የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/00 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 1/00 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥር፦ ከ1986 በፊት የታተመ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ማለትም መንግሥትህ ትምጣ፣ በሕይወት ተርፎ፣ ወጣትነትህ፣ የቤተሰብ ኑሮ፣ የአምልኮ አንድነት፣ ዘላለማዊ ዓላማ። የካቲት፦ ሁሉንም የቆዩ መጽሐፎች አበርክታችሁ ከጨረሳችሁ የቤተሰብ ደስታ የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ትችላላችሁ። መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያ፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች። ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ለማበርከት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ይዛችሁ በመሄድ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።

◼ ጥር 10 በሚጀምር ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚገኙት የተጠመቁ አስፋፊዎች በሙሉ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሞያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገው ሰነድ ይሰጣቸዋል። ለልጆቻቸው ደግሞ መታወቂያ ካርዱ ይሰጣል።

◼ ከመጋቢት ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት አዲስ የሕዝብ ንግግር “እውነተኛው አርማጌዶን—ለምን? መቼ?” የሚል ይሆናል።

◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ረቡዕ ሚያዝያ 19 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የሚውለውን የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ምንም እንኳን ንግግሩን ቀደም ብሎ መጀመር ቢቻልም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ የምትጠልቅበትን ሰዓት በአቅራቢያችሁ ከሚገኙ ምንጮች ጠይቃችሁ ተረዱ። እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን ቢያከብር ይመረጣል። በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች የሚጠቀሙ ከሆነ ምናልባት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ጉባኤዎች ለዚያ ምሽት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ ማግኘት ይችሉ ይሆናል። የሚቻል ከሆነ ሁሉም ከአጋጣሚው ሙሉ ጥቅም ማግኘት ይችሉ ዘንድ ሁለቱ ጉባኤዎች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች መካከል ከእንግዶች ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ፣ አዳዲሶችን ለማበረታታት የሚያስችል ቢያንስ የ30 ደቂቃ ጊዜ ብትመድቡ ጥሩ ይሆናል። በተጨማሪም ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴና ለመኪና ማቆሚያ ቦታ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። የሽማግሌዎች አካላት ካሁን ቀደም የተላከላቸውን የሚያዝያ 27, 1998 ደብዳቤ በመመልከት ለጉባኤያቸው ምን ዝግጅት ቢያደርጉ የተሻለ እንደሚሆን መወሰን አለባቸው።

◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው የ2000 ልዩ የሕዝብ ንግግር የሚቀርበው እሁድ ሚያዝያ 16 ይሆናል። የንግግሩ ርዕስ “የሰው ዘር ቤዛ ያስፈለገው ለምንድን ነው?” የሚል ይሆናል። የንግግሩ አስተዋፅዖ ይላክላችኋል። በዚህ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ያቀርቡታል። ማንኛውም ጉባኤ ከሚያዝያ 16, 2000 በፊት ልዩ ንግግሩን ማቅረብ አይኖርበትም።

◼ በዚህ ዓመት በሚደረገው ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ውስጥ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ ሆነው ለማገልገል ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው የዘወትር አቅኚዎች ወይም ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መረጃዎች በትልቅ ሉክ ወረቀት ጽፈው እስከ ጥር 20, 2000 ድረስ ሊልኩልን ይገባል:-1) ስም፤ 2) ዕድሜ፤ 3) የጥምቀት ቀን፤ 4) ነጠላ ወይም ያገባ መሆኑንና የሚያስተዳድረው ቤተሰብ ብዛት፤ 5) ከመቼ እስከ መቼ ማገልገል እንደምትችሉ [መጋቢት-ግንቦት?] 6) የምታውቋቸው ቋንቋዎች፤ 7) አመልካቹ አዘውትሮ ከቤት ወደ ቤት የሚያገለግል መሆን አለመሆኑን። ከዚያም የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ 1999 ያለውን የአመልካቹን አማካይ የአገልግሎት ሪፖርት እንዲሁም ድጋፉንና ፊርማውን ያሰፍራል።

◼ በቅርቡ የደረሱን፦ አረብኛ፦ ጋይዳንስ ኦቭ ጎድ፤ እንግሊዝኛ፦ የ2000 የቀን መቁጠሪያ፤ ፈረንሳይኛ፦ የ2000 የቀን መቁጠሪያ፣ ማውጫ 86-95

◼ በድጋሚ የደረሱን፦ እንግሊዝኛ፦ ቅዱስ ጽሑፍ ሁሉ፣ ፍጥረት፣ አገልግሎታችን፣ ጉድ ኒውስ ፎር ኦል ኔሽንስ፣ ማውጫ ከ30-85 እና ከ86-95፣ መጽሔት መያዣ ማኅደር፣ ባዶ የቴፕ ክር አልበም፤ የቴፕ ክሮች:- የቤተሰብ ደስታ፣ ጅሆቫስ ጃጅመንት አጌይንስት ሎው ዲፋይንግ ፒፕል፣ ፕሪዘርቪንግ ላይፍ ኢን ታይም ኦቭ ፋሚን፣ ዘፍጥረት፤ ሶማሊኛ፦ በደስታ ኑር

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ