የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/00 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 3/00 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያ እና ግንቦት:- የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች። ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ለማበርከት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ይዛችሁ በመሄድ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሰኔ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በማስጀመር ላይ ትኩረት አድርጉ።

◼ በሚያዝያና በግንቦት በረዳት አቅኚነት ለማገልገል የሚፈልጉ አስፋፊዎች አሁኑኑ እቅድ ማውጣትና ማመልከቻቸውን ቀደም ብለው መመለስ ይገባቸዋል። ይህም ሽማግሌዎች አስፈላጊ የሆኑ የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶች እንዲያደርጉና በቂ መጽሔቶችና ሌሎች ጽሑፎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል። ረዳት አቅኚዎች ሆነው እንዲያገለግሉ የተፈቀደላቸው በሙሉ ስም ዝርዝራቸው በየወሩ ለጉባኤው መነበብ ይኖርበታል።

◼ በመጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይርቅ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እሱ የወከለው ሰው የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ምርመራው እንዳለቀ ውጤቱን የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከተነበበ በኋላ ለጉባኤው አስታውቁ።

◼ የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ረቡዕ ሚያዝያ 19, 2000 ይከበራል። ጉባኤያችሁ በዚያ ዕለት ስብሰባ የሚያደርግ ከሆነና የመንግሥት አዳራሹ ደግሞ በሳምንቱ ቀናት ውስጥ ነጻ የሚሆንበት ቀን ካለ ስብሰባው ወደ ሌላ ቀን መሸጋገር አለበት። እንዲህ ማድረግ የማይቻል ቢሆንና ይህም የአገልግሎት ስብሰባችሁን የሚነካ ከሆነ ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑ ክፍሎች በሌላ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ሊካተቱ ይችላሉ።

◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች፦

እንግሊዝኛ:- የቴፕ ክሮች:- ፋሚሊስ ሜክ ዴይሊ ባይብል ሪዲንግ ዩር ዌይ ኦቭ ላይፍ፤ ፈረንሳይኛ:- አወር ፕሮብለምስ፣ ኩዌስችንስ ፒፕል አስክ አባውት ጀሆቫስ ዊትነስስ፤ ትራክቶች:- ትራክት ቁ. 13 (የይሖዋ ምሥክሮች )፣ ትራክት ቁ. 71 (ዳዝ ፌት ሩል . . .? )፣ ትራክት ቁ. 74 (ሄልፋየር )፤ ኑዌር:- ትራክት ቁ. 15 (አዲስ ዓለም )

◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች፦

እንግሊዝኛ:- ፈጣሪ፣ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣ የሰው ዘር ያደረገው ፍለጋ፣ አፕላይ ዩርሰልፍ ቱ ሪዲንግ . . .፣ አወር ፕሮብለምስ፣ ዚስ ጉድ ኒውስ ኦቭ ዘ ኪንግደም፣ የንቁ! ጥራዞች (1987, 1989)፣ ዴሉክስ መጽሐፍ ቅዱሶች (Dbi12፣ Dbi25)፣ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም (bi12)፣ በCD የሚገኝ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች 1997፤ የቪዲዮ ክሮች:- ፐርፕል ትሪያንግልስ፤ አማርኛ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፣ ትራክት ቁ. 22 (ዓለምን የሚገዛው )፤ ሶማሊኛ:- በደስታ ኑር።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ