ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ነጠላ ቅጂዎችና ኮንትራቶች ማስገባት። ኅዳርና ታኅሣሥ፦ እንግሊዝኛ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፣ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት ወይም ፍጥረት መጽሐፍ። አማርኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጣልያንኛ፣ ትግርኛ፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ኦሮምኛ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር። ጥር፦ የቆዩ መጻሕፍት።
◼ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ውስጥ የተካተተው አባሪ “የ2000 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም” ሲሆን ዓመቱን በሙሉ ስለምንጠቀምበት በጥሩ ሁኔታ ልንይዘው ይገባል።
◼ የጉባኤያችሁ የስብሰባ ሰዓት ከጥር 1 ጀምሮ የሚቀየር ከሆነ አዲሱን የስብሰባ ሰዓት የያዘ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶች ማዘዝ ያስፈልጋችሁ ይሆናል።
◼ ለ2000 የሚያገለግሉ የመታሰቢያ በዓል የመጋበዣ ወረቀቶች እያንዳንዱ ጉባኤ በሚካሄድበት ቋንቋ ተዘጋጅቶ ከዓመታዊው የቅጾች አቅርቦት ጋር ይላክላችኋል።
◼ ጉባኤዎች በጥቅምት ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2000 ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። ቡክሌቱ በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በእግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጣልያንኛ፣ በስፓኒሽ እና በትግርኛ ይገኛል።