የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/00 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ንዑስ ርዕሶች
  • መጋቢት 13 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 20 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 27 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 3/00 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

መጋቢት 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 89 (201)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- “መልካሙን የምሥራች እንሰብካለን” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ ውይይት አቅርበው። እውቀት መጽሐፍ በአገልግሎት ላይ ሲበረከት ከመጽሐፉ አዎንታዊ የሆኑ ቅዱስ ጽሑፋዊ ነጥቦችን እንዴት መውሰድ እንደሚቻል ለማስረዳት ምሳሌዎችን ጥቀስ።

20 ደቂቃ:- “በሚያዝያ 2000 ከምንጊዜውም የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ እንችል ይሆን?” (ከአንቀጽ 1-11) ጥያቄና መልስ። ጉባኤው በቅርብ ያገኘው ከፍተኛ የረዳት አቅኚዎች ቁጥር ስንት እንደነበር ጥቀስ። በአገልግሎት የነበራቸውን ተሳትፎ ከፍ በማድረጋቸው በግል ያገኙትን ጥቅም እንዲናገሩ በዚያ ወቅት ረዳት አቅኚ ከሆኑት መካከል አንዳንዶቹን ጋብዝ። ጉባኤው በረዳት አቅኚዎች ረገድ በሚያዝያ አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ለማስመዝገብ ጥረት እንዲያደርግ አበረታታ። አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 113-14 ላይ ለረዳት አቅኚዎች የቀረቡትን ብቃቶች ከልስ። ረዳት አቅኚ መሆን የሚፈልጉ አስፋፊዎች ይህ ስብሰባ ካለቀ በኋላ የማመልከቻ ቅጽ ማግኘት ይችላሉ።

መዝሙር 83 (187) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 8 (21)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ:- “በበኩሌ ምን ማድረግ እችላለሁ?” አንድ የመጽሐፍ ጥናት መሪ ከአንድ ወይም ከሁለት የጉባኤ አገልጋዮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። አንዳንድ አስፋፊዎች ባላቸው የተለያየ የአቅም ገደብ ምክንያት ጉባኤው ለሚያደርገው እንቅስቃሴ እምብዛም አስተዋጽዖ ማበርከት እንደማይችሉ ይሰማቸው ይሆናል። ጉባኤውን ለማበርታትና የመንግሥቱን ሥራ ለማስፋፋት ሁላችንም ልናደርግ ከምንችላቸው ብዙ ጠቃሚ መንገዶች መካከል ጥቂቶቹን ተናገር። እያንዳንዱ “በመጨረሻ በሚሰጠው ሪፖርት ተካፋይ” ለመሆን የበኩሉን ማድረግ የሚችለው እንዴት እንደሆነ በመናገር ክፍሉን ደምድም።​—⁠አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ላይ ገጽ 108-10 ተመልከት።

20 ደቂቃ:- “በሚያዝያ 2000 ከምንጊዜውም የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ እንችል ይሆን?” (ከአንቀጽ 12-18) ጥያቄና መልስ። በግል የምናውቀውን አንድን ግለሰብ በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኝ እንዴት እንደምንጋብዝ የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ ጨምረህ አቅርብ። በ2000 የቀን መቁጠሪያ ላይ የሚያዝያን ወር ከልስና ጉባኤው ለመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች ያደረገውን ዝግጅት ግለጽ። ጉባኤው ሙሉ በሙሉ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችል እያንዳንዱ አስፋፊ በወሩ ውስጥ በተቻለው መጠን በአገልግሎት ለመካፈል ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፕሮግራም እንዲያወጣ አሳስብ። ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ ረዳት አቅኚ እንዲሆኑና ከዚህ ስብሰባ በኋላ የማመልከቻ ቅጽ እንዲወስዱ አበረታታ።

መዝሙር 51 (127) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 81 (181)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የመጋቢት የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውስ። በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉትን ስም ዝርዝር ተናገር። አሁንም ማመልከቻ ለመስጠት ጊዜው እንዳላለፈ ግለጽ። በወሩ ውስጥ ሊደረጉ የታቀዱትን የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ፕሮግራሞች በሙሉ ዘርዝር። የሚያዝያን ወር በጥሩ ሁኔታ ለመጀመር እንዲቻል በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ሁሉም በአገልግሎት እንዲካፈል አበረታታ። በወሩ ውስጥ የምናበረክተው የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎችን ይሆናል። በቅርብ ጊዜ የወጣውን እያንዳንዱን መጽሔት ውጤታማ በሆነ መንገድ ማበርከት እንደሚቻል ለማሳየት አንድ ርዕሰ ትምህርት መርጠህ ተስማሚ የሆነ የመወያያ ነጥብ አዘጋጅ። እያንዳንዱ አስፋፊ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር በመያዝ ፍላጎት ለሚያሳዩ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት ለማድረግ ሊጠቀምበት ይገባል።

12 ደቂቃ:- “የሌሎችን እርዳታ ጠይቅ።” አንድ ሽማግሌ ከአድማጮች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። በየጊዜው ሁላችንም አንድ ዓይነት እርዳታ የሚያስፈልገን እንዴት እንደሆነ ግለጽ። እርግጥ ነው እያንዳንዱ የራሱን ሸክም መሸከም አለበት። (ገላ. 6:​5) ይሁን እንጂ ብቻችንን መቋቋም የማንችለው ችግር ካጋጠመን በመንፈሳዊ የጎለመሱ የጉባኤ አባላትን እርዳታ ለመጠየቅ ማመንታት አይገባንም። ሌሎች ሰዎች በደግነት የሰጧቸው እርዳታ እንዴት እንዳበረታታቸው የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።

8 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

15 ደቂቃ:- “ውዳሴ ነው ወይስ ሽንገላ?” በየካቲት 1, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 29-31 ላይ የተመሠረተ ንግግር። ከጉባኤው ሁኔታ ጋር በሚስማማ መንገድ አቅርበው።

መዝሙር 87 (195) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 33 (72)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች እና ከመስክ አገልግሎት የተገኙ ተሞክሮዎች። ሌሎች በአገልግሎት ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያበረታቱ በቅርቡ ከጉባኤው የአገልግሎት ክልል የተገኙና የተመረጡ ተሞክሮዎች ተጠቀም።

17 ደቂቃ:- “መንፈሳዊ እድገት ማድረጋችሁን ቀጥሉ!” በጥቅምት 1, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-31 ላይ የተመሠረተ ንግግር። አልፎ አልፎ የክለሳ ጥያቄዎችን በመጠየቅና ጉባኤው ሊሠራባቸው የሚገባውን ነጥቦች በማንሳት አቅርብ።

18 ደቂቃ:- ከባድ ኃጢአትን ማጋለጥ ይኖርብኛልን? በወጣቶች ላይ ያተኮረ በሽማግሌ የሚቀርብ ጠንከር ያለ ንግግር። በዘመናዊው ኅብረተሰብ ውስጥ በወጣቶች ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ በርካታ ችግሮች ተስፋፍተዋል:- የሥነ ምግባር ዝቅጠት፣ የዓመፅ መስፋፋት፣ የአደገኛ ዕፆች ሱሰኛነትና ለሥልጣን አክብሮት አለማሳየት። በለጋ ዕድሜ ላይ የሚገኙ አንዳንድ ወጣቶች የፈጸሙትን የሥነ ምግባር ብልግና ደብቀው ሁለት ዓይነት ሕይወት ይመራሉ። ይህ ደግሞ በጉባኤው መንፈሳዊ ደህንነት ላይ አደጋ ይፈጥራል። አንዳንዶች በተደጋጋሚ ከባድ ኃጢአት ሠርተው ያንን ደብቀው ማቆየት ይፈልጋሉ። በጉባኤ ውስጥ አንድ ወንድም ወይም አንዲት እህት የአምላክን ሕግ የሚጥስ ከባድ ጥፋት እንደሠሩ ብታውቅ ምን ማድረግ አለብህ? እንዲህ ያለውን ነገር ለሽማግሌዎች ካስፈለገም ለወረዳ የበላይ ተመልካቹ ሪፖርት ማድረግ ይገባል። ይህ ክርስቲያናዊ ታማኝነትን የሚመለከት ጉዳይ ነው። በጉባኤ ውስጥ በሚገኝ በማንኛውም ወንድ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው እህቶችም ቢሆኑ የደረሰባቸውን ጥቃት ማጋለጥ ይገባቸዋል። እንደዚህ ዓይነት ጥቃት የተፈጸመባቸው እህቶች በዝምታ ለብቻቸው መሰቃየት የለባቸውም። ከዚህ ይልቅ እንደዚህ ያለውን ብልሹ ምግባር ኃላፊነት ያላቸው ወንድሞች እንዲያውቁት ማድረግ አለባቸው። በጉባኤ ውስጥ ያለ ማንኛውም ወንድ ሥነ ምግባር የጎደለው ጥያቄ ቢያቀርብላቸው እንኳ ሪፖርት ማድረግ አለባቸው። በዘሌዋውያን 5:​1 ላይ የሚገኘውን መሠረታዊ ሥርዓት ልብ በል። (የነሐሴ 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 27-30ን ተመልከት) በተጨማሪም የወጣቶች ጥያቄ ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 68-9 ያለውን ተመልከት።

መዝሙር 69 (160) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ