የየካቲት የአገልግሎት ስብሰባዎች
የካቲት 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 48 (113)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- “‘ቃሉን በጥድፊያ ስሜት ስበኩ።’” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 170 ላይ ተጨማሪ ሐሳብ አቅርብ። የስብከት እንቅስቃሴያችንን ማሳደግ የምንችልበትን ተግባራዊ ሐሳብ ጠቁም።
20 ደቂቃ:- “በምክንያት የማስረዳት ችሎታን ማዳበር የሚቻለው እንዴት ነው?” በንግግርና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። በምክንያት የማስረዳት ችሎታ ለአገልግሎት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነና እንዴት ልናዳብረው እንደምንችል አብራራ። ችሎታ ያላቸው ሁለት አስፋፊዎች አንቀጽ 3 ላይ የሚገኙትን ነጥቦች ደረጃ በደረጃ በመከተል ለአገልግሎት እንዴት እንደሚዘጋጁ ውይይት ካደረጉ በኋላ አቀራረባቸውን በሠርቶ ማሳያ ያሳዩ። ለምናገኛቸው ሰዎች ጽሑፍ መስጠት እንችል እንደሆነና እንዳልሆነ ለመወሰን የማሰብ ችሎታን መጠቀም እንደሚጠይቅ ለማሳየት መስክ አገልግሎት ላይ የሚያጋጥሙ ሁለት ወይም ሦስት ሁኔታዎችን ጠቅሰህ አስረዳ።
መዝሙር 70 (162) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 89 (201)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ:- “‘በጌታ ሆነው የሚደክሙ ሴቶች።’” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። ከመስከረም 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14- 15 አንቀጽ 18- 19 ላይ ተጨማሪ ሐሳብ አቅርብ። እህቶችን በፈቃደኛነት ለሚሰጡት እርዳታ፣ ለሚያከናውኑት ሌሎችን የሚጠቅም አገልግሎት እንዲሁም ቅንዓት ለታከለበት የስብከት እንቅስቃሴያቸው ከልብ አመስግናቸው።
20 ደቂቃ:- “በእምነት ጸንተን ለመቆም ምን ሊረዳን ይችላል?” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። የምንኖረው በመጨረሻው ቀን ውስጥ በመሆኑ ሁላችንም በአንዳንድ ሁኔታዎች ረገድ እርዳታ ያስፈልገናል። ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች ተስፋ አስቆራጭ በሆኑ ችግሮች የተዋጡትን ለማበረታታት ምን ማድረግ እንደሚችሉ ተናገር። (የመስከረም 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21-3 ላይ የሚገኘውን “ገንቢ የሆነ እረኝነት” የሚለውን ንዑስ ርዕስ ተመልከት።) ሁላችንም ጽኑ መንፈሳዊ አቋም ለማግኘት እርስ በርስ እንዴት ልንበረታታ እንደምንችል ግለጽ።—ሮሜ 1:11, 12
መዝሙር 37 (82) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 21 (46)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የየካቲትን የመስክ አገልግሎት ሪፖርት እንዲመልሱ አስታውሳቸው። ትራክቶችን በመጠቀም እንዴት ውይይት መጀመር እንደሚቻል ለማሳየት ባለፈው ወር የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 ላይ የቀረቡትን “አራት ቀላል ደረጃዎች” በአጭሩ ከልስ። ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም የሚለውን ትራክት በመጠቀም የእውቀት መጽሐፍን እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። በትራክቱ የመግቢያ አንቀጽ ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ካነሣህ በኋላ መዝሙር 37:29ን ጨምሮ ገጽ 3 ላይ የሚገኘውን የመጀመሪያ አንቀጽ አንብብ። ሰውዬው ፍላጎት ካሳየ እውቀት መጽሐፍ ገጽ 5 ላይ ሣጥኑ ውስጥ ያለውን አንብብ። ከዚያ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር ጋብዘው። በዚህ ወር ሁሉም አዲስ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ልዩ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል።
5 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
12 ደቂቃ:- የአካባቢ ሕንፃ ሥራ ኮሚቴዎች የሚያከናውኑትን ሥራ ማድነቅ። በነሐሴ 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ እንዲሁም መስከረም 1997ና ጥቅምት 1999 በወጡ ርዕሶች ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። አሁንም ገና ብዙ የሚሠራ ሥራ አለ። የአካባቢ ሕንፃ ሥራ ኮሚቴ የሚያከናውናቸውን የሥራ እንቅስቃሴዎች በመጥቀስ ለመንግሥት አዳራሽ የግንባታ ሥራ ጉጉት እንዲያድርባቸው አድርግ። ፈቃደኛ ሠራተኛ ሆኖ ለማገልገል ብቁ የሚሆነው ማን እንደሆነ ግለጽና ብዙዎች በፈቃደኛነት ራሳቸውን እንዲያቀርቡ አነሳሳ። ልዩ ሙያ ያላቸውም ሆኑ የሌላቸው በተለያዩ ጊዜያት በሚካሄዱ ፕሮጀክቶች ላይ ለአጭር ጊዜ ለማገልገል ከፈለጉ በሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በኩል “ለመንግሥት አዳራሽ ፈቃደኛ ሠራተኞች የቀረበ መጠይቅ” (S-82) ቅጽ መጠየቅ ይኖርባቸዋል። በመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ፕሮጀክት ከተካፈሉት መካከል ለአንዳንዶቹ ቃለ መጠይቅ አድርግላቸውና ያገኙትን ደስታ አክለህ ተናገር።—የሰኔ 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-19 አንቀጽ 15-16 ተመልከት።
18 ደቂቃ:- “ጽኑ እምነት በመያዝ ምሥራቹን መስበክ።” በትምህርቱ እንዲሁም አንቀጽ 1 እና 2 ላይ ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሰውና በትምህርተ ጥቅስ መካከል በተቀመጡት ጥቅሶች ላይ የተመሠረተ የሁለት ወይም የሦስት ደቂቃ ሕያው መግቢያ አቅርብ። ከዚያም ከአንቀጽ 3-12 ያሉትን በጥያቄና መልስ በሚደረግ ውይይት ሸፍን።
መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 42 (92)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች በቅርብ ከመስክ የተገኙ ተስማሚ የአገልግሎት ተሞክሮዎችን በአጭሩ እንዲናገሩ አድርግ።
10 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ:- “እንዴት እንደምታዳምጡ ተጠበቁ።” አንድ የቤተሰብ ራስ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ሆኖ ከጉባኤ፣ ከልዩና ከወረዳ እንዲሁም ከአውራጃ ስብሰባዎች ሙሉ ጥቅም ለማግኘት ምን ማድረግ እንደሚችሉ ይወያያሉ። የቤተሰቡ ራስ ሁሉም ይበልጥ በጥሞና ማዳመጥ እንዳለባቸው ይሰማዋል። ከስብሰባ በኋላ በተማሯቸው ነገሮች ላይ የበለጠ የመወያየትን አስፈላጊነት ጨምሮ በዝርዝር የቀረቡትን ሐሳቦች እየጠቀሱ እያንዳንዱን ነጥብ እንዴት በተግባር እንደሚያውሉ ይወያያሉ። በተቻለ መጠን የትኛውም የጉባኤ ስብሰባ እንዲሁም የአውራጃ ወይም የልዩና ወረዳ ስብሰባ ክፍል እንኳን እንዳያመልጣቸው ካደረጉት ቁርጥ ውሳኔ ጋር እንዴት ተስማምተው መኖር እንደሚችሉ ይወያያሉ።
20 ደቂቃ:- “ጽኑ እምነት በመያዝ ምሥራቹን መስበክ።” ባለፈው ሳምንት በመጀመሪያዎቹ 12 አንቀጾች ላይ ተመሥርቶ የቀረበውን ሐሳብ በአጭሩ ከከለስህ በኋላ ከ13-24 ያለውን በጥያቄና መልስ ውይይት አቅርበው። ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱትንና በትምህርተ ጥቅስ መካከል የተቀመጡትን ጥቅሶች በጥሩ ሁኔታ ተጠቀምባቸው።
መዝሙር 3 (6) እና የመደምደሚያ ጸሎት።