረጉ የተሻለ ነው። እንዲህ በማድረጋችን ይሖዋ ያበረታናል እንዲሁም ይባርከናል።—መዝ. 95:6፤ ዕብ. 10:25፤ 2 ዜና 16:9
ከላይ የተብራራው አብዛኛው ነገር የጉባኤ አስፋፊዎች ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ወደ ሌላ አገር በሚሄዱበት ጊዜም ሊሠራ ይችላል። የጉባኤያችሁ ጸሐፊ አዲሱን አድራሻችሁን ካሳወቀን በሄዳችሁበት አገር እናንተ በምትኖሩበት አካባቢ ያለው ጉባኤ ከእናንተ ጋር መገናኘት እንዲችል ለሚመለከተው ቅርንጫፍ ቢሮ እናሳውቃለን።
በገለልተኛ አካባቢዎች የሚኖሩ አስፋፊዎች በመስክ አገልግሎት ላይ ያደረጉት ጥረት ከዓለም አቀፉ የይሖዋ ሕዝቦች የመስክ አገልግሎት ሪፖርት ጋር እንዲካተት ቢያደርጉ ጥሩ ነው። በመሆኑም እነዚህ የመስክ አገልግሎት ሪፖርቶች በቅርብ በሚገኘው ጉባኤ በኩል ሊላኩ ይችላሉ። ወይም ቦታው በጣም ሩቅ ከሆነ ሪፖርቱ በቀጥታ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ሊላክ ይችላል። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲኖር ቅርንጫፍ ቢሮው የጉባኤ አስፋፊ ካርዱ የት ቢቀመጥ እንደሚሻል መመሪያ ሊሰጥና በገለልተኛ ቦታ ላይ ለሚገኘው አስፋፊ ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችሉ ሌሎች ዝግጅቶች ሊያደርግ ይችላል።
እርግጥ ግለሰቡ ቦታ የቀየረው እስከ ሦስት ወር ለሚደርስ አጭር ጊዜ ከሆነ ጉዳዩ የተለየ መልክ ይኖረዋል። አገልግሎታችን መጽሐፍ ላይ በተገለጸው መሠረት ከጉባኤው ለአጭር ጊዜ የሄዱ አስፋፊዎች የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን ወዲያውኑ በደብዳቤ (ወይም በስልክ) ለጉባኤያቸው ጸሐፊ መላክ ይኖርባቸዋል። ዋጋማ የሆነው የአገልግሎት ሰዓት በዓለም አቀፉ ሪፖርት ላይ ሳይጨመር እንዳይቀር ጉዳዩ የሚመለከታቸው በሙሉ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ እናበረታታለን። ግለሰቡ ከጉባኤው ርቆ የሄደው ከሦስት ወር ለሚበልጥ ጊዜ ከሆነ ጉባኤ ቀይሮ ለሄደ ሰው እንደሚደረገው ሁሉ የጉባኤ አስፋፊ ካርዱ መላክ አለበት። (እባክህ አገልግሎታችን መጽሐፍ ገጽ 104-5ን ተመልከት።)
ከላይ የተጠቀሱት አንዳንድ ነጥቦች ከቦታ ቦታ ለሚጓዙ አስፋፊዎችም ጠቃሚ ናቸው። በጉዟችን ወቅት ከወንድሞቻችን ጋር መገናኘታችን የጥበብ እርምጃ ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ እንድንበረታታም አጋጣሚ ይሰጠናል። ቅርንጫፍ ቢሮው ስብሰባ የሚደረግባቸውን ሰዓታትና ቦታዎች ሊያሳውቃችሁ ይችላል። በተጨማሪ ባሕር ማዶ በሚገኙ በአብዛኞቹ አገሮች ስልክ ማውጫዎች ላይ “የይሖዋ ምሥክሮች” [Jehovah’s Witnesses] ወይም “የመንግሥት አዳራሽ” [Kingdom Hall] በሚል የወንድሞች ስልክ ቁጥሮችና አድራሻዎች ተመዝግበው ይገኛሉ። ቅርንጫፍ ቢሮዎች ደግሞ “መጠበቂያ ግንብ” [Watchtower] ወይም “ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ማኅበር” [International Bible Students Association] በሚል ሊመዘገቡ ይችሉ ይሆናል። በአጠቃላይ ከላይ ለተዘረዘሩት ነጥቦች ትኩረት መስጠታችን ጥበቃ የሚያስገኝ ከመሆኑም በላይ ሥርዓታማ የሆነውን ዝግጅት እንድንከተል ያስችለናል።—1 ቆሮ. 14:40
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል2]
(ወደ ገጽ 7 ዓምድ 1 ዞሯል)
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል7]
የጥያቄ ሣጥን (ከገጽ 2 የዞረ)