የኅዳር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ኅዳር 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 67 (156)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “የስብከቱ ሥራ ለይቶ ያሳውቀናል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳቦች ከተናገርክ በኋላ ክፍሉን በጥያቄና መልስ አቅርብ። እውቀት መጽሐፍ ገጽ 173 አንቀጽ 8ን በመጠቀም አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ በአገልግሎት ለመሳተፍ ጥረት እንዲያደርግ ለማበረታታት ምን ማለት እንደምንችል በአጭሩ ተናገር።
20 ደቂቃ፦ “መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት ፈቃደኛ የሚሆነው ማን ይሆን?” በንግግርና በሠርቶ ማሳያዎች የሚቀርብ። ከአንቀጽ 4 ጋር በሚስማማ መንገድ ጽሑፎቻችን የያዟቸውን ቁምነገሮች ለመማር የሰዎችን ፍላጎት ማነሳሳት የምንችልባቸውን የተለያዩ መንገዶች ተናገር። እንዲህ ማድረግ የሚቻልበትን መንገድ የሚያሳዩ ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። አድማጮች ጥናት በማስጀመር ረገድ እንዴት ሊሳካላቸው እንደቻለ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 27 (57) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 90 (204)
በዚህ ሳምንት የሚቀርበው ፕሮግራም ለሽማግሌዎች አካል በደብዳቤ ይላካል።
መዝሙር 81 (181) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 93 (211)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “መጽሐፍ ቅዱስ ያለውን ኃይል ተመልከቱ!” የሚለውንና “አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም” የሚለውን (ከጥቅምት የመንግሥት አገልግሎታችን) አቅርብ። በሚቀጥለው ሳምንት ሁሉም የጥቅምት 1999 የመንግሥት አገልግሎታችንን ይዘው እንዲመጡ አሳስብ።
10 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በንግግር የሚቀርብ። የመንግሥት አዳራሹን በንጽሕናና በጥሩ ሁኔታ ለመያዝ ጉባኤው ያደረገውን ዝግጅት ተናገር።
20 ደቂቃ፦ ወላጆች—ቋሚ የሆነ የቤተሰብ ጥናት ፕሮግራም አላችሁ? ንግግርና ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። ቤተሰቦች አንድ ላይ ማጥናታቸው አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ግለጽ። (መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 37-8ን ተመልከት።) ለቤተሰብ ጥናት እንቅፋት የሚሆኑትን የሚከተሉትን ነጥቦች ጥቀስ:- (1) ልጆቹ በጣም ሕፃናት ስለሆኑ አይጠቀሙም የሚል ስሜት፣ (2) በጉባኤ ስብሰባዎች መካፈሉ ብቻ በቂ ነው የሚል አስተሳሰብ፣ (3) ሥራ ከመብዛቱ የተነሳ የሚሰማችሁ ድካም፣ እና (4) ቴሌቪዥን በመመልከት ፕሮግራማችሁ እንዲዛባ ማድረግ። (የግንቦት 15, 1994 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 11-12ን ተመልከት።) የቤተሰብ ራሶች ጥሩ የቤተሰብ ጥናት ልማድ በመከተል ረገድ መሰናክሎችን እንዴት እንደተወጡ እንዲናገሩ ጋብዝ። ይህ ጥረት፣ ቆራጥነትና ተባብሮ መሥራትን እንደሚጠይቅ አጉልተህ ግለጽ።
መዝሙር 97 (217) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 9 (26)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና የሒሳብ ሪፖርት። “አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም” የሚለውን (ከጥቅምት የመንግሥት አገልግሎታችን) አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ በጉባኤ ውስጥ የሚሰጣችሁን ሥራ እንዴት ትመለከቱታላችሁ? በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ጉባኤው በአግባቡ መንቀሳቀሱን እንዲቀጥል መከናወን ያለባቸው ብዙ አስፈላጊ ሥራዎች አሉ:- በጉባኤ የሚቀርቡትን ክፍሎች መዘጋጀት፣ ሌሎችን ወደ ስብሰባዎች ይዞ መምጣት ወይም ወደ አገልግሎት መውሰድ፣ አረጋውያንን መርዳት፤ እንዲሁም የመንግሥት አዳራሹንና ግቢውን ማጽዳት፣ መጠገንና መንከባከብ። እርዳታ እንድታበረክት ስትጠየቅ ምን ዓይነት ምላሽ ትሰጣለህ? አንዳንዶች ፈቃደኛ ላይሆኑ፣ እያቅማሙ ሊቀበሉ ወይም ነገሩን እስከ መጨረሻ ድረስ ተከታትለው ላያጠናቅቁ ይችሉ ይሆናል። የሥራ ኃላፊነቶችን መቀበልና ሥራውን ማጠናቀቅ አስደሳች መብት የሆነበትን ምክንያት ተናገር። በጉባኤው ውስጥ ያሉ ሁሉ በፈቃደኝነት ራስን የማቅረብ መንፈስ እንዲያሳዩ አበረታታ።—መዝ. 110:3 የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ፤ ኢሳ. 6:8
15 ደቂቃ፦ “ለመንግሥት አዳራሽ የግንባታ ሥራ ድጋፍ መስጠት ትችል ይሆን?” (የጥቅምት የመንግሥት አገልግሎታችንን ተመልከት።)
መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 96 (215)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የኅዳር ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስብ።
10 ደቂቃ፦ አዳዲሶች ስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ አበረታቷቸው። የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት በተባለው ብሮሹር ገጽ 14-15 ላይ ተመሥርቶ በአንድ ሽማግሌና በአንድ ወይም ሁለት የጉባኤ አገልጋዮች መካከል የሚደረግ ውይይት። አዳዲሶች ስብሰባዎች ላይ መገኘታቸው አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ተናገሩ። ብዙ ትምህርት፣ ማበረታቻና ድጋፍ የሚያገኙት በስብሰባዎች ላይ ሲገኙ ነው። እያንዳንዱ ስብሰባ የሚያስገኘውን ጥቅም በማብራራት አምስቱን ሳምንታዊ ስብሰባዎች ጥቀሱ። የጉባኤ ስብሰባዎች አምላካዊ ባሕርይ እንድናዳብር፣ መንፈሳዊነታችንን እንድንገነባ፣ ወደ ድርጅቱ እንድንጠጋ፣ ከሌሎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንድንመሠርትና የአገልግሎታችንን ዓላማ እንድንገነዘብ እንዴት እንደሚረዱን ተወያዩ። አዳዲሶች ወደ ስብሰባዎች እንዲመጡ ለማነሳሳት አድማጮች በብሮሹሩ እንዲጠቀሙ አበረታታ።
30 ደቂቃ፦ ሦስት ሽማግሌዎች የአውራጃ ስብሰባውን ፕሮግራም ይከልሳሉ። ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ነጥቦችን በመጥቀስ እያንዳንዳቸው የአንዱን ቀን ፕሮግራም ይሸፍናሉ።
መዝሙር 74 (168) እና የመደምደሚያ ጸሎት።