ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ኅዳር እና ታኅሣሥ፦ እንግሊዝኛ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፤ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት ወይም ፍጥረት መጽሐፍ። አማርኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጣልያንኛ፣ ትግርኛ፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ኦሮምኛ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? ጥር፦ የቆዩ መጻሕፍት። የካቲት፦ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
◼ ጉባኤዎች ከኅዳር የጽሑፍ ትእዛዛቸው ጋር የ2000 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ትእዛዝ መላክ መጀመር አለባቸው። በተጨማሪም የ1999 የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ጥራዞችን በዚሁ ጊዜ ማዘዝ አለባቸው። እነዚህ መጻሕፍት በእንግሊዝኛና በፈረንሳይኛ ይገኛሉ።
◼ በ2001 የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው እሁድ፣ ሚያዝያ 8 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል።
◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ እስከተያዘው ወር 20ኛ ቀን ድረስ የሚቀጥለው የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ካልደረሰው ለማኅበሩ ደውሎ ማሳወቅ አለበት።
◼ በቅርቡ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው አዳዲስ ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ፦ ማውጫ 1998፤ የ1998 መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ጥራዞች፤ የመንግሥቱ ጣዕመ ዜማዎች ቁ. 1-8 በሲዲ፤ የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመር በሲዲ።