የጥር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ጥር 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 46 (107)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ለዓለም ዓቀፍ ሥራችን በፈቃደኝነት የሚደረጉ መዋጮዎችን እንደምንቀበል በመግለጽ መጽሔት ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። የቤቱ ባለቤት መዋጮ ይሰጣል።
15 ደቂቃ:- “የይሖዋን ስም በምድር ዙሪያ ማሳወቅ።” በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 93-4 ላይ መደበኛ ያልሆነ ምስክርነትን በተመለከተ ተጨማሪ ሐሳብ ስጥ።
20 ደቂቃ:- ደም አልባ ሕክምና ለማግኘት በሕጋዊ ሰነድ የተደገፈ ምርጫ ማድረግ። (ሥራ 15:28, 29) ጥሩ ችሎታ ባለው ሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ስብሰባው ካለቀ በኋላ የተጠመቁ ምሥክሮች አንድ አዲስ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርግ ሰነድ የሚሰጣቸው ሲሆን ያልተጠመቁ ትንንሽ ልጆች ካሏቸው ለእያንዳንዱ ልጅ የመታወቂያ ካርድ ሊሰጣቸው ይችላል። እነዚህ ካርዶች የሚሞሉት ዛሬ አይደለም። እቤት በጥንቃቄ ሊሞሉ ይገባል ሆኖም አይፈረምባቸውም። ሁሉም ካርዶች የሚፈረምባቸው፣ የምሥክሮቹ ስምና ቀን የሚጻፍባቸው ከፊታችን የሚደረገው የመጽሐፍ ጥናት ስብሰባ ካለቀ በኋላ በመጽሐፍ ጥናቱ መሪ እርዳታ ይሆናል። ከመፈረማችሁ በፊት ካርዶቹ ተጠናቅቀው መሞላታቸውን አረጋግጡ። ምሥክር ሆነው የሚፈርሙት ሰዎች የካርዱ ባለቤት ሰነዱን ሲፈርም ማየት ይኖርባቸዋል። ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ከሁኔታቸውና ከአቋማቸው ጋር በሚስማማ መንገድ ሐሳቡን ከዚህ ካርድ ላይ በመውሰድ ለራሳቸውና ለልጆቻቸው የራሳቸውን መመሪያ ሊያዘጋጁ ይችላሉ። የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች በቡድናቸው ውስጥ ያሉት በሙሉ በቅድሚያ የተሰጠውን የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሞያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገውን ካርድ መሙላት እንዲችሉ አስፈላጊውን ትብብር ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።
መዝሙር 66 (155) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 31 (67)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ:- “ጽሑፎቻችንን በአግባቡ ተጠቀሙባቸው” የሚለውን ተወያዩበት።
20 ደቂቃ:- “ውይይት ለመጀመር በትራክቶች ተጠቀሙ።” በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ አዘውትራችሁ ስለምትጠቀሙባቸው አራት ትራክቶች ጥቀስ። በእያንዳንዱ ትራክት ውስጥ መልስ የተሰጠበት አንድ ጥያቄ አንሳ። ጥያቄውን በመጠቀም እንዴት ውይይት መጀመርና ምናልባትም ሰውዬውን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት እንደሚቻል አድማጮች ሃሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። ሁለቱን ትራክቶች በመጠቀም ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚችል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
መዝሙር 27 (57) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 95 (213)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች እና ከመስክ አገልግሎት የተገኙ ተሞክሮዎች።
15 ደቂቃ:- “የይሖዋን ቃል በየዕለቱ መርምሩ!” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር-2000 የሚለውን ቡክሌት ሁሉም በጥሩ መንገድ እንዲጠቀሙበት አበረታታ። ከገጽ 3-4 ላይ በሚገኘው መቅድም ላይ የተሰጡትን ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ። አስፋፊዎች በግልም ሆነ በቤተሰብ መልክ ያለማቋረጥ የዕለቱን ጥቅስና ሐሳቡን ለመመርመር ምን ልዩ ጥረት እንደሚያደርጉ እንዲናገሩ ጋብዝ።
20 ደቂቃ:- “እውነተኛ ትሕትና ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?” በየካቲት 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 3-7 ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። የትምህርቱን ተግባራዊ ገጽታ አብራራ:- ስህተትን አምኖ መቀበል፣ ለተሳሳተ ድርጊት ይቅርታ መጠየቅ፣ ዝቅተኛ ኑሮ ያላቸውን በአግባቡ መያዝ፣ ‘ከባሪያው ክፍል’ የሚመጣውን መመሪያ መቀበል፣ የማናውቀውን ወይም ያልገባን ነገር ካለ እንደማናውቀው ወይም እንዳልገባን ማመን፣ ጉረኛ አለመሆን፣ ዝቅ ተደርገው የሚታዩ ሥራዎችን አለመናቅ፣ . . . ወዘተ።
መዝሙር 68 (157) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 31 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 7 (19)
12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የጥር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውስ። ለጉባኤ እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
15 ደቂቃ:- ‘ምልክት ማድረግን’ በተመለከተ ለሚነሳው ጥያቄ የሚሆን መልስ። በሐምሌ 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 29-31 ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
18 ደቂቃ:- ሌሎች እውነተኛውን ሃይማኖት ለይተው እንዲያውቁ መርዳት የሚቻልበት መንገድ። ጥሩ ችሎታ ያለው አንድ የጉባኤ አገልጋይና ጥሩ ችሎታ ያላቸው ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች፣ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮችን ቢያደንቁም በሌሎች ሃይማኖቶችና በእኛ መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ ላይረዱ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ይወያያሉ። በግንቦት 8, 1995 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 20 ላይ የሰፈሩትን አሥር ነጥቦች ከልስ። አንድ ቅን ልብ ያለው ሰው እነዚህን ነጥቦች ማወቁ በእውነተኛውና በሃሰት አምልኮ መካከል ያለውን ልዩነት ብቻ ሳይሆን ከይሖዋ ሕዝቦች መማርና ከእነርሱ ጋር መተባበር ያለውን ጥቅምም እንዲገነዘብ የሚረዳው እንዴት እንደሆነ አብራራ።
መዝሙር 59 (139) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 48 (113)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
17 ደቂቃ:- የዳንኤል ትንቢት የተባለውን መጽሐፍ ከልስ። በንግግር እና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የአዲሱን መጽሐፍ ጎላ ያሉ ገጽታዎች ከልስ:- ትኩረት የሚስቡ የምዕራፎቹ ርዕሶች፣ ሕያው የሆኑት ሥዕላዊ መግለጫዎቹ፣ ከእያንዳንዱ ትምህርት በኋላ የቀረቡ አመራማሪ ጥያቄዎችን የያዙ ሣጥኖች፣ ዝርዝር ጉዳዮችን ግልጽ የሚያደርጉ ካርታዎችና ሰንጠረዦች። ሚካኤል በተለየ መንገድ እንዴት ‘እንደሚቆም’ የሚገልጸውን አበረታች ማብራሪያ ጥቀስ። (ገጽ 288-90) በአምላክ ቃል አስተማሪነታችን መጽናት ያለውን ጠቀሜታ አስረዳ። (ገጽ 311-12) ሁላችንም መጽሐፉን በጥንቃቄ ማንበብና ፍላጎት ያላቸውንም ሰዎች እንዲሁ እንዲያደርጉ ተግተን ማሳሰብ ይገባናል።
20 ደቂቃ:- ጥበብ ያለበት ምርጫ አድርገዋል። በጥቅምት 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 19-21 ከአንቀጽ 3-16 ላይ የተመሠረተ ንግግር። አቅኚዎች ሕይወታቸውን መልሶ በሚክስ ጠቃሚ መንገድ እየተጠቀሙበት እንዳለ የሚሰማቸው ለምን እንደሆነ የሚጠቁሙ አስተያየቶች ጥቀስ። በስብሰባው ላይ የተገኙ ሁሉ አቅኚ መሆን ስለሚችሉበት አጋጣሚ እንዲያስቡ አበረታታ።
መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።