የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/00 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 2/00 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች የካቲት:- መንግሥትህ ትምጣ፣ በሕይወት መትረፍ፣ ወጣትነትህ፣ የቤተሰብ ኑሮ፣ የአምልኮ አንድነትና ዘላለማዊ ዓላማ የመሳሰሉትን የቆዩ መጻሕፍት አበርክታችሁ ከጨረሳችሁ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ትችላላችሁ። መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያና ግንቦት:- የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች። ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ለማበርከት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ይዛችሁ በመሄድ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።

◼ በዚህ ዓመት የሚሰጠው የልዩ ንግግር ርዕስ “የሰው ዘር ቤዛ ያስፈለገው ለምንድን ነው?” የሚል ነው። ንግግሩ የሚቀርበው እሑድ ሚያዝያ 16, 2000 ይሆናል። ይህ ንግግር በቀጣዩ ሳምንት ረቡዕ ዕለት ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ለሚከበረው የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል በደንብ ያዘጋጀናል። የንግግሩ አስተዋጽዖ በጊዜው ይላክላችኋል። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ሊያቀርቡት ይገባል።

◼ በመጋቢትና በሚያዝያ ተጨማሪ የዕረፍት ቀናት ስለሚኖሩ ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል ያመቻል። ረዳት አቅኚ መሆን የምትችሉ ከወዲሁ እቅድ እንድታወጡ እናበረታታችኋለን።

◼ በልዩ ዘመቻ ወቅት በገለልተኛ የአገልግሎት ክልሎች ውስጥ የሚያገለግሉ አስፋፊዎችና አቅኚዎች ትራክቶችን፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹርና የእውቀት መጽሐፍ በመያዝ በሚገባ የተደራጁ እንዲሆኑ እናበረታታቸዋለን። ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ለመርዳት የቆዩ መጽሐፎችንና መጽሔቶችን መጠቀም ይቻላል። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተከታትሎ ለመርዳት እንዲቻል ጥሩ ማስታወሻ ያዙ።

◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች የአገልግሎት እንቅስቃሴ መመርመር ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸው ላይ መድረስ ያልቻሉ አቅኚዎች ካሉ ሽማግሌዎቹ እርዳታ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባቸዋል። ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት የማኅበሩን የጥቅምት 1 ዓመታዊ S-201 ደብዳቤዎች ተመልከቱ። በተጨማሪም የመንግሥት አገልግሎታችን 9-68 ገጽ 5 አንቀጽ 12-20ን ተመልከቱ።

◼ ጸሐፊው ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኞች የቀረበ መጠይቅ ቅጽ (S-82) የሞሉትን የተጠመቁ አስፋፊዎች ሁኔታ በሚመለከት የአካባቢ ሕንፃ ሥራ ኮሚቴው ያለው መረጃ ወቅታዊ መሆኑን መከታተል አለበት። በፈቃደኛ ሠራተኛው ሁኔታ ላይ ለውጥ ካለ ማለትም ወደ ሌላ ጉባኤ ከሄደ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ወይም ሽማግሌ ሆኖ ከተሾመ ወዲያውኑ አዲስ ቅጽ ተሞልቶ መላክ ይገባዋል። ፈቃደኛ ሠራተኛው የፖስታ ሣጥን ቁጥር ወይም ስልክ ቁጥር ከለወጠ ወይም በጉባኤ ውስጥ እንደ ቀድሞው በጥሩ አቋም ላይ የማይገኝ ከሆነ ሽማግሌዎች ወዲያውኑ ለአካባቢ ሕንፃ ሥራ ኮሚቴው በደብዳቤ ማሳወቅ ይገባቸዋል።

◼ ካሁን በኋላ የአካባቢ ሕንፃ ሥራ ኮሚቴው እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ አካባቢ ብቻ የተወሰነ ይሆናል። በሌላ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ የመንግሥት አዳራሽ ሥራዎችን በተመለከተ መጻፍ ያለባችሁ በቀጥታ ለቅርንጫፍ ቢሮው ይሆናል።

◼ ሽማግሌዎች ማንበብና መጻፍ በመማር ረገድ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አስፋፊዎች ተጨማሪ ትኩረት እንዲሰጡ እናበረታታቸዋለን። ያሉትን አጋጣሚዎች አስመልክቶ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ተወያዩ፤ እንዲሁም ከወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጋር ተነጋገሩበት።

◼ አማርኛ በደንብ ማንበብ የማይችሉ አስፋፊዎች ያሏቸው ጉባኤዎች M-202 ቅጽ በመጠቀም እንግሊዝኛ ወይም ትግርኛ የመንግሥት አገልግሎታችን ቅጂዎች እንዲላክላቸው መጠየቅ ይችላሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ