የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/99 ገጽ 1
  • ከይሐዋ የተማርን ነን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከይሐዋ የተማርን ነን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመንግሥቱን አገልጋዮች ማሠልጠን
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
  • የይሖዋ ፍቅር መገለጫ የሆኑት ቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • የይሖዋ ምሥክሮች አገልግሎታቸውን ለማከናወን የሚሠለጥኑት እንዴት ነው?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • የአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት —ታላቅ የሥራ በር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 6/99 ገጽ 1

ከይሐዋ የተማርን ነን

1 በዛሬው ጊዜ በመለኮታዊ አመራር በ233 አገሮች ዓለም አቀፋዊ የትምህርት ፕሮግራም እየተካሄደ ነው። ይህ ዓለም የሚያቀርበው ማንኛውም ነገር ከዚህ ጋር ሊወዳደር አይችልም። ታላቁ አስተማሪያችን ይሖዋ ለዘላለም ሕይወት እንድንበቃ ሲያስተምረን አሁንም እንኳ ራሳችንን እንዴት መጥቀም እንደምንችል እያስተማረን ነው።—ኢሳ. 30:20፤ 48:17

2 መለኮታዊ ትምህርት የምንቀስምባቸው ትምህርት ቤቶች፦ ለይሖዋ ሕዝቦች ጥቅም ሲባል በአሁኑ ጊዜ በሥራ ላይ ያሉትን ትምህርት ቤቶች ተመልከት። በየሳምንቱ 87,000 በሚያህሉ ጉባኤዎች ውስጥ የሚመራው ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚልዮን የሚቆጠሩ የመንግሥቱ አስፋፊዎች ውጤታማ የምሥራቹ አገልጋዮች እንዲሆኑ ያሠለጥናል። በዚህ ትምህርት ቤት ተመዝግበሃል? ለሁለት ሳምንት በሚሰጠው የአቅኚነት አገልግሎት ትምህርት ቤት ከተካፈሉት በሺህ ከሚቆጠሩ ተማሪዎች አንዱ ነህን? ምናልባት የዘወትር አቅኚዎች የሚፈለግባቸው የሰዓት ግብ መቀነሱ ብዙዎች አቅኚ እንዲሆኑና በዚህ ትምህርት ቤት ለመካፈል እንዲበቁ ያስችላቸው ይሆናል። በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በዋና ዋና ቋንቋዎች የሚመራው ለሁለት ወር የሚቆየው የአገልጋዮች ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ያላገቡ ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች ተጨማሪ ቲኦክራሲያዊ ኃላፊነቶችን እንዲቀበሉ እያስታጠቃቸው ነው። ሁሉም ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች በየጊዜው በመንግሥት አገልግሎት ትምህርት ቤት በኩል ልዩ ትምህርት ያገኛሉ።

3 በፓተርሰን ኒው ዮርክ ያለው የመጠበቂያ ግንብ የትምህርት ማዕከል ሕንፃዎች ከፍተኛ ቲኦክራሲያዊ ስልጠና የሚሰጥባቸውን ሦስት ልዩ ትምህርት ቤቶች ይዘዋል። አምስት ወር የሚወስደው የጊልያድ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ኮርስ በውጭ አገር መስኮች በሚስዮናዊነት የሚሠማሩ አገልጋዮችን ያዘጋጃል። ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ የቅርንጫፍ ቢሮ ኮሚቴ አባሎች ስለ ቅርንጫፍ ቢሮዎች አደረጃጀት የሁለት ወር ኮርስ ይወስዳሉ። በግንቦት 1999 ደግሞ ለተጓዥ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጥ አዲስ የሁለት ወር ኮርስ ከዩናይትድ ስቴትስና ከካናዳ የመጡ 48 ተማሪዎች ባሉት አንድ ክፍል ተጀምሯል። ዞሮ ዞሮ ይሖዋ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች አማካኝነት ከሚሰጠው ስልጠና ሁሉም የይሖዋ አገልጋዮች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

4 የተማርነው ለምን ዓላማ ነው? አንድ የአስተዳደር አካል አባል እንዲህ ሲል ተናግሯል:- “ያሁኑ የትምህርት ፕሮግራማችን ዓላማ በየትኛውም ቦታ ያሉትን ሁሉንም የይሖዋ ሕዝቦች በምሳሌ 4:1-4 ላይ ወደ ተገለጸው የጉልምስና ደረጃ ማድረስ ነው።” ይሖዋ ለእያንዳንዳችን “የተማሩትን ምላስ” መስጠቱን ይቀጥል ዘንድ ምኞታችን ነው።—ኢሳ. 50:4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ