ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መስከረም፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ነጠላ ቅጂዎችና ኮንትራት ማስገባት። ኅዳር፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ታኅሣሥ፦ በምድር ላይ ለዘላለም መኖር ትችላለህ።
◼ በመስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እሱ የወከለው ሰው የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ምርመራው እንዳለቀ ውጤቱን የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ ለጉባኤው አስታውቁ።
◼ ሽማግሌዎች የመመለስ ዝንባሌ ያላቸውን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦች በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-3 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲሠሩባቸው ልናሳስባቸው እንወዳለን።
◼ በጉባኤ የሚሰበሰቡ ሁሉ የግል ኮንትራታቸውን ጨምሮ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች ኮንትራት ሲያስገቡም ሆነ ሲያሳድሱ መላክ ያለባቸው በጉባኤ በኩል ነው።
◼ አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ ማኅበሩ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ማኅበሩ ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ነገሮች ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማስታወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። በልዩ ትእዛዝ የሚገኙት የትኞቹ ጽሑፎች እንደሆኑ እባካችሁ አስታውሱ።