የአገልግሎት ስብሰባዎች
ግንቦት 31 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 20 (45)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ።” ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች ያሉትና ግለት ባለው መንገድ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ስለ መጽሐፉ ዋጋማነትና መጀመሪያ በወጣበት ወቅት ስለተሰጡት አስተያየቶች እንዲናገሩ ጋብዝ።
20 ደቂቃ፦ “ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት።” አንድ የመጽሐፍ ጥናት መሪ በመስክ አገልግሎት ሲካፈሉ የተቻላቸውን ያህል የተሟላ ተሳትፎ ለማድረግ ጊዜያቸውን እንዴት እንዳደራጁ ከሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። ሊሠራ የሚችል ፕሮግራም የማውጣቱን ጠቃሚነት ከገለጹ በኋላ አስፈላጊነቱንም ጠበቅ አድርገው ያብራራሉ። ዘግይቶ መጀመርን፣ አስቀድሞ እቅድ ያለማውጣት ድክመትን እንዲሁም በአገልግሎት ወቅት ጨዋታ ማብዛትና መገባበዝ የመሳሰሉትን ጊዜን ሊያባክኑ የሚችሉ ነገሮች እንዴት እንዳስወገዱ ይናገራሉ። የአካባቢውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጊዜን እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደሚችሉ የሚጠቁም ተግባራዊ ሐሳብ አቅርብ።
መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 19 (43)
7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ከይሖዋ የተማርን ነን።” አንድ ደቂቃ የማይሞላ የመግቢያ ሐሳብ ካቀረብህ በኋላ ትምህርቱን በጥያቄና መልስ ሸፍን። አድማጮች ከቲኣክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፣ ከአቅኚነት አገልግሎት ትምህርት ቤት፣ ከመንግሥት አገልግሎት ትምህርት ቤትና ከመሳሰሉት ያገኟቸውን አንዳንድ ጥቅሞች እንዲናገሩ ጋብዝ። እነዚህ ትምህርት ቤቶች የይሖዋን አገልጋዮች በአገልግሎቱ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ እንዴት እንደረዷቸው ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።
23 ደቂቃ፦ አንድ ሽማግሌ በ10/15/93 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8-11 ላይ ባለው “በትዕግሥት መጠበቅን ለመማር ያለብን ችግር” የሚል ርዕስ ላይ የተመሠረተና በተለይ በፍቅረ ንዋይ ወጥመድ ላይ ያተኮረ ለሥራ የሚያንቀሳቅስ ንግግር ያቀርባል። ትምህርቱን ጉባኤው ውስጥ ሊኖሩ ከሚችሉት የመስክ አገልግሎት ተሳትፎ መቀነስ፣ ለአገልግሎት መብቶች አለመጣጣር፣ ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት ከመግባት ወደ ኋላ ማለት፣ የግል ጥናትንና በሳምንቱ መሀል የሚደረጉ ስብሰባዎችን ችላ ማለት የመሳሰሉ ሁኔታዎች ጋር በማዛመድ አቅርብ።
መዝሙር 24 (50) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 30 (63)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ “ልትረዷቸው ትችሉ ይሆን?” አንድ ሽማግሌ ከአድማጮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። በጥቅምት 8, 1995 የእንግሊዝኛ ንቁ! ከገጽ 8-9 ላይ ያለውን ነጠላ ወላጆችን ስለ መርዳት የሚናገረውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ። አንዳንዶች በጉባኤው ውስጥ ካሉ ሌሎች ወንድሞችና እህቶች ለተቀበሉት ፍቅራዊ እርዳታ ያላቸውን አድናቆት እንዲገልጹ ጋብዝ።
መዝሙር 25 (53) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 33 (72)
7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ በቪዲዮዎችና በቴፕ ክር በተቀዱት ድራማዎች በሚገባ ተጠቀሙ። ማኅበሩ ያዘጋጃቸውን 10 የቪዲዮ ክሮችና 11 በቴፕ ክር የተቀዱ ድራማዎች በተሻለ መንገድ መጠቀም ይቻል ይሆን? እናንተና ቤተሰባችሁ ሁሉንም ካሴት አይታችሁታል? ወይም ሰምታችሁታል? የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችንን እንዴት እንደሚያጎለብቱልን፣ መንፈሳዊነታችንን እንዴት እንደሚያጠነክሩልንና ስለ እውነት ጥሩ ምሥክርነት እንደሚሰጡ በመግለጽ የአብዛኞቹን ርዕስ ከልስ። ከሁለት ወይም ከሦስት የቴፕ ክሮች በከፊል አጠር አድርገህ አሰማቸው። አድማጮች ቤተሰባቸውን ለማበረታታት ወይም አዳዲሶችን ወደ ድርጅቱ ለመምራት በተለይ ውጤታማ ሆኖ ያገኙት የትኛውን የቪዲዮ ክር ወይም በቴፕ ክር የተቀዳ ድራማ እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። ጥሩ ውጤት እንደተገኘ የሚያሳዩ አንዳንድ ተሞክሮዎችን ተናገር። (የ1999 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 51-2 ተመልከት።) እንግሊዝኛ ቋንቋ የሚረዱ ሁሉ በቪዲዮ ክሮችና በቴፕ ክር በተቀዱ ድራማዎች በጥሩ መንገድ እንዲጠቀሙባቸው አበረታታ።
10 ደቂቃ፦ ለግል ቤተ መጻሕፍታችሁ ትኩረት ትሰጣላችሁ? ባለፉት ሦስት ዓመታት 1,600 አዳዲስ ወንድሞችና እህቶች እንዳገኘን በመግለጽ ጀምር። ነገር ግን በዚሁ ጊዜ በወንድሞች እጅ የገባው አገልግሎታችን የተባለው መጽሐፍ ቅጂ 700 ብቻ ነበር። ስለ እነዚህ መሣሪያዎች ጠቃሚነትና ዋጋማነት አንዳችን ሌላውን እያሳሰብን ነው? ለቤተ መጻሕፍታችን ስለሚያስፈልጉት የትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ፣ ማመራመር፣ አምልኮ አንድነት፣ በሕይወት መትረፍ፣ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ መጽሔቶች ጥራዝ የመሳሰሉ ሌሎች ጽሑፎችስ ምን ማለት ይቻላል? በተጨማሪም ይህን አስመልክቶ በጉባኤው ውስጥ የሚስተዋለውንና መሻሻል የሚያስፈልገውን ነገር ለመጠቆምም ጊዜ መድብ። የተበላሹ መጽሐፎችን በአዲስ ቅጂዎች እንዲተኩ አበረታታ። ንግግርህን በምሳሌ 3:13-18 ደምድም።
18 ደቂቃ፦ “የምታዩት ውጫዊውን ሁኔታ ብቻ ነውን?” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። የምናገኛቸውን ሰዎች በችኮላ እንዲህ ናቸው ብለን ከመደምደም የምንቆጠበው ለምን እንደሆነ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ዮናስ ሰዎቹ መዳን የማይገባቸው ናቸው ብሎ በስህተት በፈረደባቸው ጊዜ ይሖዋ ያስተማረውን ትምህርት ባጭሩ ከልስ። (የነሐሴ 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ፣ ገጽ 21-2 አንቀጽ 17-19ን ተመልከት።) አድማጮች በአገልግሎት ክልላቸው ውስጥ ስላገኟቸው የተለያዩ ሰዎችና ፍርዱን ለይሖዋ በመተው አዎንታዊ አመለካከታቸውን እንዴት ጠብቀው እንደቆዩ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 34 (77) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 38 (85)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የሰኔ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በሐምሌ የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። በጉባኤው ውስጥ በበቂ መጠን የሚገኙትን ብሮሹሮች በመዘርዘር በአገልግሎት ስናስተዋውቅ ልናጎላቸው የምንችላቸውን አንድ ወይም ሁለት ገጽታዎች ጠቁም። ጥሩ ልምምድ የተደረገበት አንድ ሠርቶ ማሳያ ጨምረህ አቅርብ።
13 ደቂቃ፦ ይሖዋ አገልጋዮቹ እንዲሰደዱ ለምን ይፈቅዳል? የአምላክ መንግሥት አዋጅ ነጋሪዎች የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች በተባለው መጽሐፍ ገጽ 676-7 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረው ‘በአሕዛብ ሁሉ የተጠላን’ ነን። (ማቴ. 24:9) በአገልግሎት ስንካፈል፣ ከዓለማዊ ዘመዶቻችን ጋር ስንገናኝ ወይም ደግሞ የይሖዋ ምሥክር ካልሆኑ ሰዎች ጋር በሥራ ቦታ ወይም በትምህርት ቤት በምንውልበት ጊዜ ተቃውሞ ሊያጋጥመን ይችላል። ተናጋሪው አዎንታዊ በሆነ መልኩ ይሖዋ እንዲህ ያለውን ስደትና ተቃውሞ ለምን እንደሚፈቅድና መጽናታችን ደግሞ የኋላ ኋላ እንዴት በረከት እንደሚያስገኝልን ይገልጻል።
20 ደቂቃ፦ ሰዎች ወዳሉበት ሂዱ! በ1997 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 42-8 ላይ የተመሠረተ ንግግር። ዘወትር ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ምሥክርነት መካፈላችንን መቀጠል እንደሚገባን ግልጽ ቢሆንም በማንኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችሉን አጋጣሚዎችንም ለማግኘት እንጥራለን። ሌሎች በአውቶቡስ ሲሄዱ፣ በመንገድ ወይም በባሕር ዳር ሲጓዙ፣ የቆሙ መኪናዎችን በመቅረብ፣ በከባድ መኪናዎች ማቆሚያ ቦታ፣ በስልክና በደብዳቤ በመጠቀም እንዴት እንደዚህ ማድረግና ጥሩ ውጤት ማግኘት እንደቻሉ የሚገልጹ ተሞክሮዎችን ከዓመት መጽሐፉ ላይ ተናገር። ጊዜ ከፈቀደልህ አድማጮች የራሳቸውን ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ። ሁሉም አስፋፊዎች ሰዎች ባሉበት ቦታ ለመመሥከር የሚያገኙትን እያንዳንዱን አጋጣሚ እንዲጠቀሙበት አበረታታ።
መዝሙር 94 (212) እና የመደምደሚያ ጸሎት።