ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሐምሌና ነሐሴ፦ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም በአንድ ብር ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት እና የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን? መስከረም፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች ማበርከትና ኮንትራት ማስገባት።
◼ ከመስከረም ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር “ይሖዋ ለሕዝቡ ‘መጠጊያ’ ነው።” የሚል ይሆናል።