የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/99 ገጽ 2
  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 8/99 ገጽ 2

የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ነሐሴ 2 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 11 (29)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የአገሪቱንና የጉባኤውን የግንቦት የመስክ አገልግሎት ሪፖርት አስመልክተህ ሐሳብ ስጥ። ሁሉም አስፋፊዎች በነሐሴ ወር በመስክ አገልግሎት እንዲካፈሉ አበረታታ። ብሮሹር በማበርከት የተገኘ ጥሩ ተሞክሮና ለአንድ ባለ ሱቅ ሁለት ብሮሹሮች ሲበረከቱ የሚያሳይ ሁለት ደቂቃ የሚፈጅ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

17 ደቂቃ፦ “ውብ የሆነውን የይሖዋ ስም ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ።” አንድ ደቂቃ የማይሞላ የመግቢያ ሐሳብ ካቀረብህ በኋላ ትምህርቱን በጥያቄና መልስ ሸፍን። የተጠቀሱትን ጥቅሶች ጎላ አድርገህ ግለጽ።—ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 184-5 ተመልከት።

18 ደቂቃ፦ ወንድሞቻችንን እንወዳቸዋለን። በታኅሣሥ 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 15-17 ባሉት አንቀጽ 7-11 ላይ ተመስርቶ በአንድ ሽማግሌ የሚቀርብና አድማጮች ተሳትፎ የሚያደርጉበት ንግግር። ከወንድሞቻችን ጋር በደንብ መተዋወቃችን፣ ማበረታቻ መለዋወጣችንና እርስ በርስ እየተደጋገፍን ፈተናን መቋቋማችን የሚያስገኝልንን የጋራ ጥቅም ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ይህን በይበልጥ እንዴት ማከናወን እንደሚቻል ሐሳብ ስጥ። አድማጮች ሌሎች ከሰጧቸው ፍቅራዊ ማበረታቻ እንዴት ማነቃቂያና ጥንካሬ እንዳገኙ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 63 (148) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 9 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 58 (138)

8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

12 ደቂቃ፦ አቅኚዎች ሌሎችን ይረዳሉ—ምን እድገት ተገኝቷል? የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በንግግርና በቃለ ምልልስ ያቀርበዋል። በመስከረም 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ላይ ያለውን መመሪያ ከልስ። ይህ ዝግጅት ጉባኤው ውስጥ የተሠራበት እንዴት እንደሆነና እርዳታ ያገኙ ወንድሞች ያደረጉትን እድገት የሚገልጽ ሪፖርት አቅርብ። ከአንድ ወይም ሁለት አቅኚዎችና ከእነርሱ ባገኙት እርዳታ ከተጠቀሙ ጥቂት አስፋፊዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። ወደፊት እርዳታ የሚያገኙ አስፋፊዎችም ከዚህ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ እንዲጠቀሙ አበረታታ።

25 ደቂቃ፦ “አሁን አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል ትችሉ ይሆን?” አንድ ሽማግሌ በጥያቄና መልስ ያቀርበዋል። ብዙ አስፋፊዎች አቅኚ መሆን የሚችሉባቸውን አጋጣሚዎች አዎንታዊ በሆነ መልኩ ግለጽ። የተለመዱ ችግሮችን በመወጣት እንዴት ስኬት እንዳገኙ የራሳቸውን ተሞክሮ ከሚናገሩ አቅኚዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። ‘ለናሙና የቀረቡትን የዘወትር አቅኚነት ፕሮግራሞች’ ገጽታ በመጥቀስ ጥሩ እቅድ ማውጣት እንድናሟላ የሚፈለግብን የሰዓት ግብ ላይ ለመድረስ እንዴት እንደሚረዳን ጎላ አድርገህ ግለጽ። የአቅኚነት ማመልከቻውን ማግኘት የሚፈልጉ ካሉ ከስብሰባው በኋላ መውሰድ እንደሚችሉ አስታውቅ።

መዝሙር 91 (207) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 16 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 36 (81)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የነሐሴ ወር ሊያልቅ የቀሩት ሁለት ቅዳሜና እሁዶች ብቻ ስለሆኑ ሁሉም ወሩ ከማለቁ በፊት በአገልግሎቱ እንዲካፈሉ አበረታታ።

15 ደቂቃ፦ ፍላጎት ያሳዩ አዳዲስ ሰዎች የጋብቻን ቅዱስነት እንዲገነዘቡ እርዷቸው። አንድ ሽማግሌ ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ገጽ 248-249 ላይ ተመስርቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። ለመንግሥቱ መልእክት ጥሩ ምላሽ የሚሰጡ ነገር ግን ያለ ሕጋዊ ጋብቻ አብረው በመኖራቸው ምክንያት እድገት ለማድረግ የሚዘገዩ ወንዶችና ሴቶች ያጋጥሙናል። ክርስቲያኖች ክብራማ የሆነ ትዳር ሊኖራቸው እንደሚገባ እንዲገነዘቡ እንዴት መርዳት እንደምንችል ተወያዩ። (የጥር 8, 1992 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ከገጽ 26-7 ተመልከት።) እንደዚህ ያሉት ወንዶችና ሴቶች ጋብቻቸውን ሕጋዊ እስካላደረጉ ድረስ የጉባኤው አባል የማይሆኑት ለምን እንደሆነ እንዲያውቁ በዘዴ ለመንገር ምን ማለት እንደምንችል ሐሳብ ስጥ።

20 ደቂቃ፦ ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ የበኩላችሁን እያደረጋችሁ ነውን? ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። እያበረከትነው ካለነው ብዙ ጽሑፍ አንጻር ሲታይ ዓላማችን ሰዎቹ ከወሰዱት ጽሑፍ እንዲጠቀሙ ለመርዳት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር መሆን አለበት። አስፋፊዎች ተጨማሪ ጥናቶችን ለመምራት እንዳይችሉ እንቅፋት የሆነባቸው ምን እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። (1) ለማጥናት ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው። (2) ፍላጎት ያሳዩ አንዳንድ ሰዎች ለማጥናት ጊዜ የለንም ይላሉ። (3) ጥናት ከተጀመረ በኋላም መደበኛ ለማድረግ የሚያጠናውን ሰው ቤቱ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። በተጨማሪም አንዳንድ አስፋፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስለመምራት የሚሰማቸውን ስሜት ጥቀስ። (1) ‘የማስተማር ብቃቱ ያለኝ አይመስለኝም።’ (2) ‘በየሳምንቱ ጥናት ለመምራት ጊዜ የለኝም።’ (3) ‘ለሌላ ሰው ስል ግዴታ ውስጥ መግባት ይከብደኛል።’ (4) ‘በሌሎች የአገልግሎት መስኮች የማደርገው ተሳትፎ ይበቃል።’ ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ በግለሰብ ደረጃ ለመካፈል እነዚህን እንቅፋቶች እንዴት መወጣት እንደሚቻል የሚጠቁሙ አዎንታዊ ሐሳቦችን አቅርብ። ውጤታማ አስፋፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በመምራቱ ሥራ በመካፈላቸው ያገኙትን ደስታ እንዲናገሩ ጋብዝ።—የሚያዝያ 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ከአንቀጽ 3-8, 15 ተመልከት።

መዝሙር 75 (169) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 23 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 47 (112)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።

25 ደቂቃ፦ “የ1999 ‘የአምላክ ትንቢታዊ ቃል’ የአውራጃ ስብሰባ”—ከአንቀጽ 1 እስከ 11 ድረስ ተወያዩበት። አንቀጽ 8 እና 9 ሙሉ በሙሉ ይነበባሉ።

10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

መዝሙር 55 (133) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 30 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 83 (187)

8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የነሐሴ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። ሁሉም ሪፖርቶች ተጠናቅረው ከመስከረም 6 በፊት እንዲላኩ ለማድረግ የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች በየቡድናቸው ያሉት አስፋፊዎች በሙሉ ሪፖርት መመለሳቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።

15 ደቂቃ፦ ስለ ተስፋችሁ አስረዱ። አንድ ሽማግሌ ምሳሌ ከሚሆኑ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ አንድ ወይም ሁለት የሕዝብ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ ያደርጋል። እነዚህ ወጣቶቹ እኛ በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ለምን አትካፈሉም የሚል ጥያቄ ዘወትር ከዓለማዊ እኩዮቻቸው ይቀርብላቸዋል። ወጣቶቻችን ይህን አጋጣሚ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለተመሠረተው እምነታቸው ለመግለጽ የሚጠቀሙበት ቢሆንም ተጽእኖውን በመቋቋም በኩል ጥብቅ መሆን ያስፈልጋቸዋል። ሽማግሌውና ወጣቶቹ ትንባሆ ወይም አደገኛ ዕፆችን እንዲወስዱ ቢጋበዙ እንዴት ብለው መልስ መስጠት እንደሚችሉ ይወያያሉ። ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የተባለው መጽሐፍ ገጽ 277-81 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ከልሱ። ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት አጽንተው መያዛቸው እንዴት ሊጠብቃቸውና ለእውነትም ጥሩ ምሥክርነት ሊሰጥ እንደሚችል ግለጽ።

22 ደቂቃ፦ “የ1999 ‘የአምላክ ትንቢታዊ ቃል’ የአውራጃ ስብሰባ”—ከአንቀጽ 12 እስከ 20 ድረስ ተወያዩበት። አንቀጽ 13-15 እና 17 ሙሉ በሙሉ ይነበባሉ።

መዝሙር 52 (129) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ