የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/99 ገጽ 2
  • የሐምሌ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሐምሌ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 7/99 ገጽ 2

የሐምሌ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ሐምሌ 5 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 3 (6)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የአገሪቱንና የጉባኤውን የሚያዝያ የመስክ አገልግሎት ሪፖርት አስመልክተህ ሐሳብ ስጥ።

20 ደቂቃ፦ “የይሖዋን እርዳታ ለማግኘት ጸልዩ።” አንድ ደቂቃ የማይሞላ የመግቢያ ሐሳብ ካቀረብህ በኋላ ትምህርቱን በጥያቄና መልስ ሸፍን። የተለያየ ዓይነት ያላቸው ከልብ የመነጩ ጸሎቶች ውጤታማ አገልግሎት በማከናወን ረገድ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱት እንዴት እንደሆነ ግለጽ። አድማጮች ያቀረቧቸው ወቅታዊ ጸሎቶች በአገልግሎታቸው እንዴት እንደረዷቸው የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ።—የጥቅምት 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32⁠ን ተመልከት።

15 ደቂቃ፦ “ብሮሹሮችን በሚገባ ተጠቀሙባቸው።” ሠርቶ ማሳያዎች ያሉት በንግግር የሚቀርብ ክፍል። ብሮሹሮች ለአገልግሎታችን ጠቃሚ መሣሪያ የሆኑት ለምን እንደሆነ ግለጽ። ብዙ ሰዎችን የሚነኩ ርዕሰ ጉዳዮችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ያቀርባሉ፣ አንድን መሠረታዊ ጭብጥ ባጭሩ ያብራራሉ እንዲሁም ቅዱስ ጽሑፋዊ ትምህርቶችን ቀለል ባለ መንገድ ያስረዳሉ። በዚህ ወር የሚበረከቱትን ብሮሹሮች ከጠቀስክ በኋላ በጉባኤው ውስጥ በበቂ መጠን የሚገኙትን አሳይ። ሁለት ወይም ሦስት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ።

መዝሙር 81 (181) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 94 (212)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ፦ “አስቀድሞ መዘጋጀት ደስታ ያስገኛል።” በንግግርና በቃለ ምልልስ የሚቀርብ። ዝግጅት ለመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴ ለምን የግድ አስፈላጊ እንደሆነና በምንሠራውም ሥራ እንዴት ከፍተኛ ደስታ ለማግኘት እንደሚያስችለን ግለጽ። (ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 39 አንቀጽ 1-3⁠ን ተመልከት።) አገልግሎት ከመውጣታቸው በፊት እንዴት እንደሚዘጋጁና ይህን ማድረጋቸው ደግሞ እንዴት እንደረዳቸው ከሚናገሩ ጥሩ ችሎታ ያላቸው ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ጋር ቃለ መጠይቅ አድርግ። ለአገልግሎት በመዘጋጀት በኩል ማመራመር የተባለውን መጽሐፍ ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳየውን በሚያዝያ 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 30 ላይ ያለውን ተሞክሮ ተናገር።

20 ደቂቃ፦ “‘ፍሬ ነገሩን’ እንናገር!” አድማጮች ተሳትፎ የሚያደርጉበትና ሠርቶ ማሳያዎች ያሉት ክፍል። ሰዎችን ቤታቸው ሄደን ስናነጋግር ሰሚ ጆሮ ለማግኘት ምን ማለት እንዳለብን የቀረቡትን እያንዳንዱን ሐሳቦች ከልስ። ተሞክሮ ያላቸው አስፋፊዎች ውጤታማ የሆኑ ሁለት ሦስት መግቢያዎችን በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። አድማጮች ተጨማሪ ሐሳብ እንዲሰጡና ክልላችሁ ውስጥ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ምን እንደሆነ የሚያሳዩ የሚያበረታቱ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 82 (183) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 33 (72)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ፦ የአንድ ድርጅት አባል መሆን አለብኝን? ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ገጽ 280-4 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። አብዛኛውን ጊዜ የመንግሥቱን መልእክት የሚቀበሉ ነገር ግን የአንድ ሃይማኖታዊ ድርጅት “አባል” መሆን የማይፈልጉ ሰዎች ያጋጥሙናል። “ድርጅት” የሚለውን ቃል ፍቺና የሚታየው የይሖዋ ድርጅት ተለይቶ የሚታወቅባቸውን ሰባት ነጥቦች ከልስ። ይህ ድርጅት ከሌሎች ለምን የተለየ እንደሆነና ከዚህ ድርጅት ጋር መተባበራችን ደግሞ በረከት የሚያስገኝልን እንዴት እንደሆነ ግለጽ።

መዝሙር 92 (209) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 95 (213)

15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የሐምሌ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። የጥያቄ ሣጥን።

10 ደቂቃ፦ ብሮሹር የማበርከቱ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? “ብሮሹሮችን በሚገባ ተጠቀሙባቸው” የሚለውን ክፍል ተመልከት። ብሮሹር በማበርከት የተሳካላቸው አንዳንድ አስፋፊዎች አቀራረቡን እንዴት እንደተጠቀሙበትና ምን ጥሩ ተሞክሮ እንዳገኙ እንዲናገሩ አድርግ። ብቃት ያላቸው አቅኚዎች ወይም አስፋፊዎች ሁለት ወይም ሦስት ሠርቶ ማሳያዎችን እንዲያቀርቡ አድርግ። የሚቻል ሆኖ ሲገኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ እንዲኖራቸው ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።

20 ደቂቃ፦ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት እያደረግን ነውን? የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በየካቲት 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19-22 ላይ የወጣውን ነጥብ ከአንድ ወይም ከሁለት የጉባኤ አገልጋዮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። በክልላችን ውስጥ ያሉትን የሚገባቸውን ሰዎች ፈልገን ማግኘትና ደቀ መዝሙር ማድረግ የሚገባን ለምን እንደሆነ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያቶችን ጎላ አድርገህ ግለጽ። (ማቴ. 10:11) እነዚህ ሰዎች በአካባቢያቸው በሚያዩአቸው ክፉና አምላካዊ ያልሆኑ ሁኔታዎች የሚያዝኑና የይሖዋ የቁጣ ቀን ከመምጣቱ በፊት እርሱን የሚፈልጉ ናቸው። (ሕዝ. 9:4፤ ሶፎ. 2:2, 3) ከእነዚህ መካከል ‘ለዘላለም ሕይወት ትክክለኛ ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች’ ይገኙበታል። (ሥራ 13:48 NW) የእኛ ተልዕኮ ኢየሱስ ያዘዘውን ሁሉ በማስተማር ሰዎችን ደቀ መዝሙር ማድረግ ነው። (ማቴ. 24:14፤ 28:19, 20) ከቤት ወደ ቤት የምናገኛቸውን ሰዎች ስናነጋግር፣ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ስንመሠክር እንዲሁም በመንገድ ላይ ለምሥክርነት ስንሰማራ የሰዎችን የመጀመሪያ ፍላጎት ማነሳሳት ብንችልም ደቀ መዝሙር የምናደርጋቸው ግን ተመልሰን ስንጠይቃቸውና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንመራ ነው። ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል የሚያሳዩ ተግባራዊ ሐሳቦችን ጠቁም።

መዝሙር 8 (21) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ